• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ ለማምከን በሶማሊያ የተዘጋጀ ስትራቴጂክ ሰነድ

January 23, 2024 09:32 pm by Editor Leave a Comment

ሶማሊያ በኢትዮጵያ ላይ በወታደራዊ፣ በዲፕሎማሲ እና በሌሎችም ዘመቻዎች የምትከተለውን ስትራቴጂ የተመለከተው ሰነድ

ሚስጥራዊ ማስታወሻ

ለ፡  ሐሰን ሼክ ሞሃሙ፣ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት

A confidential Memorandum

To: HE. Hassan Sheikh Mohamoud President of the Somali Federal Republic

ከ፡ ሙክታር አይናሼ፣ የሶማሊያ መንግሰት የፀጥታ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝና አማካሪ፣ የሶማሊያ ዜጋ

–ግልባጭ፡

-ሃምዛ ባሬ፣ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር

-አብዲ ሃሺ አብዱላሂ፣ የላዕላይ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ

-አደም መሀመድ ኑር ማዶቤ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ፤ እና

-ለሁሉም የፌዴራል አባል ክልሎች ፕሬዚዳንቶች

ቀን፡ 22/01/2024

ጉዳዩ፡ የአደጋ ጊዜ ብሄራዊ መከላከያና የቀውስ አመራር ስትራቴጂ

Subject: EMERGENCY NATIONAL DEFENCE AND CRISIS MANAGEMENT STRATEGIES

I. የኢትዮጵያ የወራሪነት ተፈጥሮ፣

1.የስጋት ግምገማ ማድረግ፡

የኢትዮጵያን አይቀሬ ወረራ በተመለከተ ገፅታዎቹን፣ መጠነ ስፋቱን፣ አቅሙን፣ እና ምንጩን መረዳት የሚያስችል አስቸኳይ የደህንነት መረጃ በመሰብሰብ ትንተና መስራት፤ እንዲሁም የኢትዮጵያን እና የወረራ አጋሮች ማንነት፣ አቅምና አላማ የተመለከቱ መረጃዎችም አሰባስቦ ግምገማ ማካሄድ።

2. የብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤትን ሥራ ላይ ማዋል፡-

ከፍተኛ የፖለቲካ አመራርና የጦር አዛዦችን ጨምሮ ሁሉንም የሶማሊያ ፌዴራል ግዛቶችን ለአስቸኳይ ጉባኤ መጥራት።

በቅርብ የሚደረገውን የፕሬዝዳንት ሰኢድ ዴኒ በዓለ ሲመት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የማይናወጥ ሀገራዊ አንድነትና አላማ እንዲስተጋባበት በማድረግ የኢትዮጵያን ወረራ የሚመክት የአርበኝነት ስሜት እንዲስተጋባበት ማድረግ።

3. አገራዊ የአስቸኳይ ጊዜ ማወጅ፡

አገሪቷን ወደ ብሔራዊ የመከላከያ ዕዝ እንድትሸጋገር፣ የተቀላጠፈ የሀብት ማሰባሰብ ስራን በማረጋገጥና የኢትዮጵያውያን ያልተቀየረ የወረራ ስጋት እስክናሸንፍ ድረስ የሶማሊያ መንግስት በመከላከያ ተግባራት ላይ ብቻ ያተኩር ዘንድ ብሄራዊ የአደጋ ጊዜ ህግን ተግባራዊ ማድረግ።

4. ብሔራዊ የቀውስ አስተዳደር ቡድን፡

ከፌዴራል እና ከክልል በመጡ ከፍተኛ የፖለቲካ ሰዎች የሚመራ፣ ፈጣን ውሳኔ አሰጣጥ እና ከፕሬዝዳንቱ እና ከብሔራዊ የጸጥታው ምክር ቤት ጋር ውጤታማ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ብሔራዊ የቀውስ አስተዳደር ቡድን መፍጠር።  የቡድኑ ዋና አላማ በሶማሌዎች መካከል የፖለቲካ ትስስር መፍጠር እና የሃብት ማሰባሰብ ጥረቶችን ማስተባበር ሲሆን በተለይም ወታደራዊ ባልሆኑም የሀገር መከላከያ ዘመቻዎች ላይ ጭምር አፅንዖት በመስጠት…

5. የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ማሰማራት፡-

የወታደራዊ፣ የፖሊስ፣ የመረጃ እና ማካዊስሊ ሚሊሻ ሃይሎችን ያካተተ የተሟላ የሀገር መከላከያ መሠረተ ልማቶችን ማንቃት እና ማሰባሰብ እና ለመጪው ጊዜ ምላሽ ለመስጠት ለፈጣን እና ለአፋጣኝ ዝግጁነት ከፍ ያለ ሁኔታን ማስጀመር።

6. ስትራተጂካዊ ግንኙነት መዘርጋት፡

ስለሁኔታው እና ስለተወሰዱ እርምጃዎች በየጊዜው ወቅታዊ መረጃዎችን በመስጠት ከህዝቡ ጋር ግልጽ ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ።  የሶማሌ ህዝብን ለመከፋፈል የታለመውን ኢትዮጵያዊ ፕሮፓጋንዳ ለመመከት፣ የሀገር መከላከያ እርምጃዎችን ቀጣይነት ያለው ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያሉትን ሁሉንም የሚዲያ ጣቢያዎች ይጠቀሙ።

II. የብሔራዊ መከላከያ ኃይሎችን ማንቀሳቀስ

7. የሶማሌ ብሄራዊ ጦር ሰራዊትን ዘይላ አካባቢ ማሰማራት፡

የመከላከያ አቅሙን ለማጠናከር እና ኢትዮጵያ በአገራችን ላይ ለሚሰነዘረው አይቀሬ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ቢያንስ የሶማሌ ብሄራዊ ጦር ሰራዊትን SNA ወደ ዘይላ እና አካባቢው ማሰማራት።

8. የፑንትላንድ የጸጥታ ኃይሎችን በፌዴራል ዕዝ ስር ማድረግ፡-

የፑንትየንድ የጸጥታ ኃይሎችን በከፊል ስልታዊ በሆነ መንገድ አስቀምጦ በሶማሊላንድ ሳይላክ በሚገኘው የ SNA ኃይሎች ላይ ሊሰነዘር የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው።

9. በሶማሌላንድ ላይ በርካታ ወታደራዊ ግንባሮችን መክፈት፡

የሶማሌላንድን የውጊያ አቅም ላይ የሚያነጣጥሩ ሶስት ስትራቴጂክ ወታደራዊ ግንባሮች።

በተለይም በሶማሊላንድ ምስራቃዊ እና ምዕራባዊ አቅጣጫ ግንባሮችን በመፍጠር የሶማሊላንድን ወታደራዊ አቅም ማዳአም፣ ይህም የሶማሊያን አጠቃላይ ወታደራዊ ውጤታማነት ያሳድጋል።

10. በሶማሊላንድ የምእራብ አቅጣጫ ሶማሌላንድ የማካዊስሊ Macawisley ኃይሎችን ማሰባሰብና ማስታጠቅ።

በምእራብ ሶማሌላንድ የሚገኙትን የማዋዊስሊ ሃይሎች በማሰባሰብና በማስታጠቅ፣ በእነዚያ ክልሎች ባሉ የሶማሌ ማህበረሰቦች ዘንድ የሚገኙ  የፖለቲካ ቅሬታዎችንና ስሜቶችን ለሶማሊያ አጠቃላይ ወታደራዊ ዘመቻ ስኬታማነት ድጋፍ የማሰባሰብን አስፈላጊነት በመገንዘብ ለዚሁ ዓላማ እንዲጠቅሙን ማድረግ።

11. ስትራተጂያዊ ወታደራዊ ጥምረቶችን መፍጠር፡-

እንደ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታንያ ካሉ ወዳጅ አገሮች ጋር ሊደረጉ የሚችሉ ወታደራዊ ጥምረቶችን ወይም የደህንነት አጋርነቶችን መመርመር። እንዲሁም ቱሪክ፣ ግብጽ፣ ሳውዲ አረቢያ እና ኳታር በተመሳሳይ።

ኢትዮጵያን ለመግታት እና (የሶማሊያን) መከላከያ ሰራዊት አቅም ለማጠናከር ከሌሎችም ጋር ትብብርን ማማተር።

12. ወጣቶች የሶማሊያ መከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ማድረግ፡-

አገር ወዳድ ሶማሊያዊያን ለሀገር መከላከያው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማነሳሳትና የኢትዮጵያን የወረራ ስጋት ለማስገንዘብ ሰፊ ዘመቻ በማካሄድ የሶማሊያን የአርበኝነት ስሜት እንዲቀሰቀስ ማድረግ።

III. መላውን (በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኝ) ሶማሌዎችነ ለአንድ አላማ ማሰባሰብ

13. ህዝባዊ ግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎች፡

በሶማሊያ ብሄራዊ ደህንነት፣ ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ላይ ያለውን አደጋ በማሳየት በሁሉም ዘርፍ በሚገኙ የሚዲያ ቻናሎች በኩል ለህብረተሰቡ ጥልቅ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ዘመቻዎች ማካሄድ፣ ይህም የጋራ ሀገራዊ ርምጃ አስፈላጊ ስለመሆኑ አጽንኦት የሚሰጥ ይሆናል።

መረጃን በብቃት ለማሰራጨት ማህበራዊ ሚዲያዎችን፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥንና የማህበረሰብ መድረኮችን መጠቀም።

14. የሶማሌ ሲቪል ማኅበራትን ለአላው እንዲቆሙ ማድረግ፡-

የሶማሌ ሲቪል ማኅበራት ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ሊሰነዘርባት ከሚችለው ወረራ ለመከላከል ሊወስዱት በሚችሉት ወሳኝ ሚና ዙሪያ ማብራሪያ ለመስጠት በሁሉም የአገሪቱ ከተሞች በሚገኙ አዳራሾች የማህበረሰብ ስብሰባዎች ማካሄድ።  የሲቪል ማኅበራት የሚያበረክቱትን ልዩ አስተዋጾ ለማጉላት ግልጽ ውይይቶችን ማጠናከር፣ ቨተለይም የአገሪቱን የውጭ ሥጋቶች የመቋቋም አቅም ለማጠናከር ድርጅቶቹ የሚኖራቸውን ፋይዳ በማጉላት መወያየት።

15. የስደተኞች መብት፡

በሶማሌ ግዛቶች የሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች በተመለከተ አለም አቀፍ ህጎችን ማክበር። 

16. የሶማሌ የንግድ ማህበረሰብን ማሰባሰብ፡

ዋናውን ጉዳይ በማጉላት በሶማሊያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር ለንግዱ ማህበረሰብ ጥሪ ማቅረብ።

▪የጋራ መስዋዕትነት አስፈላጊነት

17. ከሶማሌ ዲያስፖራዎች ጋር መገናኘት፤ በተቻለ ፍጥነትም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲያስፖራ ንቅናቄ ማእከል መፍጠር።

IV.  ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ

18. አፋጣኝ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን መመስረት፡-

ከዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ከተፅዕኖ ፈጣሪ የዓለም ኃያላን መንግሥታት ጋር ለመነጋገር አፋጣኝ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ማድረግ፤ የሶማሊያን የግዛት አንድነት የሚጥስ የኢትዮጵያን ተንኮል-አዘል ጥቃት በማስገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰብ፤ ግንዛቤም ማስጨበጥ።

19. የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአስቸኳይ መሾም፡

ጥሩ ብቃትና አቆም ያለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሾም በዚህ ሀገራዊ ቀውስ ውስጥ የሶማሊያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ውጤታማ ለማድረግ ይጠቅማል።

20. ከኢትዮጵያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማቋረጥ፡

አምባሳደሩን በፍጥነት በማባረር እና ሞቃዲሾ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአስቸኳይ እንዲዘጋ በማድረግ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጥ።

21. የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ENDF እንዲወገዱ ትዕዛዝ ማስተላለፍ፡-

ማንኛውም የ ATMIS የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ከሶማሊያ ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ ትእዛዝ መስጠት።22. ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግ የትኛውንም የድርድር ጥሪ ውድቅ ማድረግ፡-

የአፍሪካ ህብረት ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ለመነጋገር ያለውን የማይረባ ሃሳብ ፈፅሞ መተው፤ አፍሪካ ኅብረት ኢትዮጵያ በሶማሊያ ላይ የምትፈጽመው የጥቃት ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም በግልጽ መጠየቅ አለበት። ሚስተር ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ የሶማሊያን ምድር እንዳይረግጡ መታገድ አለባቸው።

23. አለም አቀፍ የመንግስታት መድረኮችን መጠቀም፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ)ን ጨምሮ ቁልፍ በሆኑ የባለብዙ ወገን መድረኮች ድጋፍ እንዲደረግልን በንቃት በመከታተል ኢትዮጵያ በህዝባችን ላይ የምትፈፅመውን ያልተጠበቀ ጥቃትና የጸጥታ ስጋት ማጉላት።

24. ከኢጋድ አባልነት መውጣት፡-

ኢትዮጵያ በሶማሊያ በኢጋድ ማዕቀፍ ውስጥ መግባቷ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂካዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ምኞቷን ማሳያ ነው።  በሶማሊያ ያለው ቀውስና የፖለቲካ አለመረጋጋት የኢትዮጵያን የብሔራዊ ደህንነትና የቀጣናዊ ተፅእኖ ግቦች ለማሳካት ነው የሚሰራው። ኢትዮጵያ በሶማሊያ የፖለቲካ ልሂቃን ውስጥ ጎጂ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ተግባር በመፈፀም የህዝባችንን የፖለቲካ አንድነት ለመናድ ላለፉት ሶስት አስርት አመታት ውስጥ በቋሚነት ሰርታለች።

25. Global Media Advocacy፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር እና በአፍሪካ ህብረት መርሆዎች የተጠበቁትን የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ጥሰት በማሳየት የኢትዮጵያን ወረራ ለማጉላት ከአለም አቀፍ ሚዲያዎች ጋር በጋራ መስራት። እንዲሁም የኢትዮጵያን ያልተቋረጠ ጥቃትና የመስፋፋት ስትራቴጂክ ጥረቶችን በመቃወም አለም አቀፍ የሆነ ህዝባዊ አቋም እንዲጎለብት መትጋት። ይህ ለአለም አቀፍ ግንኙነትና ፖለቲካ ባለሙያዎች ጥሪ ማድረግን የሚያካትት ነው።

26. ዓለም አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ፡

ለሀገራችን ለሶማሊያ ዓለም አቀፍ ርኅራኄ እና ድጋፍ ለማስገኘት የኢትዮጵያ ጥቃት ሊያስከትል የሚችለውን አለመረጋጋት በተከታታይ በመግለጽ፣ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የግጭቱን ታሪካዊ ሁኔታ ለማሳወቅ ጠንካራ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዘመቻዎች ማካሄድ፣

27. አለምአቀፍ ህግጋትን መጠቀም፡-

ከአለም አቀፍ የህግ አካላት ጋር በመተባበር፣ በወራሪዋ/ኢትዮጵያ ላይ ክስ በማቅረብ እና ለቅጣት ወይም ሌሎች እርምጃዎችን በመፈተሽ በአለም አቀፍ ደረጃ የህግ ድጋፎችን ማፈላለግ

V. ኢትዮጵያ ላይ ኢኮኖሚ አድማዎችና ማዕቀቦች መጣል፡-

28. የኢኮኖሚ ቦይኮት፡

ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የንግድና የንግድ ግንኙነት በስትራቴጂክ መለኪያዎች መሰረት ማቋረጥ።  በተለይም ወደ ሶማሊያ የሚገባውን የኢትዮጵያ ጫት እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች በማገድ የኢኮኖሚ ጫና መፍጠር።

29. የአየር ትራፊክ ገደቦችን መጣል፡

የሶማሊያን አየር ክልል ሙሉ በሙሉ ለኢትዮጵያ አቪዬሽን በረራዎች ዝግ ማድረግ፣ (የሲቪልም ሆነ ወታደራዊ በረራዎችን)።

በ ATMIS ተልዕኮ ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገልግሎት ለመስጠት የተፈቀደላቸው በረራዎችን ብቻ መፍቀድ። 

30. በሶማሌላንድ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ መጣል፡

የፋይናንስ ስርዓቶችን ኢላማ ያደረጉ የቅጣት ርምጃዎችን ይፋ ማድረግ፣ የሶማሊያን ቴሌኮሙኒኬሽን (የሀገረ ሶማሊያ ኮድ 252 እንዳትጠቀም ማቋረጥ፣ (በዚህም የአለም አቀፍ ጥሪዎችን እና የኤሌክትሮኒክስ ግብይቶችን ማስቆም)፣ የአየር ጉዞ፣ የዲፕሎማሲያዊ ኮንትራቶችና የአየር ክልል ገደቦች መጣል። እንደ ምግብ እና መድሃኒት ያሉ የሰብአዊ እርዳታዎችን ብቻ መፍቀድ።

SOOMAALIYA HA NOOLAATO (ሶማሊያ ለዘላለም ትኑር)

ሙክታር አይናሼ

Mobile +47 901 25 961

Email: mainashe@gmail.com

እስሌማን ዓባይ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Politics Tagged With: Ethiopian Navy, Port of Ethiopia, somalia, Somaliland

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule