
የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ፣ የሀገርን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችልና ከውስጥና ከውጭ የሚመጡ ችግሮችን የሚመክት ዘመናዊ ባህር ሃይል መገንባት፣ ማደራጀትና ማሰልጠን አስፈላጊ መሆኑን ተናገሩ፡፡
ኮሞዶሩ በባህር ዳር ተገኝተው የባህር ሃይል መሠረታዊ ባህረኞች በውሃ አካል ላይ የሚሰጡ ግዳጆችን ለመወጣት የሚያስችል የውሃ ዋና ሥልጠና ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት፣ የውጭ ሃገራት የእጩ መኮንን ሥልጠናዎችን እና ደብረ ዘይት ባቦጋያ ት/ቤት የውሃ ዋና እና የመርከብ የተግባር ሥልጠናዎችን ማከናወን መቻሉን አስረድተዋል፡፡
አሁን የሚሰጣችሁ ሥልጠና በመርከብ ላይ ሊደረጉ የሚገቡ የጥንቃቄ፤ የአደጋ መከላከል ደንቦችና በውሃ አካል ላይ የሚሰጡ ግዳጆችን ሊያሳልጥ የሚችል ትምህርት በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
ይህ የስልጠና አቅም የኢትዮጵያን ባህር ሃይል በፍጥነት ለግዳጅ ዝግጁ ከማድረግ አንፃር ጠቀሜታው ስትራቴጂካዊ ሲሆን በሀገራችን መከላከያ ሃይል ላይ ተጨማሪ የማድረግ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
የመሠረታዊ ባህረኞች አስተባባሪ ሊውትናንት ቡሰሪ ቡልጉ እና መሠረታዊ ባህረኛ ሰልጣኝ ሊድ ሲማን ሃይለማርያም አበበ እንደተናገሩት፣ ቀጣይ ከሚሰጠን ግዳጅ አኳያ በዋናነት ፀረ-ሽብር፤ የባህር ላይ ውንብድና፤ የባህር ላይ ደህንነት ወዘተ የመከላከል እንዲሁም በአየርና በውሃ አካል ላይ የታገዘ ተልዕኮ የምንፈፅም በመሆኑ የሚሰጠንን ስልጠና ከምንጊዜም በላይ በእልህና ወኔ እንወጣዋለን ብለዋል፡፡ (የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
በጊዜ ዝግጅት ማድረግ እጅግ ወሳኝ ነው። ዓለማችን ውስብስብና ግራ መጋባት ውስጥ በገባች ቁጥር የደህንነት፣የፀጥታ፣የባሕር፣የየብስና የአየር ሃይልን ማጠናከር ወሳኝ ነው።
Good News for young people.