በተወሰደበት እርምጃ የጁንታው አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳ ታጣቂ ኃይሉን ብቻ ሳይሆን የመዋጊያ ንብረቶቹንም ጭምር በየቦታው ማዝረክረኩን የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር አስታወቀ፡፡ የደቡብ ዕዝ 21ኛ ጉና ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት፣ የማይሰበር እልህና ወኔ ሰንቀው ጁንታው በዕብሪት ተወጥሮ በሀገራችን የጀመረውን ጦርነት በማክሸፍ የሀገራችንን ሉአላዊነት በማስከበር የህግ የበላይነትን እንዲረጋገጥ እያደረጉ እንደሚገኙ የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር ህብረት ዘመቻ ቡድን መሪ ሌ/ኮ ብርሃኑ ኃይሉ ተናግረዋል። ሌ/ኮ ብርሃኑ ኃይሉ ሰሞኑን በተደረገው በፈታኝ መሰናክል የታጀበ የአሰሳ ውጊያ ፣ የአካባቢውን አስቸጋሪ ተራራና አቀበት በመጋፈጥ ጠላትን ማፅዳት መቻሉን አረጋግጠዋል፡፡ በተለይም የጁንታው አፈቀላጤ የሆነው አቶ ጌታቸው ረዳ ሲፈረጥጥ አንጠባጥቧቸውና ደብቋቸው የነበሩትን ወታደራዊ ንብረቶች … [Read more...] about መከላከያ ያገኘው የአሸባሪው ህወሃት ኮትተ
EDF
የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ
በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም አቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡ የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ሁከት፣ ሽብርና ትርምስ በመፍጠር ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለማሳካት በሚንቀሳቀሱ የውጭ እና የውስጥ ፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚደገፉ የሸብርተኞቹ የህወሓትና የሸኔ ቡድን አባላት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ሴራ ወጥነው ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳሉ በጋራ ግብረ ኃይሉ በተደረገባቸው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል። ይህን እኩይ የጥፋት ሴራ ለመፈጸም ከውጭ በተለያዩ አካላት በሚደረግላቸው … [Read more...] about የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ
“የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ
ጠቅላይ ኤታ ማጆር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ከባላገሩ ቲቪ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። ስለ ትልውድና አስተዳደጋቸው፣ ቀድሞው ሠራዊት በህወሓት/ትህነግ “ጨፍጫፊ” ስለመባሉ፣ በህወሓት ላይ የተወሰደው ዘመቻና ውጤቱ፣ ስለተያዙት የትህነግ ሹሞች፣ ወዘተ ሰፋ ያለ መግለጫ ሰጥተዋል። ዘመቻው በድል የተጠናቀቀው በሁለት ሳምንት መሆኑን የጠቆሙት ጄኔራሉ የወንበዴዎቹ ለቀማ ብቻ ተጨማሪ ጊዜ የወሰደ መሆኑን ጠቁመዋል። “እኛ የመግደል ሱስ የለብንም” ያሉት ኤታማጆር ሹሙ አብዛኛዎቹ የትህነግ አመራሮች እጃቸውን እንደሰጡ የቀሩትም እንዲሰጡ አሁንም ጥያቄ እናቀርባለን። ካልሆነ ግን የገቡበት ገብተን አንድም ሰው ሳናስቀር ለሕግ እናቀርባቸዋለን - በተለም አመራሩን ብለዋል። ትህነግ አደርገዋለሁ ስለሚለው ቀጣይ የሽምቅ ውጊያ ሲናገሩ፤ “ይሄ ሽምቅ እናደርጋለን ምናምን የሚሉት ጠቅላላ … [Read more...] about “የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ