
በተወሰደበት እርምጃ የጁንታው አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳ ታጣቂ ኃይሉን ብቻ ሳይሆን የመዋጊያ ንብረቶቹንም ጭምር በየቦታው ማዝረክረኩን የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር አስታወቀ፡፡
የደቡብ ዕዝ 21ኛ ጉና ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት፣ የማይሰበር እልህና ወኔ ሰንቀው ጁንታው በዕብሪት ተወጥሮ በሀገራችን የጀመረውን ጦርነት በማክሸፍ የሀገራችንን ሉአላዊነት በማስከበር የህግ የበላይነትን እንዲረጋገጥ እያደረጉ እንደሚገኙ የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር ህብረት ዘመቻ ቡድን መሪ ሌ/ኮ ብርሃኑ ኃይሉ ተናግረዋል።

ሰሞኑን በተደረገው በፈታኝ መሰናክል የታጀበ የአሰሳ ውጊያ ፣ የአካባቢውን አስቸጋሪ ተራራና አቀበት በመጋፈጥ ጠላትን ማፅዳት መቻሉን አረጋግጠዋል፡፡ በተለይም የጁንታው አፈቀላጤ የሆነው አቶ ጌታቸው ረዳ ሲፈረጥጥ አንጠባጥቧቸውና ደብቋቸው የነበሩትን ወታደራዊ ንብረቶች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገልፀዋል።
ከተያዙት ወታደራዊ ንብረቶች ውስጥ፣ ከዘጠኝ በላይ የመገናኛ ሬዲዮኖች፣ አስራ ሦስት ካርቶን ባትሪ፣ መጠናቸው የተለያዩ ሁለት ጀነሬተሮች፣ አስራ ሁለት ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከሦስት መቶ ጥይትና ከአስር የጥይት ካዝና ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን አረጋግጠዋል፡፡
ዘመቻ መኮንኑ፣ ሽብርተኛው በተለያዩ ቦታዎች የደበቃቸው ከ280 በላይ ኩንታል ጤፍ፣ ከ 20 ኩንታል በላይ የፊኖ ዱቄት፣ 120 ብርድ ልብስ፣ 50 አንሶላን ጨምሮ የተለያዩ ንብረቶች ተይዘዋል፡፡
ሽብርተኛው ጁንታ በየጊዜው ለጥፋት የሚመለምላቸው ወጣቶችና ሞቶ የተቀበረውን ጁንታ ተመልሶ ይመጣል በሚል ቀቢፀ-ተስፋ የተጠለፉ ሠልጣኝ ምልምሎቹ የሚለብሱት አምስት ከረጢት በላይ አልባሳትና ልዩ ልዩ መገልገያ ቁሳቁሶቹንም በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ነናግረዋል፡፡
የጁንታው ታጣቂ ሃይል ከሲቪል ተቋማትና ግለሰቦች ዘርፏቸው የነበሩ ጤፍ የጫኑ ሁለት የጭነት ተሽከርካሪዎችን አውድመው መሰወራቸውንም ሌ/ኮ ብርሃኑ ኃይሉ ጨምረው ገልፀዋል።
የጁንታው አፈ ቀላጤ ሰራዊቱ አይገባበትም ብሎ ከተማመነበት ሸጥ ድረስ እግር በእግር ተከታትሎ በመዝለቅ፣ ለፍርድ ያልቀረቡትን ተፈላጊዎች በከፍተኛ እልህ፣ ወኔና ጀግንነት በማደን ላይ እንደሚገኙ የገለፁት ሌ/ኮ ብርሃኑ፣ የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር የሰራዊት አባላት የተሰጣቸውን ተልዕኮ ሁሌም ቀን ከሌት በከፍተኛ ሞራል፣ ዲሲፕሊንና ወታደራዊ ጨዋነት በመፈፀም የላቀ የማድረግ አቅም እንዳላቸው አረጋግጠዋል።
ብርሃኑ ወርቁ (ከግዳጅ ቀጣና)
ፎቶግራፍ አብርሃም ሸዋቀና (መከላከያ ፌስቡክ)
Leave a Reply