ጠቅላይ ኤታ ማጆር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ከባላገሩ ቲቪ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። ስለ ትልውድና አስተዳደጋቸው፣ ቀድሞው ሠራዊት በህወሓት/ትህነግ “ጨፍጫፊ” ስለመባሉ፣ በህወሓት ላይ የተወሰደው ዘመቻና ውጤቱ፣ ስለተያዙት የትህነግ ሹሞች፣ ወዘተ ሰፋ ያለ መግለጫ ሰጥተዋል። ዘመቻው በድል የተጠናቀቀው በሁለት ሳምንት መሆኑን የጠቆሙት ጄኔራሉ የወንበዴዎቹ ለቀማ ብቻ ተጨማሪ ጊዜ የወሰደ መሆኑን ጠቁመዋል። “እኛ የመግደል ሱስ የለብንም” ያሉት ኤታማጆር ሹሙ አብዛኛዎቹ የትህነግ አመራሮች እጃቸውን እንደሰጡ የቀሩትም እንዲሰጡ አሁንም ጥያቄ እናቀርባለን። ካልሆነ ግን የገቡበት ገብተን አንድም ሰው ሳናስቀር ለሕግ እናቀርባቸዋለን - በተለም አመራሩን ብለዋል። ትህነግ አደርገዋለሁ ስለሚለው ቀጣይ የሽምቅ ውጊያ ሲናገሩ፤ “ይሄ ሽምቅ እናደርጋለን ምናምን የሚሉት ጠቅላላ … [Read more...] about “የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ