• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የገቡበት ገብተን አንድ ሰው አናስቀርም – በተለይ አመራሩን” ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ

February 15, 2021 11:46 pm by Editor 1 Comment

ጠቅላይ ኤታ ማጆር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ከባላገሩ ቲቪ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። ስለ ትልውድና አስተዳደጋቸው፣ ቀድሞው ሠራዊት በህወሓት/ትህነግ “ጨፍጫፊ” ስለመባሉ፣ በህወሓት ላይ የተወሰደው ዘመቻና ውጤቱ፣ ስለተያዙት የትህነግ ሹሞች፣ ወዘተ ሰፋ ያለ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዘመቻው በድል የተጠናቀቀው በሁለት ሳምንት መሆኑን የጠቆሙት ጄኔራሉ የወንበዴዎቹ ለቀማ ብቻ ተጨማሪ ጊዜ የወሰደ መሆኑን ጠቁመዋል። “እኛ የመግደል ሱስ የለብንም” ያሉት ኤታማጆር ሹሙ አብዛኛዎቹ የትህነግ አመራሮች እጃቸውን እንደሰጡ የቀሩትም እንዲሰጡ አሁንም ጥያቄ እናቀርባለን። ካልሆነ ግን የገቡበት ገብተን አንድም ሰው ሳናስቀር ለሕግ እናቀርባቸዋለን – በተለም አመራሩን ብለዋል።

ትህነግ አደርገዋለሁ ስለሚለው ቀጣይ የሽምቅ ውጊያ ሲናገሩ፤ “ይሄ ሽምቅ እናደርጋለን ምናምን የሚሉት ጠቅላላ ከሪያሊቲ (እውነታው) ውጪ ስለሆነ አይሠራም፤ የዱሮ ሸማቂና የአሁኑ አንድ አይደለም” ብለዋል።

በሁለት ክፍል የቀረበው ቃለ ምልልስ ከዚህ በታች ይገኛል፤

ክፍል አንድ

ክፍል ሁለት

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Interviews, Middle Column, News, Slider Tagged With: berhanu julla, EDF, operation dismantle tplf, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    February 16, 2021 12:23 pm at 12:23 pm

    እውቁ ደራሲ ብርሃኑ ዘሪሁን በቀደምት ስራዎቹ እንዲህ ብሎን ነበር። ” ሰው በሁለት እግሩ ቆሞ የሚሄድ አውሬ ነው”። ትክክልና ሚዛን መድፋቱን የሚረዳው አፈር በግፈኞች የተመለሰበት ሳይሆን ዛሬም ከነጠባሳው የቆመው ያ ፍጥር ነው። አዎን ስለ ወያኔ ሲነሳ ገና ከጅምሩ ግፈኞች እንደሆኑ ብዙ ተብሏል። የሃገር መሪ ከሆኑ በህዋላ ያደረሱትን ግፍ ለመጻፍ ወረቀት አይበቃም። ያ ሁሉ ግፍ እየዘነበ ቡራ ከራዪ በማለት አብሮ ለዘመናት ከጎናቸው ሆኖ በጥበቃ ላይ የተሰማራውን የሰሜን እዝ ከውጭና ከውስጥ ማጥቃታቸው እብደታቸው ጣራ መውጣቱን ፍጻሜአቸው ያሳያል። እኔ ከውጭ አዋቂዎች ከሰማሁት ከ 10 እስከ 15 ሺህ የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ ሴራ መግደላቸውን ነው። ያው የግጭት ቀዳሚ ሟች እውነት በመሆኗ ይህ ቁጥር እንዳለ የሚሰለቀጥ መሆን የለበትም። ደግሞም ይህ ምንጭ ሲያስረዳ እንዲህ ይለናል። እውነት ነው በሰው ላይ መኪና ነድተዋል፤ እውነት ነው ሰው የሚቀበርበት መሬት ምሰዋል፤ እውነት ነው የሴቶችን ጡት ቆርጠዋል (አኖሌን ያቆመ መንግሥት)፤ እውነት ነው ይህ አማራ ይመስላል በማለት ከሰራዊቱ ውስጥ ለይተው የረሽኗቸው እንዳሉ አረጋግጫለሁ ይለናል። ታዲያ በየቀኑ ደመሰስናቸው የሚለው የዶ/ር አብይ መንግስት ለምን ይህን በደል በፊልምና በመረጃ (ተራፊዎችን ቃለ መጠይቅ በማድረግ) ለዓለም ህዝብ ክፋታቸውን አጉልቶ ማሳየት እንደተሳነው ሊገባኝ አይችልም። ጡታቸው የተቆረጡ በህይወት ያሉ የሰራዊቱም ሆነ የሲቪል አባላት ለምን በግልጽ ቀርበው ማስረዳት አልቻሉም? መረጃ በየገደሉ ከመታኮስ ይበልጣል። በእውነት ላይ የተመሰረተ መረጃ ቁጭትና መነሳሳትን በህዝባችን ላይ ይጭራል። ዝም ብሎ ተባራሪ ወሬ ማውራት ከጥቅሙ ጎጂነቱ ያመዝናል። ወያኔን ሳያሰልስ የሚዋጋው የጦር ሰራዊቱ ሳይሆን የትግራይ ህዝብ እውነትን ሲታጠቅ ነው። በህዝብ ያልታቀፈና ያልተደገፈ ሰራዊት ብቻውን ነገሮችን ማሳካት አይችልም። ይህን ስል የትግራይ ህዝብ ሁሉም ባይሆን ይበልጡ የሰሜን ሰራዊትን አይደግፍም ማለቴ አይደለም። ይደግፋል። ይጠቁማል፡ ይመራል፡ ድጋፉ አያብራም። ራሱ በመረጠው ሲመራና በሌላው የሃገሪቱ ክፍል እንደ ልብ ተዘዋውሮ መስራት ሲመቻችለት ስለ ወያኔ ምንም ትዝታ አይኖረውም። ይህ ግን ራሱ የትግራይ ህዝብ አድጎና ተመንድጎ በሃሳብ ልቀት የሚያመነጨው እውነት መሆን አለበት እንጂ ኑና ልጋታችሁ ተበሎ የሚፈጸም ተግባር አይደለም። እንዲያ ከሆነ ከወያኔ አመራር የቱ ላይ ተለየና!
    ጄ/ብርሃኑ እውነት ነው በተለይ መሪዎቹን የገቡበት ገብተን ለፍርድ እናቀርባቸዋለን ማለታቸው። ግን በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰሳ ካልተደረገ ክምር ውስጥ እንዳለ መርፌ ተፈላጊዎቹ የቱ ጋ እንደሆኑ ማወቅ አይቻልም። የአሜሪካው የስለላ መረብ ኦሳማን ለመያዝ የተጠቀመበት ስልት የተላላኪውን ስልክ ድካ መከተል ነበር። ዛሬ በትግራይ በረሃ ምግብ የሚያቀብላቸው፤ የሚጠቀሙበት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች (ሞቫይልና ሳተላይት ቀመስ ስልኮች) እንዴት መጥለፍ እንደሚቻል ጠበብቶች ያውቃሉ። ምንም ይሁን ምንም በኤሌትሮኒክስ አለም ላይ 100% ዝግ የሆነ ነገር የለም። በዚህ ረገድ የእስራኤሉ የስለላ መረብ ተክኖበታል። መሬት ውስጥ ሰው መደበቁን ሁሉ ማወቂያ ስልት አላቸው። መማር፤ መጠየቅ ነው። ዙ 23 ታጥቆ አሁን የተሰሩ የጦር አውሮፕላኖችን መትቼ እጥላለሁ ማለት መቀለድ ነው። ከ 45 ዓመት በፊት የተሰራ መሳሪያ ለዛሬው የሰማይ ላይ ግር ግር ማስደንገጫ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ማድረግ አይችልም። ይህን ስል ወያኔ ጀት ያበራል ሳይሆን ሱዳንና ግብጽ የሚሰሩትን ሴራ ጠንቅቄ ስለማውቅ ነው። ግብጽ የህዳሴን ግድብ ከመታች የእኛ አየር ሃይል የአስዋንን ግድብ ለመምታት ልምምድ ማድረግ አለበት። እዚህም እሳት አለና። የሱዳን ግርግር የተልኮ ስለሆነ ጥቂት ቂጣቸውን ከተመቱ እንኳን የግብጽ እርዳታ የሌላ ሃያል መንግስትም እርዳታ አይጠቅማቸውም። እናስብ ከግብጽ ጋር እኮ ከ3 ዓመት በፊት በድንበር ተፋጠው መሳሪያ እስከማሰለፍ ደርሰው ነበር። የአሁን የሱዳና የግብጽ ቂጥ መግጠም ከልብ አይደለም። ቢዚህ ላይ ቱርክና ግብጽ በሊቢያ ጉዳይና በሌሎችም ዓይን ለአይን አይተያዪም። ይህ እንግዲህ ግብጽ ዳቦ ያረረባት ሃገር መሆኗን ሳይጨምር ነው። ስለሆነም ጄ/ብርሃኑ መጀመሪያ እነ ጌታቸው አሰፋንና ለፍላፊው ሌላው ጌታቸው ረዳ እንዲሁም ደብረጽዪንን ባሉበት መግደል ወይም ይዞ ለፍርድ ማቅረብ እስካልተቻለ ድረስ የዲጂታል ወያኔ የውጭ ጥሩንባ ነፊዎች በተፈናጣሪ ወሬ ሰውን ማማታቱን አያቋርጡም። ሌት ተቀን ተፈልገው፤ ትራፊ የወያኔ ተጋዳላይ ነን የሚሉም እንዲሁ ተለቅመው መያዝ ወይም መደምሰስ አለባቸው። እኔ እንደሚመስለኝ እነ ጌታቸው መቀሌ እንጂ ገደል ውስጥ አይደሉም። የግልባጭ ሳይኮሎጂ እየተጫወቱ ነው። እነርሱ የተወሸቁት ከተማ ውስጥ ነው። ስለላ፤ አሰሳው ከራስ እስከ እግር ጥፍር እስካልሆነ ድረስ እነዚህን የምድር እባቦች መያዝ አይቻልም። በወታደሩ ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩና በጡረታ ላይ ሆነው የወያኔን ሴራ ተቀላቅለው ሰራዊቱን ያጠቁ ሱዳን/ግብጽ/አሜሪካ/ሌላም ቦታ ቢሆን መረጃ ካለ አስሮ መላክ ይቻላል። ዋናው መረጃ ማሰባሰብ አስፈላጊ ነው። ከሰሞኑ የኢትዪጵያ መንግስት ላቪ የሚያረግ ቀጠረ ቢሉኝ በጣም ነው ያሳቀኝ። የኢትዪጵያ መንግስት ድጋፍ መረጃ ነው። ይህ መረጃ በውጭና በውስጥ ጋዜጠኞች፤ ለሰው ልጆች መብት በሚከራከሩ፤ በቀይ መስቀል፤ በሌሎችም የግልና የመንግስት ተራዶ ድርጅቶች ለአለም ህዝብ እውነቱ እንዲደርስ ማድረጉ ለላቪ ከመክፈል ያድናል። በመጨረሻም ወያኔ ሞተ፤ ተቀበረ፤ አበቃ ለምትሉ እኔ ጭራሽ አይሞቱም ባይ ነኝ። በተንኮል ብቻ የተበረዘ ጭንቅላት ስላላቸው ድልድይ ማፍረስ፤ የሃይል ማመንጫ መቁረጥ፤ ገደል ለገደል እየተሮጠ ነጻ አውጪ ነኝ ማለት እንደ ጀግንነት የሚቆጠር በመሆኑ በትራፊዎቹ የጥፋት ስራውን ይቀጥላል። ስለሆነም ሌት ተቀን ነቅቶ ጠላት ጥፋት ከማድረሱ በፊት ሁሉን አዳምጦና አላምጦ ማክሸፍ እያመነመናቸውና ክራርና ከበሮአቸውን አስትቶ ወደ እርሻ ሊያስገባቸው ይችል ይሆናል። ሰርቶ መኖር አያውቁምና እንደገና ሀ ብለው ኑሮን ይጀምሩታል። ለነገሩ አንድ እግራቸው መቃብር ላይ አይደል የቆመው የመማሪያ ጊዜም የላቸው። እንዲህ ነው የሮም አወዳደቅ። እንዘጭ እንጂ ብድግ የማይሉበት። አይ እብደት። ሰው እንዲህ ይቀላል፡፤ አታድርስ። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule