የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በህቡዕ ሲሰራ የቆየ ቡድን ከእነ ግብረአበሮቹ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ። የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት በላከው መግለጫ÷ በቢሾፍቱና በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ከሚከበረው የኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃቶች ለመፈጸም፣ አመጽ ለማቀጣጠል፣ ግጭትና ትርምስ ለመፍጠር ከጥቂት የህወሓት የጥፋት ቡድኖች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ተልዕኮ ተቀብሎ በህቡዕ ሲያስተባብርና ሲመራ የነበረ የኦነግ ሸኔ ቡድን ከእነ ግብረአበሮቹ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ማድረጉን አስታውቋል። አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙሃን ባሰራጨው መረጃ እንደገለጸው÷ ከኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱና በሌሎቹም የአገሪቱ አካባቢዎች በጦር መሳሪያ የተደገፈ … [Read more...] about መቀሌ ተሸርቦ አዲስ አበባና ደብረዘይት ሊተገበር የነበረው ሽብር ከሸፈ
NISS
“ጄኔራል” አደም መሐመድ፤ ከሬዲዮ ኦፕሬተርነት እስከ መረጃና ደኅንነት ዳይሬክተርነት
ወሎ-አምባሰል የተወለደው አደም መሐመድ በ1975 ዓ.ም ኢህዴንን የተቀላቀለ ነባር ታጋይ ነው። በትጥቅ ትግሉ ወቅት በዋናነት የአዲሱ ለገሰ ሬዲዮ ኦፕሬተር ሆኖ ሰርቷል። አንዳንዶች በሰውየው ላይ ሲቀልዱ “የአዲሱ ለገሰ ሻሂ አፍይ” ይሉት ነበር። አደም መሐመድ ለአዲሱ ለገሰ ለአምልኮ የቀረበ ፍቅር ያለው በመሆኑ በሬዲዮ የሚተላለፉ መልዕክቶችን በጽሁፍ ከመገልበጥና መረጃዎችን ከማድረስ ባሻገር ለሰውየው ማሸርገድ ይወድ ነበር የሚሉት የእርሱ ዘመን ጓዶች፣ አድርባይነቱን ያለ ልዩነት ይስማሙበታል። ከኢህአዴግ ምስረታ በኋላ በነበሩ አውደ ውጊያዎች በ“ዘመቻ ዋለልኝ” እና “ኢህአዴግ ፋና” በተሰኙ ዘመቻዎች ላይ ተሳትፏል። በትጥቅ ትግሉ ወቅት እንደ ድርጅት “መስመር ማጥራት” በሚል በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዱ ሴሚናሮች፣ ኮንፍረንሶች እና በሁለቱም ድርጅታዊ ጉባዔዎች (1976 እና 1981ዓ.ም) … [Read more...] about “ጄኔራል” አደም መሐመድ፤ ከሬዲዮ ኦፕሬተርነት እስከ መረጃና ደኅንነት ዳይሬክተርነት
የህወሃት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ እየተበረበረ ነው
“አዲሱ ቴሌ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ/ኢንሳ” በሚል ርዕስ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ያዘጋጀው ጥናታዊ ሪፖርት የታላላቅ አገር የስለላ ተቋማት፣ ለጉዳዩ አግባብ ያላቸው መምሪያዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ትኩረት መሳቡ ታወቀ። ሪፖርቱን አገራቱ በራሳቸው ቋንቋ በመተርጎም የህወሃት/ኢህአዴግን የስለላ መረብ ከተለያየ አቅጣጫ እየመረመሩት ነው። የጎልጉል ምንጭ የሆኑ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንዳስታወቁት አኢጋን የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አዲሱ ቴሌን (ኢትዮ ቴሌኮምን) ከዋንኛው የስለላ መ/ቤት ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል NISS (National Intelligence and Security Service) እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ወይም በእንግሊዝኛው … [Read more...] about የህወሃት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ እየተበረበረ ነው