• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መቀሌ ተሸርቦ አዲስ አበባና ደብረዘይት ሊተገበር የነበረው ሽብር ከሸፈ

October 2, 2020 12:35 pm by Editor 2 Comments

የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በህቡዕ ሲሰራ የቆየ ቡድን ከእነ ግብረአበሮቹ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት በላከው መግለጫ÷ በቢሾፍቱና በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ከሚከበረው የኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃቶች ለመፈጸም፣ አመጽ ለማቀጣጠል፣ ግጭትና ትርምስ ለመፍጠር ከጥቂት የህወሓት የጥፋት ቡድኖች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ተልዕኮ ተቀብሎ በህቡዕ ሲያስተባብርና ሲመራ የነበረ የኦነግ ሸኔ ቡድን ከእነ ግብረአበሮቹ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ማድረጉን አስታውቋል።

አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙሃን ባሰራጨው መረጃ እንደገለጸው÷ ከኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱና በሌሎቹም የአገሪቱ አካባቢዎች በጦር መሳሪያ የተደገፈ የሽብር ጥቃት፣ አመጽ፣ ግጭትና ትርምስ ለመፍጠር ተልዕኮ ለተሰጠው በህቡዕ የተደራጀ አንድ ታጣቂ ቡድን የሚውል 10 ክላሺንኮቭ የጦር መሳሪያ ከ 280 ጥይቶች ጋር ከመቀሌ ወደ ባቲ ሲጓዝ መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም ቀን በደቡብ ወሎ ዞን ሃይቅ ከተማ ከእነ ተሽከርካሪው በቁጥጥር ሥር ውሏል።

በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ህዝባዊ አመጽ እንዲነሳ በማድረግ ይህን እንቅስቃሴ ለማሳካት ከተመለመሉት መካከል አንዱ የሆነው እንድሪስ እያሱ መሃመድ የተባለ የኦነግ ሸኔ አባል ከትግራይ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊና ከሌሎች ጥቂት የህወሓት የጥፋት ቡድኖች ጋር በህቡዕ ተልዕኮውን ሲያቀናጁ እንደነበር የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል ማረጋገጡን አመልክቷል።

እነዚህ የጥፋት ቡድኖች በመጪው ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባና የኦሮሚያ ክልሎች የሚከበሩትን የኢሬቻ በዓልን ተገን በማድረግ በኦሮሚያ ክልል አመፅ እንዲቀጣጠልና ወደ ሌሎች ክአካባቢዎች እንዲዛመት በጦር መሳሪያ ጭምር የታገዘ ትርምስ ለመፍጠር ከመቀሌ ወደ መሃል አገር የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን ሲልኩ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

ለዚህ እኩይ ተግባራቸውም ግለሰቦችን መልምለው ወደ መቀሌ በመውሰድ አሰልጥነው ወደተለያዩ አካባቢዎች ይልኩ እንደነበር የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።

ለዚህ ተልዕኮው እንዲረዳቸው ካደራጇቸው የህቡዕ ቡድኖች መካካልም አንዱ እንድሪስ እያሱ መሃመድ በተባለ የኦነግ ሸኔ አባል የሚመራ ሲሆን÷ ላለፉት ወራት ከከሚሴ፣ መቀሌ አዲስ አበባ በመመላለስ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማስፈጸም ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡

ቡድኑ መስከረም 16 ቀን 2013 ዓም በደቡብ ወሎ ዞን ሃይቅ ከተማ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ገልጿል።

የጥፋት ቡድን መሪው መቀሌ ከሚገኘው የትግራይ ክልል የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ከሆነው ተኪኡ ምትኩና ሌሎች ጥቂት የህወሓት የጥፋት ቡድኖች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት በመፍጠር ወደ መቀሌ በመመላለስ የጦር መሳሪያ፣ ገንዘብና ተልዕኮ በመቀበል ከሸኔ ታጣቂ ቡድን ጋር በማስተሳሰር በኦሮሚያ የአመጽ ቡድን ሲያደራጅ ቆይቷል።

ከዚህም በተጨማሪ እንድሪስ እያሱ መሃመድ እና ግብረአበሮቹ ከመቀሌ በተሰጣቸው ተልዕኮ መሠረት በባቲ የህቡዕ ቡድን አበላትን በማደራጀት በአካባቢው የብሄር ግጭቶችን የማስፋፋት እንዲሁም በሌሎችም ስፍራዎች ግጭት የመቀስቀስ ተልዕኮ ተቀብለው ሲያስፈጽሙ ቆይተዋል።

አማርኛ፤ ኦሮሞኛ፤ ሱማሊኛ፤ አፋርኛና አረብኛ በድምሩ አምስት ቋንቋዎችን የሚናገረው የሽብር ቡድኑ መሪና አስተባባሪ ተጠርጣሪው እንድሪስ እያሱ መሃመድና ግብረ አበሮቹን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው እንቅስቃሴ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በጥብቅ ሙያዊ ዲስፕሊን የመከታተልና መረጃ የመስጠት ስራዎችን ሲሰራ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንና የኢፌዴሪ መካላከያ ሰራዊት በጋራ መስራታቸውን መግለጫው አመልክቷል፡፡

መቀሌ ተሸርቦ ደቡብ ወሎ ዞን ሀይቅ ከተማ ላይ የከሸፈው የሽበር ጥቃት መሳሪያዎችን በከረዩና በባቲ በኩል ወደ ቢሾፍቱና አዲስ አበባ በማስገባት ከፍተኛ ሁከትና ግርግር በመፍጠር አገርን ለማተራመስ እቅድ እንደነበረው የጠቆመው መግለጫው÷ ሴራውን በማክሸፍ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጉንም አገልግሎት መስሪያ ቤቱ መግለፅ ይወዳል፡፡

በቀጣይም በአገራችንና በህዝባችን ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ የሚቃጡ ማናቸውንም የሽብር ጥቃቶች አስቀድሞ በማወቅ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እያረጋገጠ የህብረተሰቡ ትብብርና ድጋፍም እንዳይለየውም ጥሪ ማቅረቡን ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News, Politics Tagged With: NISS, terrorism, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. ዳን says

    October 4, 2020 03:32 am at 3:32 am

    ይገርማል።

    Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    October 22, 2020 11:52 am at 11:52 am

    ደብረ ዘይት? ደብረ ዘይት? ማን ኣወጣላት ይህን ስም?
    ሃይሌ ቀጭኑ? ነው? ነው እንጂ! ላይጣጣም
    ከቋንቋችን ከምስላችን፥ ካምልኮኣችን ላይሳሳም
    ላይሰልጥ፥ ላይሆን ድርጭት ፍለጋ፥ እንደላም
    ግብራችን፥ ትንፋሻችን ላይጥም ትምክህትም
    ድርቅ እንደመታው ማሽላ ፍግምግም
    ብሎም ጠውልጎ እሸት ላይኖረው ምርትም
    ደብረዘይት ኣልከኝ? እልህ ኣንገባም!!
    የበላኸውን ኣጣጥም!!
    የሃይሌ ቀጭኑ ስም!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am
  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule