
ወሎ-አምባሰል የተወለደው አደም መሐመድ በ1975 ዓ.ም ኢህዴንን የተቀላቀለ ነባር ታጋይ ነው። በትጥቅ ትግሉ ወቅት በዋናነት የአዲሱ ለገሰ ሬዲዮ ኦፕሬተር ሆኖ ሰርቷል። አንዳንዶች በሰውየው ላይ ሲቀልዱ “የአዲሱ ለገሰ ሻሂ አፍይ” ይሉት ነበር። አደም መሐመድ ለአዲሱ ለገሰ ለአምልኮ የቀረበ ፍቅር ያለው በመሆኑ በሬዲዮ የሚተላለፉ መልዕክቶችን በጽሁፍ ከመገልበጥና መረጃዎችን ከማድረስ ባሻገር ለሰውየው ማሸርገድ ይወድ ነበር የሚሉት የእርሱ ዘመን ጓዶች፣ አድርባይነቱን ያለ ልዩነት ይስማሙበታል። ከኢህአዴግ ምስረታ በኋላ በነበሩ አውደ ውጊያዎች በ“ዘመቻ ዋለልኝ” እና “ኢህአዴግ ፋና” በተሰኙ ዘመቻዎች ላይ ተሳትፏል።
በትጥቅ ትግሉ ወቅት እንደ ድርጅት “መስመር ማጥራት” በሚል በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዱ ሴሚናሮች፣ ኮንፍረንሶች እና በሁለቱም ድርጅታዊ ጉባዔዎች (1976 እና 1981ዓ.ም) ላይ ታጋዩ በድርጅታዊ ነፃነትና በህወሓት ጣልቃ ገብነት ዙሪያ ሲከራከርና ሲጨቃጨቅ ድምጹን አጥፍቶ፣ አጨብጭቦ የሚወጣ ሰው ነበር። በተለይም ከኃይልና ከዚያ በላይ ላሉ የግንባርና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት መሽቆጥቆጥ የሚያበዛ ሰው እንደነበር የትግል ጓዶቹ ይመሰክራሉ። ይህ ባህሪው አድጎ የጄኔራልነት ማዕረግ ካገኘ በኋላም በተለያዩ ወታደራዊ ኮንፍረንሶችና ስብሰባዎች ላይ “እከሌ እንዳለው፣ እሱ ከተናገረው ላይ የምጨምረው ነገር ቢኖር፣…” እያለ ሰግዶ የሚኖር ሰው መሆኑን የጎልጉል ምንጮች ይናገራሉ።
በድህረ-ደርግ የሠራዊት አደረጃጀት ወቅት ወደ አየር ኃይል የተመደበው አደም መሐመድ፣ አየር ኃይል ውስጥ ከበረራ እስከ ጥገና፣ ከአየር ወለድ እስከ አየር ላይ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ አሰጣጥ ድረስ የደረሱ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችን ወስዷል። በውል የተመዘገበ የጦር አየር በረራ ቆይታ ባይኖረውም፣ ስንቅና ቁስለኛ አመላላሽ የሆኑ ሂልኮፕተሮችን ያበርር ነበር። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ በሂልኮፕተር ስንቅ አመላላሽ በመሆን እንዳለገለገለ የሚያስታውሱት የቅርብ ጓዶቹ፣ ዛሬ ላይ በህይወት በሌለው የኢህዴን መስራች በነበረው ሜ/ጀኔራል ኃይሌ ጥላሁን አጋዥነት በአየር ኃይል ውስጥ የቀጠና ስምሪት አዛዥ በመሆን ሲሰራ ቆይቷል። በባድመ ጦርነት ወቅት ሻላቃ የነበረው አደም መሐመድ በአስራ ሰባት አመት ውስጥ ሙሉ ጀኔራል ማዕረግ ላይ ደርሷል። በዚህ ጊዜ ሂደት ሰውየው ይህ ነው የሚባል የውጭ አገር ትምህርት አልወሰደም። በርግጥ አሜሪካ ሁለት ጊዜ፣ እስራኤል አንድ ጊዜ ለሥራ ጉብኝት እንደሄደ የሚገልጹት የጎልጉል የመረጃ ምንጮች እነዚህ ጉዞዎች ግን ለጀኔራልነት ማዕረግ ያበቃሉ ማለት እንዳልሆነ አክለው ይገልፃሉ።
ድህረ-ደርግ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ በመሆን በተከታታይ ከሰሩት፡- ሜ/ጀኔራል አበበ ተ/ኃይማኖት፣ ሜ/ጀኔራል ኃይሌ ጥላሁን፣ ሜ/ጀኔራል ዓለምሸት ደግፌ ቀጥሎ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ የሆነው ጀኔራል አደም መሐመድ በስታፉ ውስጥ እንደቀደሙት አዛዦች የሚከበር ሰው አልነበረም።ሰውየው ራሱን ችሎ ውሳኔ ለመስጠት የሚቸገርና የአድርባይነት ዝንባሌ የተጫነው ህወሓት አምላኪ ነው የሚሉት የጎልጉል ምንጮች፣ ውሃ በማይቋጥሩ ምክንያቶች 13 ጄኔራሎች፣ 45 ኮሎኔሎች፣ 250 ሻለቆች፣ ከ41000 በላይ የመስመር መኮንኖችና ተራ ወታደሮች አማራ በመሆናቸው ብቻ ሰበብ እየተፈለገ ከሠራዊቱ ሲሰናበቱ “ለምን?” የሚል ጥያቄ ማንሳት ቀርቶ “የትምክህት ሰለባዎች” እያለ ከነአዲሱ ለገሰ ጋር ሆኖ ሲያንቋርር የኖረ አድርባይ ሰው ለመሆኑ አስረጅ ምሳሌ አድርገው ያቀርቡታል።
በጥር 2010ዓ.ም ወልድያ ከተማ በጥምቀት በዓል ላይ በታቦታቱ ፊት በአጋዚ ወታደሮች በርካታ ምዕመናን መረሸናቸው የሚታወስ ነው። ይህንን መንግሥታዊ ፍጅት ተከትሎ በተከታዩ ሳምንት በቆቦ ከተማ በተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ ያለ አየር ኃይሉ ዋና አዛዥ (“ጀኔራል” አደም መሐመድ) ዕውቅናና ፍቃድ የሰሜን ዕዝ የአየር ኃይል ቤዝ በከተማው ላይ መትረየስ የጫነ ሂሊኮፕተር አሰማርቶ ህዝብ ሲያሸብር የዋለበት ሁነት ስለሰውየው የአመራር አቅምና ተደማጭነት መጠን የሚናገረው እንዳለ ብዙዎች የሚስማሙበት ነው።

በሚያዚያ 2001ዓ.ም “የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አድርጋችኋል” በሚል ከታሰሩት የኢህዴን/ብአዴን ነባር ታጋዮች ውስጥ አንድ ቤት አብረው ያደጉት፣ በ1975 ዓ.ም ወደትግል አብረው የወጡት የእህቱ ልጅ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሓባ ዘጠኝ ዓመት በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ሲማቅቅ አንድ ቀን እንኳ ማረሚያ ቤቱ መጥቶ ያልጠየቀው መሆኑ፣ ስለሰውየው አድርባይነትና ፍርሃት የሚነገርን ብዙ ነገር አለ የሚሉት የቀድሞ ጓዶቹ “ሰውየው ራሱን ችሎ መቆም የማይችል የአዲሱ ለገሠ የእጅ ሥራ ውጤት ነው” ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።
ህወሓትን እንደ ብቸኛ ነፃ አውጪ ድርጅት፣ መሪዎቹን ደግሞ እንደ ፈጣሪ የሚያየው አደም መሐመድ፤ይሄ ባህሪው በአንድ ጀንበር የያዘው እንዳልሆነ የቀድሞ ጓዶቹ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። “የአዲሱ ለገሰ የቅርብ አሸርጋጅ ሆኖ ለዓመታት የኖረ ሰው ከመሆኑ ጋር ይያያዛል” የሚሉት የጎልጉል መረጃ ምንጮቻችን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሆኖ እየሠራ እንኳ የሳምንቱን የዕረፍት ቀናት ጠመንጃ ያዥ አካባቢ ባለው የአዲሱ ለገሰ ቤት እንደሚያሳልፍና ምክር ሲቀበል እንደሚውል ይናገራሉ። አዲሱ ለገሰ ከህወሓት ሰዎች በላይ ለህወሓት ድርጅታዊ ህልውና የሚጨነቅ ብአዴንን እንደ አማራ “ጠባይ ማረሚያ” የሚገለገልበትን የድርጅቱን ብአዴንን መነቃቃትና የአማራን ሕዝብ ቀና ብሎ መሄድ የማይወድ ሰው ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የበረሃ ሻይ አፊይው አደም መሐመድ አሁን የያዘውን ቁልፍ ቦታ በእነ አዲሱ ለገሰ “የቅዳሜ ምክር” ለህወሓት ፖለቲካል-ኢኮኖሚ ጥቅም መገልገያ ማስጠበቂያ ከማድረግ ወደ ኋላ የሚል አይመስልም።
“ለራሱ ተገቢ የሆነ ክብር መስጠትና መብቱን ማስጠበቅ አይችልበትም” እየተባለ የሚብጠለጠለው አዲሱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዳይሬክተር አደም መሐመድ፤ ብርጋዴል ጄኔራል እያለ አዲስ አበባ ሳሪስ አካባቢ በተሰጠው አነስተኛ ቪላ ቤት ዛሬም ሙሉ ጀኔራል ሆኖ እዛው ጠባብ ቪላ ቤት ውስጥ እንደሚኖር የመረጃ ምንጮቻችን ዘገባ ያመለክታል። የህወሓት ጄኔራሎች በምን ዓይነት የቅንጦት ህይወት እንደሚኖሩ ልብ ይሏል። በጠባብ ቪላ ቤት ውስጥ ኑሮውን ለመኖር መምረጡ ሰውየውን ራሱን የካደ አብዮተኛ ወታደር አያስብለውም (ላለመሆኑ ብዙ ማሳያዎችን ማቅረብ ይቻላል) የሚሉት የቀድሞ ጓዶቹ “እንደ ጄኔራልነቱ ሊያገኝ የሚገባውን መብቱን የዘነጋ፣ ራሱን በፍርሃት የቀበረ ጄኔራል ብንለው የሚያንስበት እንጅ የሚበዛበት አይደለም” ሲሉ የከረረ አስተያየታቸውን ለጎልጉል ሰጥተዋል።
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ዳይሬክተር ሆኖ ለአስራ ስምንት ዓመታት ሲሰራ ከነበረው ጌታቸው አሰፋ ጋር አዲሱን ተሿሚ ማወዳደር ተገቢ ባይሆንም በራስ የመተማመንና የውሳኔ ሰጪነት አቅማቸው ግን ለንጽጽር የሚቀርብ አይደለም። በመረጃ እገታ እና በአፈና መዋቅሩ ራሱን ስውር ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ከኖረው ጌታቸው አሰፋ በራስ የመተማመን አቅምም ሆነ የመረጃ ትንተና ችሎታ ጋር ማወዳደር ፍርደ ገምድልነት ይሆናል የሚሉት የመረጃ ምንጮቻችን፤ ከመረጃና ደኅንነት ጉዳዮች አኳያ በአገር ውስጥ፣ በቀጠናው፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ላይ ያለውን ፈጣን ለውጥና የመረጃ ልውውጥ በብቃት መምራት የአዲሱ ተሿሚ ቀጣይ የቤት ሥራዎች ይሆናሉ። በተለይም ከዓለምአቀፎቹ የመረጃና ደኅንነት ተቋማት ጋር የሚኖረውን አጋርነት ማስቀጠል የሬዲዮ መልዕክት የመቀበል ያህል ቀላል እንደማይሆን ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ ይናገራሉ።
ከጌታቸው አሰፋ መነሳት በኋላ በደህንነት መስሪያ ቤቱ ውስጥ የአደረጃጀት እና በየዘርፉ ያሉ አመራሮች ለውጦች ሊደረጉ እንደሆነ ለጎልጉል የደረሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። በተለየ መልኩ የአገር ውስጥ ጉዳዮች እና የቀጠናው የመረጃ መረብ ትስስር መጠናከር ትኩረት የተሰጠው በመሆኑ፤ ህወሓት ለረዥም ዓመታት በብቸኝነት ይዞት የቆየ መስሪያ ቤት እንደመሆኑ መጠን ትምህርትና ሥልጠና ከልምድ ጋር ተጣምረው ከሚፈጥሩት የኤጀንትነት ብቃት አኳያም ቢሆን የህወሓት ሰዎች በታኮነት ቦታ የሚያጡ አይመስልም። ከሬዲዮ ኦፕሬተርነት ተነስቶ አድርባይ ባህሪውን ተሞርክዞ የመረጃና ደኅንነት ዳይሬክተር ለመሆን የበቃው “ጀኔራል” አደም መሐመድ ኢትዮጵያን ወይም ሕወሓትን ለመምረጥ ግድ የሚለው ጊዜና ወንበር ላይ ተቀምጧል። እንደቀደመው የሥራ ዘመኑ በአድርባይነት ለጌታቸው አሰፋ የስልክ ጥሪዎች ታዛዥ ሆኖ መቀጠል ወይም ህዝባዊ ውግንና ይዞ የአፓርታይድ አገዛዝ ማስፈጸሚያ ሆኖ የቆየውን መስሪያ ቤት ለታሪክ የሚበቃ ሥር-ነቀል ለውጥ ማምጣት። ምርጫው በእጁ ላይ ነው። (የፊት ፎቶ የተወሰደው ከሪፖርተር ጋዜጣ ነው)
(በቀጣይ ዕትም የጌታቸው አሰፋን ሌጋሲ በተመለከተ ዘገባ እናቀርባለን)
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
Too much talk, time to deliver.
የሰው ልጅ ከክበሩ ወረዶ 2 እግር ያለው እንሥሣ መሆን እንደሚችል ማሳያው የትግሬ ወያኔ የማፊያ ቡድን አንዱ ነው። (ክቡሩ ሰው) የተባለው ፍጡር ሣር የማይበሉ ባለ 2 እግሮች የእንስሳዎቹ ጉሮኖ የሆነው የትግሬ ወያኔ የወንበዴው ቡድን ፤ ደረጃቸው ይለያይ እንደሆን እንጅ ተቋሙ እንዳለ ከሰውነት የወጡ ባለ 2 እግር እንሰሶች መሆናቸው ለአደባባይ ተጋልጧል። ለምሳሌ አያቱ እንግሊዛዊ የሆነው ሰካራሙ ስብሃት ነጋ እጅግ እጅግ የወጣለት አፍሪካዊነቱን የሚጠላ፤ ኢትዮጵያዊነቱ የሚያንገሸግሸው፤ ትግሬነቱ ደግሞ ይበለጥ እከከ የሆነበት ለመሆኑ ለ 1 ቀን ጠጋ ብሎ ከእንስሳው ጋር ለቆዬ ሰው፤ ባለ 2 እግሩ እንስሳ ከእንስሳዎቹ የትኛው ጋ እንደሚመደብ ይቸግር ይሆናል እንጅ በስዉነቱ የሚያፈር፡ የማነነት ቀውስ ያለበት አሳማ መሆኑን ትረዱታላችሁ። ይሄን የማንነት ቀውሱን በገንዝብና በሃብትም እንኳ ሊሸፍነው አልቻለም። ሁልግዜ ይደባደባል። ሚስቱን በስከረ ቁጥር በዱላ እየነረተ በማሰቃየት የሚረካ ወዘተ….ፍጡር ነው። አያድርስ ነው የእርሱማ መላ ቤተሰቦቹ ፀረ፡ ሰው ማለት ናቸው ማለት ይቻላል። ፀረ ሰው መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንግዲህ .ማብራሪያ የሚያስፈልገው አይመስለኝም። በነገራችን ላይ ሚስቱም የጣሊያን ክልስ ናት። አባቱ ደግሞ ትሩንቡሌ እንደነበር፣ ሳይዘነጋ
Bravo Ezira, Tell them the truth. God bless you brother.
ላም ያል ዋለበት ኩበት ለቀማ፡
ስለ ጄኔራሉ እየ ተቦኘቀ፡
Ezira ድግሞ ህወሓት, ትግራዋይ, እንስሳ, ኣቦይ ስብሓት, ምናምን ትላለህ ሙትቻ !!!
ወንዳወንድ የሆነ ሃሳብ ማስቀመጥ ካልቻልክ ዝምታ ክብር ኣለው።
ጀኔራል አደም መሀመድ የተወለደው በደቡብ ወሎ ዞን ወርባቦ ወርዳ ነው፡