
የፌዴራል ፖሊስ ጥብቅ ፍተሻ እያደረገ ያለው ከአማራ ክልል በሚመጡ መንገደኞች ብቻ ሳይሆን ወደ መዲናዋ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ተመሳሳይ የቁጥጥር ስራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በአልን ምክኒያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም እና ይህንኑ ተከትሎ ሁከት እና ግጭት እንዲፈጠር በዝግጅት ላይ የሚገኙ አካላት እንዳሉ ደርሰንበታል ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራሉ መረጃውን መሰረት በማድረግ ወደ አዲስ አበባ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።
የበዓሉን እንቅስቃሴ ለማደፍረስ ዕቅድ ያላቸው ሀይሎች እንዳሉ ፖሊስ በምርመራ እንደደረሰበት ጠቁመው፤ እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቀቆጠቡ አሳስበዋል።
ከመስከረም 25 በኋላ መንግስት አይኖርም በሚል የተለያዩ እንስቃሴዎች የሚያደርጉ አካላት እንዳሉ ገልጸው የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።
በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ መግቢያ በሮች በሱልልታ፣ ለገጣፎ፣ ቡራዩ፣ ገላንና ሰበታ ፍተሻ እየተደረገ እንደሆነም ኮሚሽነር እንዳሻው ጣሰው ተናግረዋል።
አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ገልጸው፤ በበዓሉ ለመታደም የሚመጡ ምዕምናንና እንግዶችም ትክክልኛውን የይለፍ ባጅ ማድርጋቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ተናግረዋል። ይህን ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውንም አካል አይታገስም ፤ ፖሊስ እርምጃ ይወስዳልም ብለዋል።
ፖሊስ ከኅብረተሰብ ጋር በትብብር እየሰራ ነው ያሉት ሀላፊው፤ ህብረተሰቡ ለየት ያለ እንቅስቃሴ ሲመለከት የተለመደ ትብብርንና ጥቆማውን ለፖሊስ እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
under no intention- z-habesha:
ኢትዮጵያ ያለባት ሃላፊነት
1. ለዜጎችዋ
2. ለምድሪቱ የሰው ልጆች በሙሉ
3. በዚሁም መሰረት ኢትዮጵያ ዜግዎችዋ የሚያስፈልጋቸውን በሙሉ ለማሳካት የተቻላትን ጥረት ታደርጋለች:: ግብፅ የአባይን ውሃ ሸጣ ገቢ ከማግኘቷ በፊት ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ተራራዎች ላይ ዘንቦ በኢትዮጵያ ወንዞች ውስጥ የሚፈሰውን ውሃና አፈርን ለህዝቦችዋ ጥቅም ታውላለች:: የሰው ልጆች እንደመሆናችን መጠን በሌሎች ህዝቦች ላይ ሌሎች ሃያላን ሃገራት በጎረቤቶቻቸው ላይ እንደሚያካሂዱት አይነት የማድረቅ barbaric ተግባራትን በጎረቤት ሃገራት ላይ አናካሂድም:: ስለሆነም እኛ የግብፆች ጉሮሮ እንዲደርቅ ፍላጎታችን ሊሆን አይችልም:: ከዚህን በላይ እነ የግብፅ አሽቀርቃሪዎች የሚመኙትን ስግብግብነት የሟሟላት ግን አንዳችም ግዴታም ሆነ ሃላፊነት የለብንም:: ኢትዮጵያ በዚህ መልኩ አለም አቀፋዊ ሃላፊነቷን ስለምትወጣ ግድቦቻችንንና ውሃ አፈሮቻችንን አስመልክቶ አማላጅ ምንቲሴም አስፈላጊነት የለውም:: ግን ምናልባት የGlobal አዲስ ሁናቴ ተፈጥሮ አሜሪካና ሜክሲኮ ከአሜሪካ ወደ ሜክሲኮ በሚወርዱት ወንዞችን አስመልክቶ በአማላጅ ጣልቃ ገብነት ከተደራደሩ፣ እኛም የአዲሱ የድርድር ህጎች ተገዢዎች ልንሆን ነው ማለት ነው፣ እስከዚያን ጊዜ ድረስ ነጋ ጠባ መደነቛቆሩ ቢቆም ይመረጣል::
4. ለኢትዮጵያውያን በሙሉ፣ unity in diversity፣ ዋናው የመከላከያ ሃይል አንድነት ነውና!
the manipulation form of z-habesha
sagt:
26. September 2020 um 5:50 Uhr
ሃላፊነት ያለባት ሃላፊነት
1. ለዜጎችዋ
2. ለምድሪቱ የሰው ልጆች በሙሉ
3. በዚሁም መሰረት ኢትዮጵያ ዜግዎችዋ የሚያስፈልጋቸውን በሙሉ ለማሳካት ታደርጋለች :: :: ልጆች እንደመሆናችን መጠን በሌሎች ህዝቦች ላይ ሌሎች ሃያላን ሃገራት በጎረቤቶቻቸው ላይ እንደሚያካሂዱት bar barbarisch ተግባራትን በጎረቤት ሃገራት አናካሂድም :: ስለሆነም እኛ የግብፆች ጉሮሮ እንዲደርቅ አይችልም አይችልም :: ከዚህን በላይ እነ የግብፅ አሽቀርቃሪዎች የሚመኙትን ስግብግብነት የሟሟላት ግን አንዳችም ግዴታም የለብንም የለብንም :: የለብንም የለብንም የ አለም አቀፋዊ ሃላፊነቷን ስለምትወጣ ግድቦቻችንንና ውሃ አፈሮቻችንን አስመልክቶ አማላጅ የለውም የለውም :: ግን የ የ Global አዲስ ሁናቴ ተፈጥሮ አሜሪካና ሜክሲኮ ከአሜሪካ የ በሚወርዱት በሚወርዱት አስመልክቶ በአማላጅ ጣልቃ ገብነት ፣ እኛም እኛም የድርድር ህጎች ተገዢዎች ልንሆን ነው መደነቛቆሩ መደነቛቆሩ ፣ ፣ እስከዚያን ቢቆም ይመረጣል ::
4. ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ፣ Einheit in Vielfalt ፣ ዋናው የመከላከያ ሃይል ሃይል ነውና!