የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክተው ትላንት መግለጫ ሰጥተዋል።
- በአጠቃላይ በ2015 ዓ.ም ከተፈተኑ ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል።
- በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ ለፈተና ከተቀመጡ በድምሩ 845,677 ተማሪዎች 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡት 27, 267 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።
- በዚህም 160 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎችን በሬሜዲያል ፕሮግራም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚቀበሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል።
- የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ትምህርት ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻላቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
- 376 ተፈታኞች በቡድን፤ 483 ተፈታኞች ደግሞ በግል ጥፋት ፈጽመዋል
- ጥፋቶቹም፤
ለሌላ ሰው ለመፈተን መሞከር
የፈተና ወረቀት ቀይሮ ለማስገባት መሞከር
መኮራረጅ
በግልና በቡድን መረበሽ
ያለፈቀዱ ቁሳቁሶች ይዞ መግባት ናቸው። - ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ2014 ዓም 20,170 ተፈታኞች ጥሰት የፈጸሙት ሲሆኑ በ2015 ዓም ግን 859 ተፈታኞች ብቻ ናቸው
- የታየው ለውጥ የሚበረታታ ነው (95% ነው የሌብነት ቁጥሩ የቀነሰው)
- ተማሪዎችም ሌብነት እንደማያዋጣ የተገነዘቡ መሆናቸውን ያመላከተ ነው
- “አምስት ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸው ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ አሳልፈዋል።”
- “ሌሎች አምስት ትምህርት ቤቶች ድግሞ ካስፈተኗቸው ውስጥ 95 ከመቶ ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል።”
ከፍተኛ አፈጻጻም ያሳዩ አስር ትምህርት ቤቶች (በደረጃ)፦
1. አዲስ አለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት (ደብረ ማርቆስ)
2. ደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት
3. ባህርዳር ስቴም (STEM) ትምህርት ቤት
4. ሀይራንዚ አዳሪ ትምህርት ቤት (ስልጤ ዞን)
5. ሊች ጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት (ሀድያ)
6. ኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤት (ናዝሬት)
7. ኮተቤ ሼርድ ካምፓስ
8. የኔታ አካዳሚ
9. ወላይታ ሊቃ አዳሪ ትምህርት ቤት
10. ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት
- በተፈጥሮ ሳይንስ መስክ 200 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት አምጥተዋል።
- በማህበራዊ ሳይንስ መስክ 15 ተማሪዎች ብቻ ከ500 በላይ ውጤት አምጥተዋል።
- በተፈጥሮ ሳይንስ ከፍተኛው ውጤት 649 ሲሆን በአዲስ አበባ የልደታ ክሩዝ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት።
- በማህበራዊ ሳይንስ ከፍተኛው ውጤት 533 ሲሆን የደብረ ማርቆስ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ነው።
- በከተማ ደረጃ አዲስ አበባ፣ ሀረሪ እና ድሬዳዋ የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ ከተሞች ናቸው።
- በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገበው አማካይ ውጤት 28.65 ከመቶ ነው። አንድ ተማሪ በአማካኝ ከመቶ ያገኘው ውጤት ማለት ነው።ይህ ማለት አንድ ተማሪ በአቦ ሰጥ ምንም ሳያስብ ፈተናውን ቢሠራ የሚያመጣው ውጤት ነው።
- ከፍተኛው ውጤት 30.99 ከመቶ በኬሚስትሪ ትምህርት ሲሆን ዝቅተኛው 25.62 በመቶ በማህበራዊ ሳይንስ ሒሳብ ትምህርት የተመዘገበ ነው።
- ሀገራዊ አማካይ ውጤቱ ከጾታ አንጻር ሲታይ የወንዶች አማካይ ውጤት 29.55 ከመቶ ሲሆን የሴቶች ደግሞ 27.64 ከመቶ ሆኗል።
ሀናን ናጂ አህመድ
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው የክሩዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት።
ተማሪ ሀናን ናጂ አህመድ በተፈጥሮ ሳይንስ 649 ውጤት በማስመዝገብ ከዘንድሮ ተፈታኞች በቀዳሚነት ተቀምጣለች።
ባስመዘገበችው ውጤት በጣም ደስተኛ መሆኗን የገለጸችው ተማሪ ሀናን፤ በቀጣይም ለበለጠ ውጤት እንደመትተጋ ተናግራለች።
ክሩዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኝ የግል ትምህርት ቤት ነው።
ወላይታ ሊቃ
ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ካስመዘገቡ አስር ትምህርት ቤቶች መካከል 9ኛ ደረጃ አጊኝቷል።
ትምህርት ቤቱ በ2015 ዓ.ም ካስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ውጤት ያመጡት፦
• ከ600-623 ➧3 ተማሪዎች
• ከ500-599 ➧ 26 ተማሪዎች
• ከ400-499 ➧ 31 ተማሪዎች
• ከ350-399 ➧ 12 ተማሪዎች
• ከ324-345 ➧ 4 ተማሪዎች
- በትምህርትትምህርት ቤቱ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 623 መሆኑ ተግልጿል።
- “የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ግንቦት ወር ይሠጣል።”
- “ከሰኔ ጀምሮ ለሦሥት ወራት ዩኒቨርሲቲዎች የክረምት ትምህርት ይሰጣሉ።”
“በሚቀጥለው ዓመት የሚሰጠው ፈተና ድብልቅ ፈተና ይሆናል። ግማሹን በኦንላይን፣ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ በአካል ይሰጣል።” @tikvahuniversity
ይህ ያለንበትን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ፤ ለምን በማሰብ እና በዕውቀት እንደማንመራ የሚያሳይ፤ ለምን ሌብነት የተንሰራፋባት አገር እንደሆንን፤ ዘረኝነት ለምን የሙጢኝ ብለን እንደያዝን፤ በማኅበራዊ ሚዲያ በየዕለቱ የሚዋሹንን ሳናገናዝብ እንደምንሰማ፤ የወሬ ሰለባ ለምን እንደሆንን፤ ወዘተ ባጠቃላይ የማንነታችን መገለጫ ይህ በያመቱ የሚወጣ ፈተና ውጤት ነው። ጥያቄው ያ ሁሉ በመቶ ሺህ የሚቆጠር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አጠናቀቀ ተብሎ በየዩኒቨርሲቲው ተመርቆ ሲወጣ የነበረባት አገር ምነው አሁን ከምታስፈትነው ውስጥ ከ3በመቶ ያላለፈ ተማሪ ለዪኒቨርሲቲ ማብቃት አቃታት?
መዘንጋት የሌለበት ሐቅ ይህ ሁኔታ ጀመረ እንጂ አያቆምም፤ ላለፉት 30 ዓመታት ሲፈርስ የነበረ ተቋም ባንድ ጀምበር ተዓምር አይሠራም፤ የሚቀጥለው ዓመትም ውጤት ከዚህ የሚለይ አይደለም። አሁን ዘጠነኛ ክፍል ያሉት ተማሪዎች ወደ 10ኛ ክፍል ሲደርሱ ነው ለውጥ ማየት የምንጀምረው። የትሕነግ ወንበዴዎችን መርቶ ለሥልጣን ያበቃው የምዕራባውያን ድጋፍና የ30 ዓመታት የትሕነግ የክፋት መርዝ በቶሎ የሚለቅ አይደለም። በትንሹ አንድ ትውልድ አክሽፎ እና ቀጣይ ትውልዶችን መርዞ ነው ያለፈው። ይህ እስከሚጸዳ ዓመታት የግድ መውሰዱ አይቀርም። የተጀመረው ተሃድሶ ሳይደናቀፍ ማስቀጠል መቻል በራሱ ታላቅ ዕድል ነው።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply