የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክተው ትላንት መግለጫ ሰጥተዋል። በአጠቃላይ በ2015 ዓ.ም ከተፈተኑ ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል። በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ ለፈተና ከተቀመጡ በድምሩ 845,677 ተማሪዎች 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡት 27, 267 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። በዚህም 160 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎችን በሬሜዲያል ፕሮግራም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚቀበሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል። የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ትምህርት ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻላቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል። 376 ተፈታኞች በቡድን፤ 483 ተፈታኞች ደግሞ በግል ጥፋት ፈጽመዋልጥፋቶቹም፤ለሌላ … [Read more...] about ከ3,106 ትምህርት ቤቶች 1,328ቱ (44%) አንድም ተማሪ አላሳለፉም