የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክተው ትላንት መግለጫ ሰጥተዋል። በአጠቃላይ በ2015 ዓ.ም ከተፈተኑ ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል። በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ ለፈተና ከተቀመጡ በድምሩ 845,677 ተማሪዎች 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡት 27, 267 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። በዚህም 160 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎችን በሬሜዲያል ፕሮግራም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚቀበሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል። የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ትምህርት ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻላቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል። 376 ተፈታኞች በቡድን፤ 483 ተፈታኞች ደግሞ በግል ጥፋት ፈጽመዋልጥፋቶቹም፤ለሌላ … [Read more...] about ከ3,106 ትምህርት ቤቶች 1,328ቱ (44%) አንድም ተማሪ አላሳለፉም
Ethiopian Education
የትግሬ ወራሪ ለ፳፯ ዓመት ያደነቆረውን ትውልድ ለመታደግ አዲስ የጸረ መሃይምነት ዘመቻ ሊጀመር ይገባል
በኢትዮጵያ ጥልቅ አሳቢና ሩቅ አላሚ ትውልድ ለመፍጠር የንባብ ባህልን ማዳበር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበባትና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳ ገለጹ። የንባብ ባህልን ለማጎልበት ጥረት ቢደረግም የአንባቢው ቁጥር እስካሁን የሚታሰበውን ያክል አልደረሰም ብለዋል። “ንባብ ለሠላምና ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት በሚል” መሪ ሃሳብ በአብርኆት ቤተ-መጻሕፍት ከየካቲት 9 እስከ የካቲት 11 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቆይ የንባብ ባህል ሳምንት ተጀምሯል። ለ4ተኛ ጊዜ በተካሄደው የንባብ ባህል ሳምንት ላይ የተገኙት ዶ/ር ሂሩት ካሳ፤ የንባብ ባህልን ለማጎልበት ጥረት ቢደረግም የአንባቢው ቁጥር የሚታሰበውን ያክል አልጨመረም ብለዋል። በንባብ ሳምንት ዝግጅቱ ላይ በርካታ አንባቢያን እንዲሳተፉ የተለያዩ ማነቃቂያዎች ቢደረጉም በርካታ አንባቢዎችን ለማፍራት አለመቻሉን … [Read more...] about የትግሬ ወራሪ ለ፳፯ ዓመት ያደነቆረውን ትውልድ ለመታደግ አዲስ የጸረ መሃይምነት ዘመቻ ሊጀመር ይገባል