በኢትዮጵያ ጥልቅ አሳቢና ሩቅ አላሚ ትውልድ ለመፍጠር የንባብ ባህልን ማዳበር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበባትና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳ ገለጹ።
የንባብ ባህልን ለማጎልበት ጥረት ቢደረግም የአንባቢው ቁጥር እስካሁን የሚታሰበውን ያክል አልደረሰም ብለዋል።
“ንባብ ለሠላምና ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት በሚል” መሪ ሃሳብ በአብርኆት ቤተ-መጻሕፍት ከየካቲት 9 እስከ የካቲት 11 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቆይ የንባብ ባህል ሳምንት ተጀምሯል።
ለ4ተኛ ጊዜ በተካሄደው የንባብ ባህል ሳምንት ላይ የተገኙት ዶ/ር ሂሩት ካሳ፤ የንባብ ባህልን ለማጎልበት ጥረት ቢደረግም የአንባቢው ቁጥር የሚታሰበውን ያክል አልጨመረም ብለዋል።
በንባብ ሳምንት ዝግጅቱ ላይ በርካታ አንባቢያን እንዲሳተፉ የተለያዩ ማነቃቂያዎች ቢደረጉም በርካታ አንባቢዎችን ለማፍራት አለመቻሉን ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፓርትነርሺፕና የምርምር ግራንት አማካሪ ፕሮፌሰር ሐረገወይን አሰፋ በበኩላቸው፤ ንባብ የሰው ልጅ ታሪኩን፣ ማኅበራዊና ባህላዊ አኗኗሩን የሚገልፅበት መንገድ እንደሆነ ገልጸዋል።
በመሆኑም ማንበብ ሙሉ ሰው ስለሚያደርግ ሰዎች የንባብ ባህልን ማዳበርና ልምድ ማድረግ አለባቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። (አዲስ ሚዲያ)
በቀድሞው አገዛዝ ዘመን ከተደረጉ ዋንኛ ስኬቶች መካከል የጸረ መሃይምነት ዘመቻ ዋና ተጠቃሽ ነው። ይህ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖችን ከመሃይምነት ጥቁር መጋረጃ ነጻ ያወጣ ዘመቻ አሁንም ላለፉት ፳፯ ዓመታት የትግሬ ወራሪ ቡድን ራሱ ደንቁሮ የአገራችንን ሕዝብ ለከፋ የመሃይምነት አደጋ እንዳጋለጠው ጎልጉል ያምናል። ይህም ድንቁርና አሁን ለሚታየው የአስተሳሰብ፣ የአመለካከት መቀንጨር እንዳጋለጠን ማስረጃ አቅርቦ መሞገት ይቻላል። ስለዚህ መንግሥትም ሆን የከተማ እና የክልል መስተዳድሮች በዚህ ላይ በመምከር አንድ ወጥ አገራዊ ዘመቻ እንዲያስተባብሩ ጎልጉል ጥሪ ያቀርባል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Assefa says
Subscribe me