በ2016 ዓም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 684 ሺህ 205 ተማሪዎች ያለፉት 36 ሺህ 409 ወይም 5.4 በመቶ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከትላንት በስቲያ ማስታወቃቸው ይታወሳል። ከዚህ በታች ያለውን መረጃ ያሰባሰብነው ከመንግሥታዊ ሚዲያና ከቲክቫህ ነው። በአጠቃላይ 1 ሺህ 363 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ሲሆን በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ 4 ትምህርት ቤቶች ከሐረሪ ክልል ውጭ ሁሉም ክልሎች ላይ አንድም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን አመላክተዋል።በአጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት ከ500 በላይ ያመጡ ተማሪዎች ባለፈው ዓመት 273 የነበሩ ሲሆን በአሁኑ 1ሺ 220 ተማሪዎች ከ500 በላይ ያመጡ ናቸው ተብሏል።እንዲሁም በዘንድሮ 12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 5.4 በመቶ ፈተናውን አልፈዋል ይህም ማለት … [Read more...] about የ፲፪ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት የዘንድሮና የአምናው መጠነኛ ንጽጽር