መግቢያ ሰሞኑን የፋሲል ቤተመንግሥት እድሳት ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል፤ ምክንያቱ ደግሞ የግንቡ የውጭ ገፅታ ቀለም ከተለመደው ተቀይሮ መታየቱ ነው። ውዝግቡን ተከትሎም በእድሳቱ ስራ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸውም ሆኑ ሌሎች የቅርስ ጥበቃ ባለሙያዎች ምላሾችን ሰጥተዋል። ሆኖም የተሰጡት ምላሾች ውዝግቡን የማቆም አቅም ያላቸው አይመስልም። በፕሮጀክቶች ቅደም ተከተል ላይ ያለንን ጥያቄ ለጊዜው ያዝ እናድርገውና የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የዓለም ቅርስ የሆነው የፋሲል ቤተመንግሥት መታደሱን የሚቃወም የለም። በተለይም ግቢው ውስጥ የተሰራው ላንድስኬፕና ለቱርስቶች የተዘጋጀው የማረፊያ ቦታ በጥሩ ጎኑ የምንመለከተው ነው፤ እንዲሁም የግንቡ መዋቅራዊ ዝንፈቶችን ለማስተካከል የተወሰደው እርምጃም መልካም የሚባል ነው። ሆኖም የብዙዎቻችን ጥያቄና ውዝግብ መንስኤ የሆነው በግንቡ ውጫዊ ገፅታ … [Read more...] about ታሪካዊዉ የፋሲል ቤተመንግሥት ለምን ነጣ?