በኢትዮጵያ የአጼዎች እና የሥልጣኔ መናገሻነት ስማቸው ከሚጠቁሱት ታሪካዊ ስፍራዎች መካከል ጎንደር አንዷ ናት። ጎንደርን ማዕከል ያደረገው የ17ኛው እና የ18ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ የእድገት፣ የምርት መፍለቂያ፣ የሃይማኖት ማዕከል እንዲሁም በኪነጥበብ ታላቅ ስፍራ የደረሰችበት ወቅት እንደሆነ ይጠቀሳል።። የእነዚህ ታላላቅ ተግባራት ማሳያዎች መካከል ደግሞ ከጎንደር ነገሥታት መካከል አንዱ በነበሩት አጼ ፋሲለደስ በ17ኛው ክፍለ ዘመን የተገነባው የፋሲል ግንብ ነው። በአስደናቂነቱ፣ በታሪካዊነቱ እና በኪነ ህንጻ ጥበቡ ብዙ የተባለለት እና እና በዩኔስኮ የዓለማችን ቅርስ አንዱ ሆኖ የተመዘገበው የፋሲል ግንብ ተሰነጣጥቆ እና አርጅቶ መቆየቱ በርካቶች ሲያነሱት የነበረ ጉዳይ ነው። የጥገና እድሳት እየተከናወለት ያለው ታሪካዊው የፋሲል ግንብ በቅርቡ ይፋ መደረጉን ተከትሎ … [Read more...] about የፋሲል ግንብ እድሳት እንዴት ተካሄደ? የመንጣቱ ምክንያት?
Fasil Palaces
ታሪካዊዉ የፋሲል ቤተመንግሥት ለምን ነጣ?
መግቢያ ሰሞኑን የፋሲል ቤተመንግሥት እድሳት ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል፤ ምክንያቱ ደግሞ የግንቡ የውጭ ገፅታ ቀለም ከተለመደው ተቀይሮ መታየቱ ነው። ውዝግቡን ተከትሎም በእድሳቱ ስራ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸውም ሆኑ ሌሎች የቅርስ ጥበቃ ባለሙያዎች ምላሾችን ሰጥተዋል። ሆኖም የተሰጡት ምላሾች ውዝግቡን የማቆም አቅም ያላቸው አይመስልም። በፕሮጀክቶች ቅደም ተከተል ላይ ያለንን ጥያቄ ለጊዜው ያዝ እናድርገውና የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የዓለም ቅርስ የሆነው የፋሲል ቤተመንግሥት መታደሱን የሚቃወም የለም። በተለይም ግቢው ውስጥ የተሰራው ላንድስኬፕና ለቱርስቶች የተዘጋጀው የማረፊያ ቦታ በጥሩ ጎኑ የምንመለከተው ነው፤ እንዲሁም የግንቡ መዋቅራዊ ዝንፈቶችን ለማስተካከል የተወሰደው እርምጃም መልካም የሚባል ነው። ሆኖም የብዙዎቻችን ጥያቄና ውዝግብ መንስኤ የሆነው በግንቡ ውጫዊ ገፅታ … [Read more...] about ታሪካዊዉ የፋሲል ቤተመንግሥት ለምን ነጣ?