ሁሉም ባይባልም አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዋና የፖለቲካ ፕሮግራም ሶሻል ዴሞክራሲ ወይም ሊበራል ዴሞክራሲ ወይም ምርጫን ማዕከሉ ያደረገ ዴሞክራሲያዊ ፖሊሲ ነው። የኢኮኖሚ ፕሮግራማቸው ደግሞ ገበያ መር ኢኮኖሚ ነው። እነዚሁ ፓርቲዎች በምርጫ ክርክር ሲደረግ በዋናነት እያነሱ የሚከራከሩት መንግሥት ኢኮኖሚውን ተቆጣጥሮታል፤ የዕዝ ኢኮኖሚ ነው አገሪቱን ለችግር የዳረጋት፣ የኢኮኖሚው አካሄድ በገበያ እንጂ በመንግሥት መመራት የለበትም በሚል የከረረ ተቃውሞ በማቅረብ ሲቃወሙ ላለፉት በርካታ ዓመታት ሰምተናል። ባለፈው ሰኞ መንግሥት የአገሪቱን ዐቢይ (ማክሮ) ኢኮኖሚ ወደ ገበያ መር የሚወስድ ውሳኔ ይፋ ሲያደርግ እነዚሁ ተቃዋሚዎች “እሰይ ስለቴ ሰመረ” ባይሉም ቢያንስ ለዓመታት ሲሟገቱለት የነበረው ሃሳብ ድል አድርጎ በማየታቸው ጥንቃቄ የተሞላበት ድጋፍ ሊያሰሙ የሚጠበቅ … [Read more...] about “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አእምሮና የደም ዝውውር ሊኖረው ነው”
yonas biru
“አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት)
“አመጽ ሁሉ መመራት ያለበት ለበቀል ባለህ ጥማት ሳይሆን፤ ለፍትሕ ባለህ ከፍተኛ ፍላጎት መሆኑ እጅግ አስፈላጊ ነው” ደራሲ አብሂጂት ናስካር 1. ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ። በቅርብ ዓመታት ለምዕራባውያን መንግሥታት የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ ያስተላለፈው መልዕክት "ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ" የሚል ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ መብትና ድምጽ በረገጠ እቡይ መንፈስ፤ ዶ/ር ዮናስና አጋሮቻቸው፤ ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ፤ ደጅ ጥናት ላይ ናቸው። ይህ ዓይነት እኩይ መንንፈስ፤ እንኳን ትላንት ወደ ፖለቲካው መድረክ አንገታቸውን ብቅ ላደረጉ ይቅርና፤ ከ40 ዓመታታ በላይ በምዕራባውያን ጉያ ውስጥ የነበረውና የኢትዮጵያን ጥቅም ለምዕራባውያን አሳልፎ ለሸጠው ለሕወሃትም አልበጀም። ገራሚው ነገር፤ ከዓመት ተኩል በፊት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍቅር ታመው … [Read more...] about “አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት)
“አንድ ሰው ለመግደል ሕንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት (ክፍል 1)
የኢትዮጵያ ሕዝብ እራሱ በመረጠው መንግሥት እንዲተዳደር ይነሳ የነበረው ጥያቄ፤ ከ50 ዓመታት በላይ በተደረገ ትግልና በተከፈለ ከፍተኛ መስዋዕትነት በሰኔ 2013 ምላሽ አግኝቷል። ምንም እንኳን ምርጫው አንዳንድ መሰናክሎች ቢያጋጥሙትም፤ ገለልተኛና ተአማኒ በሆነ የምርጫ ቦርድ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመንግሥት ሥልጣን ምርጫ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው ነው። ይህ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብና በበርካታ ሃገራዊና አለም አቀፍ ተቋማት ፍትሃዊና ሚዛናዊ ምርጫ ነው ቢባልም፤ ይህ መንግሥት በሕዝብ የተመረጠ አይደለም የሚሉ ግን አልጠፉም። የሕወኃት መራሹ መንግሥት ተወግዶ ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ፤ ከሕዝብ ያገኙት ድጋፍ በሃገራችን ታይቶ የማይታወቅ ድጋፍ ነበር። በጊዜ ሂደት ግን፤ … [Read more...] about “አንድ ሰው ለመግደል ሕንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት (ክፍል 1)