የኢትዮጵያ ሕዝብ እራሱ በመረጠው መንግሥት እንዲተዳደር ይነሳ የነበረው ጥያቄ፤ ከ50 ዓመታት በላይ በተደረገ ትግልና በተከፈለ ከፍተኛ መስዋዕትነት በሰኔ 2013 ምላሽ አግኝቷል። ምንም እንኳን ምርጫው አንዳንድ መሰናክሎች ቢያጋጥሙትም፤ ገለልተኛና ተአማኒ በሆነ የምርጫ ቦርድ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመንግሥት ሥልጣን ምርጫ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው ነው። ይህ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብና በበርካታ ሃገራዊና አለም አቀፍ ተቋማት ፍትሃዊና ሚዛናዊ ምርጫ ነው ቢባልም፤ ይህ መንግሥት በሕዝብ የተመረጠ አይደለም የሚሉ ግን አልጠፉም። የሕወኃት መራሹ መንግሥት ተወግዶ ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ፤ ከሕዝብ ያገኙት ድጋፍ በሃገራችን ታይቶ የማይታወቅ ድጋፍ ነበር። በጊዜ ሂደት ግን፤ … [Read more...] about “አንድ ሰው ለመግደል ሕንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት (ክፍል 1)
Dawit Wolde Giorgis
የ”ከሃዲው” ዳዊት የሌብነት መረጃ
ባለፈው ሳምንት "ከሃዲው ዳዊት ወልደጊዮርጊስን" አስመልክቶ "ዳዊት ወልደጊዮርጊስ – የጸረ ኢትዮጵያዊነት መገለጫ" በሚል እርዕስ ዜና ማቅረባችን ይታወሳል። በዜናው ግንባር የተጠቀሰው ሳይጀመር በከሸፈው "የሽግግር መንግሥት" ማመልከቻ ጉዳይ ነበር። ያተምነውን ዜና ተከትሎ አቶ ለማ መገርሳ "ተውኝ። ልኑርበት" ሲሉ ስለጉዳዩ ምንም እንደማያውቁ በይፋ መናገራቸው፣ ፕሮፌሰር ተዘራ ዳዊት የሤራው ስብስብ አገር ለመርዳት መስሏቸው ከገቡ በኋላ ሲያዩት ሃያ ሰባት ዓመታት ኢትዮጵያን ሲዘርፍና ሲያደማ የኖረውን ትህነግን ወደ ስልጣን ለመመለስ እንደሆነ ሲረዱ ራሳቸውን ማግለላቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ራሱ አስተባባሪውም "የለሁበትም" ሲል ዳግም ክህደቱን አሳይቷል። በዚህ ዜና ላይ ዳዊት ከሃዲና ዘራፊ መሆኑን ለማሳየት ከረሃብ ሰለባዎች ጉሮሮ መንትፎ አገር ስለመክዳቱ መግለጻችን ከተራ … [Read more...] about የ”ከሃዲው” ዳዊት የሌብነት መረጃ