* በሶስት ወራት ብቻ ከ6,600 በላይ ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰድዋል" - የትግራይ የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በትግራይ ክልል ከተሞች በሚገኙ አውራ መንገዶች "ልጄ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ስደት ሲሄድ በአጋቾች ተይዞ ይህንን ብር ክፈል፣ ካልከፈልክ ትገደላለህ ብለውኛል እርዱኝ" የሚሉ በትልቅ ባነር በተቀመጠ የወጣቶች ፎቶ አስደግፈው እርዳታ የሚለሙኑ ወላጆች ተበራክተዋል። ከነዚሁ ወላጆች የአክሱም ከተማ ነዋሪዋ ወ/ሮ ኣስካለ ውብኣንተ አንድዋ ሲሆኑ፤ ይጦረኛል ብለው ኮስኩሰው አስተምረው ያሳደጉት ወንድ ልጃቸው ህገ-ወጥ ስደት የነጠቃቸው እናት ናቸው። "ልጄ በጦርነቱ ማግስት በአከባቢው የስራ እድል በማጣቱ በህገ-ወጥ መንገድ የተለያዩ ሃገራት ደንበር አቋርጦ ሊብያ ሲደርስ ለሰው ህይወት ቁብ በሌላቸው ሽፍቶ እጅ ወድቆ ቁም ስቅሉን እያሳዩት ነው" ብለዋል። "አካል … [Read more...] about በትግራይ ከሞትና ከአካላዊ ጉዳት የተረፉት ለስደት ተዳርገዋል
tplf children soldiers
ሰሞኑን በተደረገ አንድ መድረክ ላይ አካል ጉዳተኛ የወያኔ ታጣቂዎች ከተናገሯቸው…
ደብረ ፅዮን ተከቦ ለማዳን እኮ አግአዚ እና ሃውዜን የተባሉ ሁለት ክፍለ ጦር ይበሉ ወጣቶች (ይለቁ) ተብሎ አልቀው የተረፍነው ተርፈን መስዋእት ሆነዋል። ከመቼው ረሳችሁት እረሱት? ደብረጺዮንን ብቻም አይደለም ሌሎችም አመራሮችን ለማዳን ተብሎ እኮ ብዙ መስዋእት ተከፍለዋል። ወጣት አልቋል! አሁን የትግራይ እናት በረንዳ አደር ሁናለች። በየቤታችን ያለዉ ጉድ አቅፈን ይዘን ዝም ብለን ኖረናል። እዚህ ያላቹ አመራሮች ጭምር ጆሮ ዳባ እንደሆናቹ እናዉቃለን ጨንቆን እንጂ። ሰልፍ ስንወጣ እኮ ለጠላት አመቺ መሆኑ ሳይገባን ቀርቶ አደለም መፍትሄ ስናጣ ነዉ። ለምሳሌ እኔ ሙሉ ሰዉነቴ ኦፕሬሽን ብቻ ነዉ ሂወት አለኝ ብዪ አላስብም። ረሳችሁን በ2013 አብረን እኮ ብዙ ችግር አሳልፈን ነበር አሁን የመኪና ሰርቪስ አገልግሎት እንኳን እየገፈተራቹ እና በማስክ ነዉ ምታልፉ። የ18 አመት ልጆች … [Read more...] about ሰሞኑን በተደረገ አንድ መድረክ ላይ አካል ጉዳተኛ የወያኔ ታጣቂዎች ከተናገሯቸው…
መፍትሔ የሚሹ የኢትዮጵያ የጎን ውጋቶች
ኢትዮጵያ ባለፉት አራት በላይ በሆኑ ዓመታት ከባድ ጫናዎችን ተሸክማ ቆይታለች። ይልቁንም የሰሜኑ ጦርነት በውስጥም በውጭም ገፊና ሳቢ ምክንያቶችን ፈጥሮ ሲያናውጣት ቆይቷል። ይኸው ጦርነት ኹለት ዓመት ሊደፍን የዋዜማው እለት የተደረሰው የሰላም ስምምነት በጉዳዩ ላይ የብዙዎች ተስፋ እንዲያንሰራራ አድርጓል። ኢትዮጵያን ችግሮቿ ሁሉ የተቀረፉ ያህል ብዙዎች ተሰምቷቸዋል። ሆኖም አሁንም ኢትዮጵያ የጎን ውጋት የሆኗት ችግሮች አሉ። የወሰንና አስተዳደር ጥያቄዎች፣ የታጣቂ ኃይሎች እንቅስቃሴ፣ የምጣኔ ሀብት መዳከም፣ ማንነትን መሠረት ያደረጉ የተለያዩ ጥቃቶች አሁንም ይስተዋላሉ። እናም ኢትዮጵያ ችግሮቿን ቁልቁል ደርድራ አንድ በአንድ በማስተካከል፣ እንደ ሰሜኑ ጦርነት ሁሉ በኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል እና ጋምቤላ እንዲሁም በሌሎች ክልሎችም ሌሎቹንም ችግሮች እንድትቀርፍ ይጠበቅባታል። በሰብአዊ … [Read more...] about መፍትሔ የሚሹ የኢትዮጵያ የጎን ውጋቶች
ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን
ትግራይ የሸመቀው የወንበዴና አሸባሪ ቡድን ረቡዕ ስብሰባ አካሄድኩ ብሎ በሚዘውራቸው ሚዲያ ዘግቦ ነበር። በስብሰባው ላይ የ4 ወር የሥራ አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን ደብረጽዮን ትግራይን ራስገዝ አገር እናደርጋለን ብሏል። “ተልዕኳችን” ሲል አገርን የማፍረስ ዕቅዱን የተናገረው ደብረጽዮን ዓላማችን ትግራይን አገር ማድረግ ነው ብሏል። ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሰበሰባቸው ደካሞች እጅግ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ሲናገር “የምንገኝበት ምዕራፍ በውይይት እና በጦርነት ሊቋጭ የሚችልበት ሁኔታ የሰፋ ነው” ብሏል። ደብረጽዮን አገር አደርጋታለሁ በሚላት ትግራይ እጅግ በርካታው ሕዝብ አጥንትን ዘልቆ በሚገባ ችጋር ውስጥ የተሸማቀቀ ሲሆን ሠርቶ የሚያበላው ልጆቹን ለጦርነት ገብሯል፤ ለዐቅመ ሔዋን ያልደረሱ ሴቶች ልጆቹን ደግሞ ለሴተኛ አዳሪነት እየሸጠ ነው። ደብረጽዮንና ወንበዴ ጓደኞቹ ይቺን ትግራይ … [Read more...] about ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን
ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ መቶዎችን ጨፍጭፏል
የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ጭና ተክለሃይማኖት በነሃሴ 26ና 27 ሁለት ቀን ብቻ ከመቶ ሃያ በላይ ንጹሃንን መጭፍጨፉ ከአካባቢው መረጃ እየወጣ ይገኛል። ትህነግ ለምን ጭፍጨፋውን እንደፈጸመ መረጃዎቹ እስካሁን ዝርዝር አላቀረቡም። ይሁን የቀብር ስፍራዎችን በፎቶ ማስረጃ ይፋ እየሆኑ ሲሆን፤ በጅምላ የተጨፈጨፉት ወገኖች ማንነት እየተለየ መሆኑ ታውቋል። ትህነግ የአማራና የአፋር ክልልን ከወረረ በሁዋላ በርካታ የጅምላ ጭፍጨፋና የነብስ ወከፍ ግድያ መፈጸሙ ይፋ እየሆነ ነው። መረጃዎች መሰራጨት ከጀመሩ በሁዋላ ክልሉ የሚከተለውን በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በኩል ገልጿል። እንዳለ አቅርበነዋል። የጀግኖቻችንን የተቀናጀ ጥቃት ሲቀምስ፣ በየጫካው እየተፋለሙት ያሉትን ጀግኖችን መቋቋም ያልቻለው ወራሪ በየቤታቸው የነበሩ አዛውንቶችን፣ ህፃናትንና … [Read more...] about ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ መቶዎችን ጨፍጭፏል
በሱዳን ስደተኛ ካምፕ የነበሩት ሳምሪዎች ለትህነግ ተዋግተዋል
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) ከትግራይ ክልል ወጥተው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በጦርነት መሳተፋቸውን ባወጣው መግለጫ አመለከተ። ዩኤንኤችሲአር ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ የሚገኙና ድጋፍ የሚደረግላቸውን ስደተኞች የመረጃ ሁኔታን ከልሷል። በዚሁ መሰረት በመጠለያ ጣቢያው ተመዝግበው የነበሩ ስደተኞች ቁጥር ከቅርብ ወራት ወዲህ መቀነሱንና በስደተኛነት ተመዝግበው የነበሩ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ይመለሱ ወይም የት ይሂዱ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ይፋ አድርጓል። በግጭት ውስጥ የተሳተፈን ሰው በስደተኛነት የማይቀበለው ዩኤንኤችሲአር በስደተኛነት ተመዝግቦ በግጭት ውስጥ የተሳተፈ ማንኛውንም ሰው ዳግም እንደማይቀበል አድርጓል። ከኢትዮጵያ ግጭት ሸሽተው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ ውስጥ … [Read more...] about በሱዳን ስደተኛ ካምፕ የነበሩት ሳምሪዎች ለትህነግ ተዋግተዋል
የዳያስፖራ ትህነጎች ቀጣይ አጀንዳ
የትግራይ ዲያስፖራ የሳይበር ቡድን (Diaspora Cyber Team) ትላንት (Sep 5) ስብሰባ ነበራቸው።የእኛ ሰዎችም የሳይበር ውይይታቸውን ሰብረው በመግባት ታድመው ወጥተዋል። አጀንዳዎቹ:- 1- አለም አቀፍ ጫናዎችን በድጋሜ በአዲስ መልክ እንዴት እንፍጠር? 2- ትግራይ ውስጥ ቤተሰቦቻችን በርሃብ እያለቁ ነው። ለዚህስ መፍትሄው ምንድነው? 3- ህወሓት/የትግራይ መንግስት ምን ማድረግ አለበት? የሚሉ ናቸው። የተስማሙባቸው ነጥቦች:- 1ኛ) ጦርነቱ ትግራይ መሬት ላይ በነበረበት ወቅት ተዘረፍን ፣ ሴቶች ተደፈሩ ፣ በጅምላ ተገደልን ... ብለን የአለም አቀፍ መንግስታት ጫና እንዲፈጥሩ አድርገናል። አሁን ያንን መንገድ መከተል አዋጭ ስላልሆነ 5.2 ሚሊዮን ህዝብ በርሃብ እየተጎዳና እየሞተ እንደሆነ ፣ ወደ ትግራይ እየገባ ያለው የእርዳታ እህልም እጅግ … [Read more...] about የዳያስፖራ ትህነጎች ቀጣይ አጀንዳ
ከወልዲያ አምልጦ የመጣው የትህነግ ኃይል እንዳይመለስ ተደረገ
በአማራ ክልል ሰርጎ የገባውን የአሸባሪውን ህወሓት ሀይል በመደምሰስ ላይ መሆኑን በሰሜን ወሎ ግንባር የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊቱ ክፍል አስታወቋል ። ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ዋድላ ወረዳ ፣ ኮን ከተማ እንዲሁም በጋሸና አካባቢ የሚገኘውን የአሸባሪው የህወሓት ቡድን በመምታት አኩሪ የጀግንነት ተግባር መፈጸሙን አዛዡ አረጋግጠዋል። ጀግኖቹ የሰራዊት አባላት በአካባቢው የሚገኝ የጠላት ፣ የሰውና የመሳሪያ ሀይል በየትኛውም አቅጣጫ እንዳይወጣ በማድረግና በመደምሰስ ከዋድላ ወረዳ እስከ ጋሸና ከተማ በመቆጣጠር ድል መቀዳጀታቸውን አመልክተዋል ። ሠራዊቱ ከወልዲያ አምልጦ የመጣውን ጠላት በመከታተል ፣ በዋድላ ወረዳና አካባቢ የመሸገውን የጠላት ሀይል እና መሳሪያ በመደምሰስ ጋሸና ከተማን መቆጣጠሩን የመከላከያ ሠራዊት አስታውቋል። (ኢብኮ-ፎቶ ማርቆሥ አለሙ) ጎልጉል … [Read more...] about ከወልዲያ አምልጦ የመጣው የትህነግ ኃይል እንዳይመለስ ተደረገ
የ”ከሃዲው” ዳዊት የሌብነት መረጃ
ባለፈው ሳምንት "ከሃዲው ዳዊት ወልደጊዮርጊስን" አስመልክቶ "ዳዊት ወልደጊዮርጊስ – የጸረ ኢትዮጵያዊነት መገለጫ" በሚል እርዕስ ዜና ማቅረባችን ይታወሳል። በዜናው ግንባር የተጠቀሰው ሳይጀመር በከሸፈው "የሽግግር መንግሥት" ማመልከቻ ጉዳይ ነበር። ያተምነውን ዜና ተከትሎ አቶ ለማ መገርሳ "ተውኝ። ልኑርበት" ሲሉ ስለጉዳዩ ምንም እንደማያውቁ በይፋ መናገራቸው፣ ፕሮፌሰር ተዘራ ዳዊት የሤራው ስብስብ አገር ለመርዳት መስሏቸው ከገቡ በኋላ ሲያዩት ሃያ ሰባት ዓመታት ኢትዮጵያን ሲዘርፍና ሲያደማ የኖረውን ትህነግን ወደ ስልጣን ለመመለስ እንደሆነ ሲረዱ ራሳቸውን ማግለላቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ራሱ አስተባባሪውም "የለሁበትም" ሲል ዳግም ክህደቱን አሳይቷል። በዚህ ዜና ላይ ዳዊት ከሃዲና ዘራፊ መሆኑን ለማሳየት ከረሃብ ሰለባዎች ጉሮሮ መንትፎ አገር ስለመክዳቱ መግለጻችን ከተራ … [Read more...] about የ”ከሃዲው” ዳዊት የሌብነት መረጃ
የኢሰመኮና የሪፖርተሩ ጎዶሎ ሪፖርት ብዙ ይነግረናል – አለ ገና!!
ራሱን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) ብሎ በመጥራት ለበርካታ ዓመታት አገራችንን ሲያሸብር የኖረው እና በዓለምአቀፉ የአሸባሪዎች ቋት በአሸባሪነት የተዘመገበው፤ በቅርቡም በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአሸባሪነት የተመዘገበውን ትህነግ “አሸባሪ” ብሎ ለመጥራት ሲጨንቃቸው የሚታዩ የአገር ውስጥና የውጪ (እንደ ቢቢሲ፣ ቪኦኤ እና ጀርመን ድምፅ) ሚዲያ ተቋማት መኖራቸው በግልጽ እየታየ የመጣ ክስተት ሆኗል። በቅርቡ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባወጣው መግለጫ “ሕወሓትን የክልል መንግስት ማለት እና በክልል ደረጃ የመከላከያ ኃይል የሚል ስያሜ መጠቀም የተወካዮች ምክር ቤት ስልጣንን አለማከበር ነው” ካለ በኋላ “እነዚህን ስያሜዎች በሚጠቀሙ ሚዲያዎች ላይ ባለስልጣኑ ፈቃድ እስከመሰረዝ እርምጃ እንደሚወስድ” አስታውቋል። በአገር ውስጥ የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ይህንን ሕግ እና … [Read more...] about የኢሰመኮና የሪፖርተሩ ጎዶሎ ሪፖርት ብዙ ይነግረናል – አለ ገና!!