የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) ከትግራይ ክልል ወጥተው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በጦርነት መሳተፋቸውን ባወጣው መግለጫ አመለከተ።
ዩኤንኤችሲአር ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ የሚገኙና ድጋፍ የሚደረግላቸውን ስደተኞች የመረጃ ሁኔታን ከልሷል።
በዚሁ መሰረት በመጠለያ ጣቢያው ተመዝግበው የነበሩ ስደተኞች ቁጥር ከቅርብ ወራት ወዲህ መቀነሱንና በስደተኛነት ተመዝግበው የነበሩ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ይመለሱ ወይም የት ይሂዱ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ይፋ አድርጓል።
በግጭት ውስጥ የተሳተፈን ሰው በስደተኛነት የማይቀበለው ዩኤንኤችሲአር በስደተኛነት ተመዝግቦ በግጭት ውስጥ የተሳተፈ ማንኛውንም ሰው ዳግም እንደማይቀበል አድርጓል።
ከኢትዮጵያ ግጭት ሸሽተው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ተጠልለዋል የተባሉት ስደተኞች አብዛኛዎቹ ወጣቶች መሆናቸው ብዙውን ጊዜ በግጭት ምክንያት ለስደት ከሚዳረጉ ሕጻናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች ተቃራኒ መሆኑ አነጋጋሪ እንደነበር ይታወቃል።
ወጣቶቹ በአሸባሪው ሕወሓት የሰለጠኑ ታጣቂ ወጣቶች እንደሆኑና በማይካድራ ጭፍጨፋ የተሳተፉ “ሳምሪ” በሚል ስያሜ የሚታወቁ እንደነበሩ በተደጋጋሚ ተገልጿል።
እነዚህ ወጣቶች አሸባሪውን ቡድን የሚያደርገውን የሽብር ድርጊት ተቀላቅለው ለማገዝ ድንበር አቋርጠው ለመግባት ተደጋጋሚ ሙከራ አድርገው ሙከራቸው እንደከሸፈ ይታወሳል። (አሚኮ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply