የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ጭና ተክለሃይማኖት በነሃሴ 26ና 27 ሁለት ቀን ብቻ ከመቶ ሃያ በላይ ንጹሃንን መጭፍጨፉ ከአካባቢው መረጃ እየወጣ ይገኛል። ትህነግ ለምን ጭፍጨፋውን እንደፈጸመ መረጃዎቹ እስካሁን ዝርዝር አላቀረቡም። ይሁን የቀብር ስፍራዎችን በፎቶ ማስረጃ ይፋ እየሆኑ ሲሆን፤ በጅምላ የተጨፈጨፉት ወገኖች ማንነት እየተለየ መሆኑ ታውቋል። ትህነግ የአማራና የአፋር ክልልን ከወረረ በሁዋላ በርካታ የጅምላ ጭፍጨፋና የነብስ ወከፍ ግድያ መፈጸሙ ይፋ እየሆነ ነው። መረጃዎች መሰራጨት ከጀመሩ በሁዋላ ክልሉ የሚከተለውን በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በኩል ገልጿል። እንዳለ አቅርበነዋል። የጀግኖቻችንን የተቀናጀ ጥቃት ሲቀምስ፣ በየጫካው እየተፋለሙት ያሉትን ጀግኖችን መቋቋም ያልቻለው ወራሪ በየቤታቸው የነበሩ አዛውንቶችን፣ ህፃናትንና … [Read more...] about ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ መቶዎችን ጨፍጭፏል