የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ጭና ተክለሃይማኖት በነሃሴ 26ና 27 ሁለት ቀን ብቻ ከመቶ ሃያ በላይ ንጹሃንን መጭፍጨፉ ከአካባቢው መረጃ እየወጣ ይገኛል። ትህነግ ለምን ጭፍጨፋውን እንደፈጸመ መረጃዎቹ እስካሁን ዝርዝር አላቀረቡም። ይሁን የቀብር ስፍራዎችን በፎቶ ማስረጃ ይፋ እየሆኑ ሲሆን፤ በጅምላ የተጨፈጨፉት ወገኖች ማንነት እየተለየ መሆኑ ታውቋል። ትህነግ የአማራና የአፋር ክልልን ከወረረ በሁዋላ በርካታ የጅምላ ጭፍጨፋና የነብስ ወከፍ ግድያ መፈጸሙ ይፋ እየሆነ ነው።
መረጃዎች መሰራጨት ከጀመሩ በሁዋላ ክልሉ የሚከተለውን በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በኩል ገልጿል። እንዳለ አቅርበነዋል።
የጀግኖቻችንን የተቀናጀ ጥቃት ሲቀምስ፣ በየጫካው እየተፋለሙት ያሉትን ጀግኖችን መቋቋም ያልቻለው ወራሪ በየቤታቸው የነበሩ አዛውንቶችን፣ ህፃናትንና እናቶችን በያሉበት መንደርና ሰፈር በመግባት፣ ቀሳውስትን ቤተ ክርስትያን ውስጥ ገብቶ የፍጥኝ በማሰር ጨፍጭፏቸዋል።
የትግራይ ወራሪ ኃይል ቀደም ሲል በሰሜን ወሎ፣ በአፋር ክልል የፈፀመውን አይነት ዘግናኝ ጭፍጨፋ በሰሜን ጎንደር በዳባት ወረዳ በጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ በድጋሜ ፈፅሟል። ይህ ሰይጣናዊ ቡድን ከወረራቸው አካባቢዎች በአፋጣኝ ግብአተ መሬቱ እስካልተፈፀመ ድረስ ሌሎች ጭፍጨፋዎችን እንደሚፈፅም ግልፅ ነው።
በጥላቻ የናወዘውና ጭፈጨፋን የዕለት ተዕልት ተግባሩ ካደረገው የትግራይ ወራሪ አድማስ የነካ በደል፣ ሰቆቃና የግፍ ፅዋ ሕዝባችንን ለመታደገ ፍጥነታችንን ጨምረን ማርሻችንን ቀይረን ከያለበት ግብአተ መሬረቱን በመፈፀም ሕዝባችን ልንታደግ ይገባል።
ሚዲያዎቻችንም ይሄንን እውነት ዓለም እንዲያውቀውና ከወራሪውና ጨፍጫፊው ጋር በምናደርገው ትግል አብረውን እንዲቆሙና ድርጊቱንም እንዲያወግዙት በፍጥነት መዘገብና ቦታው ድረስ በመሄድም ሁኔታውን ማስረዳት ይገባናል።
በንፁሀን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የትግራይን ወራሪ ኃይል ግብአተ መሬቱን በማፋጠንና ለሕዝባችን ዳግም ስጋት እንዳይሆን በማድረግ ደማቸውን እንደምንመልስ ጥርጥር የለውም። የትግራይን ወራሪ ኃይል ከየገባበት እየመታን ባለንበት ወቅት የቤተሰብና የወገንን ሀዘን የምንጠግነው በትግራይ ወራሪ ኃይል መቃብር ላይ ይሆናል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply