አራቱ የጋሽ ኑር ልጆች እኛ እያለን ሀገር አትፈርስም ብለው ብርሸለቆ ማሰልጠኛ ገብተው ወታደራዊ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ፤ ወንድማማቾቹ ቃሲም ኑር፣ ኤዳሶ ኑር፣ ታጁ ኑር እና ዘይኑ ኑር ይባላሉ። አራቱ ወንድማማቾች ጁንታው ሀገር ሊበትን ቢያስብም እኛ የኢትዮጵያ ልጆች እያለን ይህ እንዴት ይሆናል ብለው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድነት መዝመት እንዳለባቸው ተነጋግረውና መክረው ስልጠናቸውን በሚገባ እየተከታተሉ እንደሚገኙ በሥፍራው ለሚገኙት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች ነግረዋቸዋል። አባታቸው ጋሽ ኑር 11 ወንድ ልጆች እና 6 ሴት ልጆች አሏቸው። ወደማሰልጠኛው የገቡት አራቱ ወንድማማቾች "አባታችን በሀገር ፍቅር ስሜት እና ወኔ ነው አንጾ ያሳደገን። በዚህም ምክንያት አገር ጥሪ ስታቀርብ መርቆና በአባገዳዎች አስመርቆ ሸኝቶናል" ነው ያሉት ሰልጣኞቹ … [Read more...] about አራቱ ወንድማማች የኢትዮጵያ ዘማቾች
ethiopian defesne force
ከወልዲያ አምልጦ የመጣው የትህነግ ኃይል እንዳይመለስ ተደረገ
በአማራ ክልል ሰርጎ የገባውን የአሸባሪውን ህወሓት ሀይል በመደምሰስ ላይ መሆኑን በሰሜን ወሎ ግንባር የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊቱ ክፍል አስታወቋል ። ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ዋድላ ወረዳ ፣ ኮን ከተማ እንዲሁም በጋሸና አካባቢ የሚገኘውን የአሸባሪው የህወሓት ቡድን በመምታት አኩሪ የጀግንነት ተግባር መፈጸሙን አዛዡ አረጋግጠዋል። ጀግኖቹ የሰራዊት አባላት በአካባቢው የሚገኝ የጠላት ፣ የሰውና የመሳሪያ ሀይል በየትኛውም አቅጣጫ እንዳይወጣ በማድረግና በመደምሰስ ከዋድላ ወረዳ እስከ ጋሸና ከተማ በመቆጣጠር ድል መቀዳጀታቸውን አመልክተዋል ። ሠራዊቱ ከወልዲያ አምልጦ የመጣውን ጠላት በመከታተል ፣ በዋድላ ወረዳና አካባቢ የመሸገውን የጠላት ሀይል እና መሳሪያ በመደምሰስ ጋሸና ከተማን መቆጣጠሩን የመከላከያ ሠራዊት አስታውቋል። (ኢብኮ-ፎቶ ማርቆሥ አለሙ) ጎልጉል … [Read more...] about ከወልዲያ አምልጦ የመጣው የትህነግ ኃይል እንዳይመለስ ተደረገ
ኢትዮጵያ “failed state” አይደለችም – የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት
የም/ቤቱ አባላት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ነፃነት እና የግዛት አንድነት ያላቸውን ጠንካራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በክልሉ ላለው ቀውስ እልባት ለመስጠት የኢትዮጵያ መንግስት እያከናወነ ያለውን ተግባር አድንቋል፡፡ መግለጫው እንደሚለው፣ የፀጥታው ም/ቤት አባላት የኢትዮጵያ መንግሥት ሰብዓዊ ዕርዳታን ለማቅረብ እና ሰብዓዊ ተደራሽነትን ከፍ ለማድረግ እያደረገ ላለው ጥረት እውቅና ሰጥተዋል፡፡ ይሁንና የም/ቤቱ አባላት የሰብዓዊ ችግሮች አሁንም መኖራቸውን እንደሚገነዘቡ እና በክልሉ ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸውም ነው መግለጫው ያመለከተው፡፡ ከምግብ ዋስትና ጋር በተያያዘም የሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ መጨመር እንዳለበት እና ያልተገደበ የሰብዓዊ … [Read more...] about ኢትዮጵያ “failed state” አይደለችም – የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት
መከላከያ ፈጣን ምላሽ የሚሰጡ ሁለት ዕዞች አቋቋመ
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት የሚሰጡኝን ግዳጆች በፍጥነት ማከናወን ያስችሉኛል ያላቸውን ተጨማሪ ሁለት ዕዞች ማደራጀቱን ትላንት አስታውቋል። አዲሶቹ ዕዞች በዚህ ዓመት ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል። ዕዞቹ በውስጥም በውጭም የሚቃጡ ጥቃቶችና ችግሮችን ፈጥነው ለመከላከል እንዲችሉ ታስቦ የተደራጁ እንደሆኑ ተገልጿል። ማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ አዲስ የተደራጁት ዕዞች ሲሆኑ የቀደሙት ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዕዞች መኖራቸው ይታወቃል። ዕዞቹ አዲስ አበባና ባሕር ዳር ላይ እንደሚደራጁ ሁለቱ ጄኔራሎች በመግለጫቸው አስታውቀዋል። (ኢዜአ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about መከላከያ ፈጣን ምላሽ የሚሰጡ ሁለት ዕዞች አቋቋመ
የመከላከያ ሠራዊት በቤንሻንጉል አካባቢ ታጣቂዎች ላይ የመደምሰስ እርምጃ መውሰድ ጀመረ
የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ግድያ በፈጸሙ ጥፋተኞች ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋግጥ አሳስቧል የመከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ በአካባቢው ግድያና ጥቃት በፈጸሙ ማንነታቸው በግልጽ ያልተነገረ ታጣቂዎችን የመደምሰስ ዕርምጃ መውሰድ መጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን፣ ጥቃት በተሰነዘረባቸው አካባቢዎች ላይም 150 ኪሎ ሜትር የሸፈነ ስምሪት ማድረጉንም ገልጿል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከዚህ ቀደም ለተደጋጋሚ ጊዜ እንዲሁም ሰሞኑን በነዋሪዎች ላይ በተቃጣው ግድያና ጥቃት ሥጋት ውስጥ የወደቁ የአካባቢው ነዋሪዎች መንግሥት ደኅንነታቸውን በዘላቂነት እንዲያስጠብቅላቸው ጠየቁ። ነዋሪዎቹ ጥያቄያቸውን ያቀረቡት የሰሞኑን ግድያና ጥቃት ተከትሎ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን የተመራ የፌዴራልና የክልል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ቡድን ባለፈው ዓርብ መስከረም 8 ቀን … [Read more...] about የመከላከያ ሠራዊት በቤንሻንጉል አካባቢ ታጣቂዎች ላይ የመደምሰስ እርምጃ መውሰድ ጀመረ