የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት የሚሰጡኝን ግዳጆች በፍጥነት ማከናወን ያስችሉኛል ያላቸውን ተጨማሪ ሁለት ዕዞች ማደራጀቱን ትላንት አስታውቋል።
አዲሶቹ ዕዞች በዚህ ዓመት ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል።
ዕዞቹ በውስጥም በውጭም የሚቃጡ ጥቃቶችና ችግሮችን ፈጥነው ለመከላከል እንዲችሉ ታስቦ የተደራጁ እንደሆኑ ተገልጿል።
ማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ አዲስ የተደራጁት ዕዞች ሲሆኑ የቀደሙት ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዕዞች መኖራቸው ይታወቃል።
ዕዞቹ አዲስ አበባና ባሕር ዳር ላይ እንደሚደራጁ ሁለቱ ጄኔራሎች በመግለጫቸው አስታውቀዋል። (ኢዜአ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Mulugeta Andargie says
ተመልከት፥ እይ፥ ህዝባችን ሲኮራ
መች ወሬ፥ መች ጉራ
ሊያቅራራ?
ፉከራ?
የተግባር፥ ይዕውን ልሳን፥ ይልቅ ድርሳን
እንጂ፥ ዳሩ ላህያ ማር ኣይጥማት ዕውን?
በዕኩልነት ፈርጅ፥ ልባችን ደንድኖ ልናጤን
ማንን ፈርተይ?
የልብ ልብ ኣለን!!
ኮርተን!!ኮርተን!!
የህዝብ ኣለኝታችን!!
Tewodros says
አዎ ወቅታዊውን ሁኔታ ያገናዘበ አደረጃጀት መፍጠር ከመከላከያ የሚጠበቅ ነው። ይህን የሚቃወሙ አልጠፉም። ግን ይደረጋል። ለምሳሌ ባህርዳር ላይ የነበረው የምዕራብ ዕዝ ባለፈው ዓመት ወደ ሌላ ቦታ እንዲዘዋር መደረጉ መታወስ አለበት።