• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የመከላከያ ሠራዊት በቤንሻንጉል አካባቢ ታጣቂዎች ላይ የመደምሰስ እርምጃ መውሰድ ጀመረ

September 22, 2020 01:59 am by Editor Leave a Comment

የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ግድያ በፈጸሙ ጥፋተኞች ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋግጥ አሳስቧል

የመከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ በአካባቢው ግድያና ጥቃት በፈጸሙ ማንነታቸው በግልጽ ያልተነገረ ታጣቂዎችን የመደምሰስ ዕርምጃ መውሰድ መጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን፣ ጥቃት በተሰነዘረባቸው አካባቢዎች ላይም 150 ኪሎ ሜትር የሸፈነ ስምሪት ማድረጉንም ገልጿል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከዚህ ቀደም ለተደጋጋሚ ጊዜ እንዲሁም ሰሞኑን በነዋሪዎች ላይ በተቃጣው ግድያና ጥቃት ሥጋት ውስጥ የወደቁ የአካባቢው ነዋሪዎች መንግሥት ደኅንነታቸውን በዘላቂነት እንዲያስጠብቅላቸው ጠየቁ። 

ነዋሪዎቹ ጥያቄያቸውን ያቀረቡት የሰሞኑን ግድያና ጥቃት ተከትሎ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን የተመራ የፌዴራልና የክልል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ቡድን ባለፈው ዓርብ መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም. አካባቢውን ጎብኝቶ ነዋሪዎቹን ባነጋገረበት ወቅት ነው። 

በአካባቢው ጉብኝት በማድረግ ከነዋሪዎች ጋር የተወያዩት የመንግሥት ባለሥልጣናት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን፣ የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለምና ሌሎች የሁለቱ ክልሎችና የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የፀጥታ አመራሮች ናቸው። 

ከነዋሪዎቹ ጋር የተወያዩት ባለሥልጣናት በአካባቢው ዘላቂ ሰላምን የማስፈንና በአጥፊዎች ላይ አስፈላጊው ዕርምጃ የመውሰድ ተግባር እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል። 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ የፀጥታ መደፍረሶችንና በሰለማዊ ነዋሪዎች ላይ እያጋጠሙ ያሉ ጥቃቶችን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ መንግሥት በአካባቢው የነዋሪዎችን ደኅንነት ማረጋገጥ እንዳለበት አሳስቧል።

በተጠቀሰው አካባቢ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ጥቃቶች በተደጋጋሚ ማጋጠማቸውን የገለጸው ኮሚሽኑ፣ መንግሥት እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ጥቃት ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት ገለልተኛ፣ ፈጣንና ውጤታማ ምርመራዎችን በማካሄድ ጥቃትና ግድያውን በፈጸሙ ጥፋተኞች ላይ ተጠያቂነት እንዲያረጋግጥ አሳስቧል። 

ኮሚሽኑ በአካባቢው ከሚገኝ አንድ መንግሥታዊ ምንጭ አገኘሁት ባለው መረጃ ቢያንስ በሁለት ዙር በደረሱ ጥቃቶች ባልታጠቁ ሲቪሎች ላይ ግድያዎች መፈፀማቸውን እንዲሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን ማረጋገጥ እንደቻለ ገልጿል፡፡

ከክልሉ መንግሥት ባገኘው መረጃ በርካታ ነዋሪዎች በጥቃቱ ምክንያት መፈናቀላቸውንና ከጥቃቱ በኋላ ከተፈናቃዮቹ መካከል 300 ያህሉ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉን እንዳረጋገጠ፣ የአገር መከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር አካባቢውን ለማረጋጋት እየሠሩ ስለመሆኑ መረጃ ማግኘቱንም አስታውቋል። 

ኮሚሽኑ ሁሉም የፖለቲካ ቡድኖችና ባለድርሻ አካላት ገንቢ ውይይት እንዲያደርጉና ከማንኛውም ዓይነት የሁከት ድርጊቶች እንዲታቀቡ ጥሪውን ያቀረበ ሲሆን፣ ሁሉም አካላት ሕገ መንግሥቱንና ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለቻቸውን ሌሎች አግባብነት ያላቸውን የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ውስጥ የተቀመጡ መብቶችንና ግዴታዎችን እንዲያከብሩ ኮሚሽኑ ጠይቋል።  በቀጣይም ጉዳዩን በንቃት እንደሚከታተለው ገልጿል። (ዮሐንስ አንበርብር፤ ሪፖርተር)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News, Politics, Slider Tagged With: benshagul gumuz, ethiopian defesne force

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule