
በአማራ ክልል ሰርጎ የገባውን የአሸባሪውን ህወሓት ሀይል በመደምሰስ ላይ መሆኑን በሰሜን ወሎ ግንባር የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊቱ ክፍል አስታወቋል ።
ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ዋድላ ወረዳ ፣ ኮን ከተማ እንዲሁም በጋሸና አካባቢ የሚገኘውን የአሸባሪው የህወሓት ቡድን በመምታት አኩሪ የጀግንነት ተግባር መፈጸሙን አዛዡ አረጋግጠዋል።
ጀግኖቹ የሰራዊት አባላት በአካባቢው የሚገኝ የጠላት ፣ የሰውና የመሳሪያ ሀይል በየትኛውም አቅጣጫ እንዳይወጣ በማድረግና በመደምሰስ ከዋድላ ወረዳ እስከ ጋሸና ከተማ በመቆጣጠር ድል መቀዳጀታቸውን አመልክተዋል ።
ሠራዊቱ ከወልዲያ አምልጦ የመጣውን ጠላት በመከታተል ፣ በዋድላ ወረዳና አካባቢ የመሸገውን የጠላት ሀይል እና መሳሪያ በመደምሰስ ጋሸና ከተማን መቆጣጠሩን የመከላከያ ሠራዊት አስታውቋል። (ኢብኮ-ፎቶ ማርቆሥ አለሙ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply