• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮጵያ “failed state” አይደለችም – የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት

April 23, 2021 09:29 am by Editor 3 Comments

የም/ቤቱ አባላት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ነፃነት እና የግዛት አንድነት ያላቸውን ጠንካራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል

የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በክልሉ ላለው ቀውስ እልባት ለመስጠት የኢትዮጵያ መንግስት እያከናወነ ያለውን ተግባር አድንቋል፡፡

መግለጫው እንደሚለው፣ የፀጥታው ም/ቤት አባላት የኢትዮጵያ መንግሥት ሰብዓዊ ዕርዳታን ለማቅረብ እና ሰብዓዊ ተደራሽነትን ከፍ ለማድረግ እያደረገ ላለው ጥረት እውቅና ሰጥተዋል፡፡ ይሁንና የም/ቤቱ አባላት የሰብዓዊ ችግሮች አሁንም መኖራቸውን እንደሚገነዘቡ እና በክልሉ ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸውም ነው መግለጫው ያመለከተው፡፡

ከምግብ ዋስትና ጋር በተያያዘም የሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ መጨመር እንዳለበት እና ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ ለሁሉም የተቸገሩ ወገኖች ተደራሽ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

ከተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ አስቸኳይ እርዳታ መርሆዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ሰብዓዊነትን፣ ገለልተኛነትን እና ነፃነትን መሰረት በማድረግ የሚከናወኑ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶች እንዲቀጥሉ የፀጥታው ም/ቤት አባላት ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

በትግራይ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ለቀጣይ የሰብአዊ አገልግሎቶች እንቅፋት መሆኑን በመግለጽ መደበኛ ሁኔታው እንዲመለስም አባላቱ መጠየቃቸው በመግለጫው ተካቷል ፡፡

በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ የፆታ ጥቃት እንደሚፈጸም የሚያመለክቱ ሪፖርቶችን ጨምሮ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና በደሎች ላይ የተሰማቸውን ጥልቅ ስጋት በመግለፅ፣ ምርመራ ተደርጎ ጥፋተኞች ለህግ እንዲቀርቡም ነው የፀጥታው ም/ቤት አባላት የጠየቁት፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና በደሎች ላይ የሚያካሂዱትን የጋራ ምርመራ በአድናቆት ተቀብለዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተሳትፎም የፀጥታው ም/ቤት አባላት በአድናቆት መቀበላቸው ተገልጿል፡፡

ዓለም አቀፍ ህግን ሙሉ በሙሉ ማክበር አስፈላጊ መሆኑንም አባላቱ አሳስበዋል ፡፡

የም/ቤቱ አባላት ለአህጉራዊ እና ለክፍለ-አህጉራዊ ጥረቶች እና ድርጅቶች ማለትም ለአፍሪካ ህብረት እና ለኢጋድ ያላቸውን ጠንካራ ድጋፍ የገለጹ ሲሆን የድርጅቶቹ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስምረውበታል፡፡

የፀጥታው ም/ቤት አባላት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ነፃነት፣ የግዛት እና ሀገራዊ አንድነት ያላቸውን ጠንካራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡ (አል-ዐይን)

ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ጎልጉል ያነጋገራቸውና ለጉዳዩ ቅርብት ያላቸው የዲፕሎማሲ ኤክስፐርት እንዳሉት ይህ የጸጥታው ምክር ቤት ወሳኔ በዲፕሎማሲ አነጋገር ኢትዮጵያ “failed state” አይደለችም፤ መንግሥት ያለባት አገር ነች፤ የግዛቷ ልዕልና እናከብራልን፤ የድንበሯን ወሰን እናከብራልን፤ ሰላም አስከባሪ ኃይል አንልክም፤ የራሷን ችግር መወጣት የሚችል ብቃት ያለው መንግሥት ያለባት አገር መሆኑን አረጋግጠናል የሚል መግለጫ ነው ብለዋል።

ይህ የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ያነሳሳውና በቴድሮስ አድሃኖም፣ በብርሃነ ገብረክርስቶስ እንዲሁም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከእነርሱ ጋር በማበር ኢትዮጵያ መንግሥት የሌለባት አገር (failed state) ነች ሲሉ ለነበሩ ሚዲያ ላይ ሲደሰኩሩ እና ጋዜጣዊ መግለጫና ሲሰጡ ለነበሩ ቅስም ሰባሪ፣ አንገት አስደፊ ውሳኔ ሆኖ መገኘቱ በሥፋት እየተወራበት ያለ ዜና ሆኗል። (ፎቶ፤ ከቀድሞ የUNSMIL ክምችት)

UN Security Council reaffirms commitment to Ethiopia’s sovereignty, political independence and unity

The UN Security Council member countries reaffirms commitment to Ethiopia’s sovereignty, political independence and unity. And acknowledged the efforts by the Government of Ethiopia to provide humanitarian assistance and to provide increased humanitarian access.

Security Council Press Statement on Ethiopia

The following Security Council press statement was issued today by Council President Dinh Quy Dang (Viet Nam):

The members of the Security Council noted with concern the humanitarian situation in the Tigray region, Ethiopia.

The members of the Security Council acknowledged the efforts by the Government of Ethiopia to provide humanitarian assistance and to provide increased humanitarian access.  The members of the Security Council recognized, nevertheless, that humanitarian challenges remain.  They called for a scaled-up humanitarian response and unfettered humanitarian access to all people in need, including in the context of the food security situation.

The members of the Security Council called for a continuation of international relief efforts in a manner consistent with the United Nations guiding principles of humanitarian emergency assistance, including humanity, neutrality, impartiality and independence.  The members of the Security Council noted that insecurity in Tigray constitutes an impediment to the ongoing humanitarian operations and called for a restoration of normalcy.

The members of the Security Council expressed their deep concern about allegations of human rights violations and abuses, including reports of sexual violence against women and girls in the Tigray region and called for investigations to find those responsible and bring them to justice. They welcomed the joint investigation by the Office of the United Nations High Commissioner for Human Rights (OHCHR) and the Ethiopian Human Rights Commission into alleged human rights violations and abuses.  The members of the Security Council also welcomed the engagement on this issue of the African Commission on Human and People’s Rights.

The members of the Security Council stressed the need for full compliance with international law.

The members of the Security Council reiterated their strong support to regional and subregional efforts and organizations, namely the African Union and the Intergovernmental Authority on Development (IGAD), and underscored the importance of their continued engagement.

The members of the Security Council reaffirmed their strong commitment to the sovereignty, political independence, territorial integrity and unity of Ethiopia.

Read the original press release here

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, News Tagged With: ethiopian defesne force, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Comments

  1. ነፃ ሕዝብ says

    April 23, 2021 11:06 am at 11:06 am

    ድንቄም ሶሻሊዝም ነበር ያሉት እማማ ዝናሽ ! የሰው ልጅ በየሰዓቱ እንደ ከብት የሚታረድባት የደም መሬት ሀገር ሆናለች ፥ ከመጋቢት ወር 2010 ዓ/ም ጀምሮ ዜጎች እንደ ቅጠል እየረገፉባት የምትገኝ ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ነች ፡፡

    Reply
  2. Gi Haile says

    April 24, 2021 09:38 pm at 9:38 pm

    That is fair, and for the first time the Ethiopian.Goveenment. fairly Judged by UNSC. That is balanced and fair Judgement. Thank you UNSC.

    Reply
  3. Tesfa says

    April 26, 2021 11:45 am at 11:45 am

    ደሮን ሲደልሏት በመጫኛ ጣሏት ይሉ የለ አበው። የሃበሻው ምድር የመከራ ዝናብ በህዝቡ ላይ ማዝነብ ከጀመረ እልፍ ጊዜ አልፏል። ዝም ብሎ የምጽድቅ ፓለቲካ ከእውነት ጋር አይታረቅምና ማስተዋል አስፈላጊ ነው። ለመሆኑ አንድ ሃገር ፈረሰ የሚባለው መቼ ነው? አጉል የ 3 ሺ ዘመን ያላት ሃገር፤ የክርስቲያን ደሴት እያሉ ራስን ማንቆለጳጰስ ውስልትና ነው። ሃበሻ የክፋት ጆኒያ ነው። የዛሬውን ክፍት ካለፈው መከራ ጋራ በማስተያየት መለስ ብሎ ሲደረጉ የነበሩ ተግባሮችን መመልከት ያስፈልጋል። በ1967 ዓ. ም በጅማ በግፍ ለተገደለ መምህር አዲስ አበባ ላይ የተገኘ አንድ ሌላ መምህር የሟች እናት፤ አባቱ፤ ህጻን ያዘለች ሚስቱ፤ ጓደኛና ዘመዶቹ በእንባ እየታጠቡ ሲቀብሩት እንዲህ ብሎ ነበር። ወገኖቼ አስተውሉ የማችን ስም በመጥራት እናንተም ሆነ እርሱ እድለኛ ናችሁ። የራሳችን መቃብር ቆፍረን የምንቀበርበት ጊዜ ይመጣል በማለት ተንግሮ ነበር። ብዙም ሳይቆይ ከጅማ ተጋፈው እሱና ጓደኞቹ አዲስ አበባ ተወስደው የራሳቸውን ጉድጓድ ቆፍረው ነበር በጥይት ተደብድበው የተገደሉት። ይህ ወሽካታ ባንዲራ አምላኪና በነጭ የኳስ ፈንጠዚያ እንባ የሚያፈስ የሙት ትውልድ ወገኑ ከአጠገቡ እየወደቀ እኔን ብሎ ከመርዳት ይልቅ ኪስ አውላቂ ከሆነ ቆይቷል። የአሁኗም ሆነች የበፊቷ ኢትዮጵያ ሰላም ያጡ፤ ህዝብ የሚያሸብሩ ጠበንጃ ታጣቂዎች የሚንጋጉባት ምድር ነበረች አሁንም ናት ወደፊትም ይቀጥላል። ሌላ መረጃ ላቅርብ ደርግ በስልጣን ሰክሮ የምርት ካድሬ የሚባሉ አስለጥኖ በየስፍራው ይበትናል። ደጀን ላይ የማይረሳ ነገር በዚያ ዘመን ተፈጸመ። ሰው ይበላል ይጠጣል እና በማህል አንድ ጎረምሳና አንድ የምርት ካድሬ ይጣላሉ። የምርት ካድሬው ልጅን ገፍትሮ ይጥልና ጥይት አቀባብሎ ሊመታው ሲሉ እህቱ ከወደቀው ወንድሟ ላይ ትዘረራለች። ሁለቱንም ይገድላቸዋል። የምድሪቱ ግፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ እያለ እንጂ እየተሻለው አልመጣም። አሁን ወያኔ በዘር፤ በቋንቋ፤ በክልል የከፋፈላትና ዶ/ር አብይ በኦሮሞ ስም የተቀበላት ሃገር ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ የሚሏት አይነት ናት። ለዚህ እዚህ ላይ ማስረጃ አላቀርብም። የየጊዜው የፈጠራም ሆነ እውነት ላይ የተመረኮዘ የሃገርና የውጭ የዜና አውታሮች የሚያራግቡት ጉዳይ በመሆኑ ያንኑ አንብቡ። ባጭሩ ሃገሪቱ ቀረርቶ የበዛባት፤ ትላንት ያለቀሱ አይኖች ዛሬም የሚያለቅሱባት፤ ግፈኞች በሰው ሞት ተሰባስበው የሚዘፍኑባት የግፍ ሃገር ናት። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ጣሊያን በሁለቱ የወረራ ሙከራው ያልፈጸመውን በደል የፈጸመ የዘር የፓለቲካ ስብስብ ነው። ወያኔ የቀበረውና በመቅበር ላይ ያለው ነባርና አዳዲስ እሳቶች ናቸው አሁን ምሪቱን ምጥ ውስጥ የከተቷት። የሚያስገርመው የወያኔ ደጋፊዎች ከባህር ማዶ ያሉ ሃበሾችንም ማጥቃታቸው ነው። በደቦ ይደባደባሉ፤ የንግድ ቤቶችን ይሰብራሉ፤ ያቃጥላሉ፤ ስልክና ኢሜል በመላክ ሰውን ያስፈራራሉ እንዲህ ካሉ የውሻ ፓለቲካ ከሚከተሉ ጋር እንዴት ነው ሃገር ሃገር ሆኖ የሚቆመው? ምን የወያኔ ደጋፊዎች ብቻ ሌላውም በየጎጡ ሃገር መስርቶ አጥር ባጠረባት ምድር ላይ አብሮ መኖር እንዴት ይሆናል? የማይሆን ነገር ለሚስትህ አትንገር። እንዴት ባለ ሂሳብስ ነው 500 ሺህ ህዝብ በላይ ሜዳ ላይ የፈሰሰባት ሃገር አትፈርስም የሚባለው? አዲስ አበባ ራሱ ወጥቶ በሰላም መግባት የማይቻልባት ከተማ ሆናለች። ዝርፊያው፤ ግድያው፤ አፈናው ስንቱ ይወራል? አፍሪቃ ከናጄሪያ እስከ ካሜሩን ከቻድ እስከ ሱማሊያ ፍርክርኩ የወጣ ገናም የሚወጣ አህጉር ነው። ዛሬ በሞዛቢክ የምናየው የጨካኞችን ሥራ ነው። ራስን በራስ ማፍረስ እንዲህ ነው።
    ተመድ የሥራ ፈቶች ስብስብ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ የፈረሰች/ወይም የምትፈርስ ሃገር አይደለችም ቢሉም ውስጥ ውስጡን እንደ ምስጥ የሚሰሩት ሥራ መፍረሷን የሚሻ ነው። እልፍ ብድር ለሃገሪቱ መፍቀዳቸው ራሱ በዋናነት ተጠቃሽ ነው። አሁን ለወያኔ የአዞ እምባ የሚያነቡት በዚሁ ስብስብ ውስጥ ያሉ ሃይሎች አይደሉምን? የተራበው የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው? ግን ከፋፍለህ ለአንድ እሳት ለሌላው ነዳጅ መስጠት የተካኑበት የሴራ ፓለቲካ ነው።
    ባጭሩ ኢትዮጵያ በመፍረስ ላይ ያለች ሃገር ናት። ፍትህ በምድሪቱ አልነበረም፤ ዛሬም የለም። ወደፊትም አይኖርም። አሁን እስር ቤት ያለው አቶ በቀለ ገርባ ትግራይ ላይ በተደረገ ስብሰባ ሲናገር “የእኔ ምርጫ በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፌዴራሊዝም ነው” ወቸው ጉድ አታድርስ ነው። የተማረ ወይም ተምሬአለሁ ያሉ የሚያፈርሷት ሃገር። ስለዚህ ተመድ ይህን አለ ያን አላለ ምንም ፋይዳ የለውም። በተጨባጭ በሃገሪቱ ውስጥ በየቀኑ የሚታዪ ዘግናኝና አፍራሽ ስራዎች ግን የወደፊቱን የሃገሪቱን እድል ፈንታ ያመላክታሉ። ፈረሰችም/ነቃችም/ተደረመሰችም ሚዛኑ በምድሪቱ ላይ በአራቱም የሃገሪቱ ማእዘን ይታያልና አይን ያለው ይመልከት፤ ጆሮ ያለው ይስማ። ሌላው ሁሉ የነጭ ለባሽ ወሬ ነው። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am
  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule