- ደብረ ፅዮን ተከቦ ለማዳን እኮ አግአዚ እና ሃውዜን የተባሉ ሁለት ክፍለ ጦር ይበሉ ወጣቶች (ይለቁ) ተብሎ አልቀው የተረፍነው ተርፈን መስዋእት ሆነዋል። ከመቼው ረሳችሁት እረሱት? ደብረጺዮንን ብቻም አይደለም ሌሎችም አመራሮችን ለማዳን ተብሎ እኮ ብዙ መስዋእት ተከፍለዋል። ወጣት አልቋል! አሁን የትግራይ እናት በረንዳ አደር ሁናለች። በየቤታችን ያለዉ ጉድ አቅፈን ይዘን ዝም ብለን ኖረናል። እዚህ ያላቹ አመራሮች ጭምር ጆሮ ዳባ እንደሆናቹ እናዉቃለን ጨንቆን እንጂ።
- ሰልፍ ስንወጣ እኮ ለጠላት አመቺ መሆኑ ሳይገባን ቀርቶ አደለም መፍትሄ ስናጣ ነዉ። ለምሳሌ እኔ ሙሉ ሰዉነቴ ኦፕሬሽን ብቻ ነዉ ሂወት አለኝ ብዪ አላስብም። ረሳችሁን በ2013 አብረን እኮ ብዙ ችግር አሳልፈን ነበር አሁን የመኪና ሰርቪስ አገልግሎት እንኳን እየገፈተራቹ እና በማስክ ነዉ ምታልፉ። የ18 አመት ልጆች የሞቱ ጓዶች መርዶ ሳይነገር ነዉ እናንተ ፌስታ ላይ ያላቹ። እናዉቃለን በየመዝናኛ ቤቶች እንደምትዉሉ እና ምታድሩ። የ15 ብር ጫማ መሸወጃ እየገዛቹ አትዘልቁትም። አሁንም ሁኔታዉ ገና ነዉ የሚመስለዉ ነገር ግን ከአሁን በኋላ ሞኛቹ ፈልጉ ለማን ብለን እንዋጋለን። ተዋረድን ተረሳን በቁማችን እያየን አይናቸዉ የጠፉ ጓዶች መሪ አልባ እየሆኑከግድግዳ ጋ እየተጋጩ ነዉ የሚዉሉት።
- በ2013 ዓ.ም ሃምሌ 24 ቀን ሻምበል ኪሮስ የተባለን የአህፈሮም ክ/ጦር ወታደራዊ አመራር ከከበባ ለማውጣት አንድ ክፍለጦር ኮማንዶ መስዋዕትነትን ከፍሏል።
- በኩንታሎች የታጨቀ ብር ተሸክመን ስንከተላችሁ እንደነበር አትክዱም (ደሴ ውስጥ ብቻ በወያኔ ጄኔራሎች የተዘረፈውን ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ያስታውሷል)። ኮሎኔል መብራህቱ ….. አንተ ትመራው በነበረ ሃይል ውስጥ ለነበርነው አባላት ለመረጃ ብላችሁ ወደ ብር እንደወሰዳችሁን ትዝ አይልህም?
ትርጉም፤ በአስፋው አብርሃ
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply