“አመጽ ሁሉ መመራት ያለበት ለበቀል ባለህ ጥማት ሳይሆን፤ ለፍትሕ ባለህ ከፍተኛ ፍላጎት መሆኑ እጅግ አስፈላጊ ነው” ደራሲ አብሂጂት ናስካር 1. ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ። በቅርብ ዓመታት ለምዕራባውያን መንግሥታት የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ ያስተላለፈው መልዕክት "ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ" የሚል ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ መብትና ድምጽ በረገጠ እቡይ መንፈስ፤ ዶ/ር ዮናስና አጋሮቻቸው፤ ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ፤ ደጅ ጥናት ላይ ናቸው። ይህ ዓይነት እኩይ መንንፈስ፤ እንኳን ትላንት ወደ ፖለቲካው መድረክ አንገታቸውን ብቅ ላደረጉ ይቅርና፤ ከ40 ዓመታታ በላይ በምዕራባውያን ጉያ ውስጥ የነበረውና የኢትዮጵያን ጥቅም ለምዕራባውያን አሳልፎ ለሸጠው ለሕወሃትም አልበጀም። ገራሚው ነገር፤ ከዓመት ተኩል በፊት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍቅር ታመው … [Read more...] about “አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት)
dawit woldegiorgis
“አንድ ሰው ለመግደል ሕንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት (ክፍል 1)
የኢትዮጵያ ሕዝብ እራሱ በመረጠው መንግሥት እንዲተዳደር ይነሳ የነበረው ጥያቄ፤ ከ50 ዓመታት በላይ በተደረገ ትግልና በተከፈለ ከፍተኛ መስዋዕትነት በሰኔ 2013 ምላሽ አግኝቷል። ምንም እንኳን ምርጫው አንዳንድ መሰናክሎች ቢያጋጥሙትም፤ ገለልተኛና ተአማኒ በሆነ የምርጫ ቦርድ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመንግሥት ሥልጣን ምርጫ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው ነው። ይህ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብና በበርካታ ሃገራዊና አለም አቀፍ ተቋማት ፍትሃዊና ሚዛናዊ ምርጫ ነው ቢባልም፤ ይህ መንግሥት በሕዝብ የተመረጠ አይደለም የሚሉ ግን አልጠፉም። የሕወኃት መራሹ መንግሥት ተወግዶ ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ፤ ከሕዝብ ያገኙት ድጋፍ በሃገራችን ታይቶ የማይታወቅ ድጋፍ ነበር። በጊዜ ሂደት ግን፤ … [Read more...] about “አንድ ሰው ለመግደል ሕንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት (ክፍል 1)
የ”ከሃዲው” ዳዊት የሌብነት መረጃ
ባለፈው ሳምንት "ከሃዲው ዳዊት ወልደጊዮርጊስን" አስመልክቶ "ዳዊት ወልደጊዮርጊስ – የጸረ ኢትዮጵያዊነት መገለጫ" በሚል እርዕስ ዜና ማቅረባችን ይታወሳል። በዜናው ግንባር የተጠቀሰው ሳይጀመር በከሸፈው "የሽግግር መንግሥት" ማመልከቻ ጉዳይ ነበር። ያተምነውን ዜና ተከትሎ አቶ ለማ መገርሳ "ተውኝ። ልኑርበት" ሲሉ ስለጉዳዩ ምንም እንደማያውቁ በይፋ መናገራቸው፣ ፕሮፌሰር ተዘራ ዳዊት የሤራው ስብስብ አገር ለመርዳት መስሏቸው ከገቡ በኋላ ሲያዩት ሃያ ሰባት ዓመታት ኢትዮጵያን ሲዘርፍና ሲያደማ የኖረውን ትህነግን ወደ ስልጣን ለመመለስ እንደሆነ ሲረዱ ራሳቸውን ማግለላቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ራሱ አስተባባሪውም "የለሁበትም" ሲል ዳግም ክህደቱን አሳይቷል። በዚህ ዜና ላይ ዳዊት ከሃዲና ዘራፊ መሆኑን ለማሳየት ከረሃብ ሰለባዎች ጉሮሮ መንትፎ አገር ስለመክዳቱ መግለጻችን ከተራ … [Read more...] about የ”ከሃዲው” ዳዊት የሌብነት መረጃ
ዳዊት ወልደጊዮርጊስ – የጸረ ኢትዮጵያዊነት መገለጫ
ዳዊት ወልደጊዮርጊስ እሱን የመሰሉትን ከየዓይነቱ ሰብስቦ በጀመረው ዘመቻ የሽግግር መንግሥት ሰነድ ነድፎ የሞተውን ትህነግን አዝሎ እየሮጠ እንደሆነ አስቀድሞ የተገለጸ ቢሆንም ዛሬ ላይ ግን እሱና ራሱን በሚከረፉ ቃላት አደባባይ መላው ኢትዮጵያ ህዝብ ፊት ካዋረደው ታምራት ላይኔ የሚደግፏቸው ሚዲያዎች አማካይነት ይህንኑ የሽግግር መንግሥት አዋጅ ልክ ነገ እንደሚተገበር አድርጎ እያሳወጃቸው ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ተሞክረው ከከሸፉ በርካታ መልካም አጋጣሚዎች ጀርባ ስሙ የሚነሳው ሰላዩ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ደጋፊ ለማሰባሰብ ሲል እሱና ታምራት ላይኔ፣ እንዲሁም በመረጃ ቲቪ ባለቤቶች ስፖንሰር አድራጊነት የአሜሪካ መንግሥት ዕውቅና እንዳለው አድርጎ የሚዲያ ማስታወቂያ ያሰራበት ዕቅድ ሰነድ ለአሜሪካ መንግሥት ከመድረሱ በፊት ሙሉ ዶሴው መንግሥት እጅ መግባቱን የጎልጉል ተባባሪ ዘጋቢያችን … [Read more...] about ዳዊት ወልደጊዮርጊስ – የጸረ ኢትዮጵያዊነት መገለጫ