• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዳዊት ወልደጊዮርጊስ – የጸረ ኢትዮጵያዊነት መገለጫ

July 26, 2021 02:57 am by Editor 7 Comments

ዳዊት ወልደጊዮርጊስ እሱን የመሰሉትን ከየዓይነቱ ሰብስቦ በጀመረው ዘመቻ የሽግግር መንግሥት ሰነድ ነድፎ የሞተውን ትህነግን አዝሎ እየሮጠ እንደሆነ አስቀድሞ የተገለጸ ቢሆንም ዛሬ ላይ ግን እሱና ራሱን በሚከረፉ ቃላት አደባባይ መላው ኢትዮጵያ ህዝብ ፊት ካዋረደው ታምራት ላይኔ የሚደግፏቸው ሚዲያዎች አማካይነት ይህንኑ የሽግግር መንግሥት አዋጅ ልክ ነገ እንደሚተገበር አድርጎ እያሳወጃቸው ነው።

በኢትዮጵያ ውስጥ ተሞክረው ከከሸፉ በርካታ መልካም አጋጣሚዎች ጀርባ ስሙ የሚነሳው ሰላዩ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ደጋፊ ለማሰባሰብ ሲል እሱና ታምራት ላይኔ፣ እንዲሁም በመረጃ ቲቪ ባለቤቶች ስፖንሰር አድራጊነት የአሜሪካ መንግሥት ዕውቅና እንዳለው አድርጎ የሚዲያ ማስታወቂያ ያሰራበት ዕቅድ ሰነድ ለአሜሪካ መንግሥት ከመድረሱ በፊት ሙሉ ዶሴው መንግሥት እጅ መግባቱን የጎልጉል ተባባሪ ዘጋቢያችን ከዲሲ አረጋግጧል።   

“ከሃጂና አስገዳይ” የሚል ስም የተሰጠው ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ተዋናይ የሆነበት የመፈንቅለ መንግሥት ንድፈ ሃሳብ “ልዩነት ቢኖርም አገር ቢቀደም ይሻላል” በሚሉ የራሱ ምልምሎች ዕርቃኑን ከወጣ በኋላ አሜሪካ ተለዋጭ ዕቅዷ አልታወቀም። በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በዚህ ከሃዲ ዕቅድ ውስጥ ስማቸው የተነሳ ሰዎች ሚዲያው ባልተሰጣቸውና ባላገኙት “ክብር” ዜናውን ቢያሯሩጠውም እውነታው ሌላ እንደሆነ መረጃ ለጎልጉል ደርሷል። 

በአብዛኛው አሁን ተዘጋጀ በሚባለው የከሸፈው የ”ተተኪ መንግሥት” ውስጥ ባብዛኛው ስማቸው የተካተተው እንደ ቤት ጥራጊ ቆሻሻ አገርና ህዝብ “እንትፍ” ብሎ የጣላቸው መሆናቸው በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ “እንዴት ሊሆን ይችላል?” የሚል ጥያቄ አስነስቶ ከርሟል።

ለግንዛቤ

የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አገዛዝ በደርግ በተወገደ ጊዜ በትምህርት ውጭ አገር የነበረው ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በራሱ አንደበት ሲናገር እንደተሰማው (የፒኤችዲ) ትምህርቱን አቋርጦ ወደ አገር ቤት መጣ። እርሱ እንደሚለው ትግሉን ለመቀላቀል ቢሆንም ዋናው ዓላማ ግን በደርግ ውስጥ በመግባት ለምዕራባዊ ኃይሎች ለመሰለል እንደሆነ የበኋላ ሥራው ይናገራል። እርሱ እራሱም ቢሆን ይህንን የሁለት ቢላዋ ጨዋታ ሊያስተባብል አይችልም። እንዲያውም በአንዳንድ ቃለመጠይቆች ሞቅ ሲለው እየዘላበደ እምነቱን ሰጥቷል።

ደርግ ውስጥ በመግባት የስለላ ተግባሩን የቀጠለው ዳዊት፤ በወቅቱ ደርግን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል አመቺ ሁኔታ ባለመኖሩና ወቅቱ የጎላ አገር ወዳድነት የሚንጸባረቅበት፣ እንደ ዛሬ የጎጥ አስተሳሰብ የነገሰበት ባለመሆኑ ደርግን የተቀላቀለበትን ዋና የማፍረስ ተግባሩን አዘገየው። በቀጣይም ወታደርነቱን ሳይገፋበት የኤርትራ አስተዳዳሪ፣ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ወዘተ የተለያዩ ሥልጣን ላይ ከቆየ በኋላ ኢትዮጵያን ለምዕራባውያን በሯን ወለል አድርጋ እንድትከፍት የሚያደርጋት ሤራ ዋና ጠንሳሽ ሆነ። ይህንኑ እንዲያመቻች “ወታደሩ” ዳዊት የዕርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ዋና ኮሚሽነር ተደረገ።

ይህም በሰው ሰራሽ ምክንያት የደረሰብን ችጋር አጉልቶ በዓለምአቀፍ መድረክ እንዲሰማ በማስደረግ በዕርዳታ ሰበብ ለምዕራቡ ዓለም በሯን ጥርቅም አድርጋ የዘጋችው ኢትዮጵያ በግድ እንድትከፍት ጫና ተደረገባት። “እምቢ” ብትል በዓለም ዓቀፉ መድረክ ክስ እንዲቀርብባት የሚያስደርግ እንደሚሆን በተሠራው ሥራ ውስጥ የዳዊት ሚና የጎላ ነበር። ከውጭ የሚመጡትን “የዕርዳታ ሰዎች” የሚያነጋግር ወደ ውጭ አገራት በመሄድ የሚወያይ፣ የሚዋዋል … ተደርጎ የተሾመው ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ሆነ። ራሱ በተለያዩ መድረኮች እንደተናገረው አየርላንዳዊውን ቦልጊዶፍን እና “We are the World” የዘፋኞች ቡድን እንዲመጣ በማስደረግ ትልቅ ድርሻ አለው።

በዳዊት ወልደጊዮርጊስ አጼ ዮሃንሳዊ ምሪት ምዕራባውያን ሰተት ብለው አዲስ አበባ ገቡ። ኢትዮጵያ ተበረበረች፤ ትህነግ እስካፍንጫው ታጠቀ፤ የዕርዳታ እህል እየሸጠ ጦር መሣሪያ እንዲገዛ ዕድሉ ተከፈተለት፤ እነ ቦብ ጊልዶፍ “አናውቅም” ቢሉም በድራማው ዋና ተዋናይ ሆኑ፤ የድራማው ዳይሬክተር ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ነበር። ሁሉም ሲጠናቀቅ ዳዊት ከችጋር ሰላባዎች ጉሮሮ 300ሺ የአሜሪካ ዶላር ዘርፎ ወደ “እናት አገሩ” አሜሪካ ኮበለለ። እዚያም ሆኖ የኮ/ሎ መንግሥቱን ስም በሚያጠለሽ መልኩ እርሱ የሌለበት ይመስል “የደም ዕንባ” የሚል መጽሃፍ አሳተመ፤ በእንግሊዝኛ ተተርጉሞ ለምዕራባውያን የፖሮፓጋንዳ ፍጆታ እንዲውል ተደረገ። ዳዊት በዓላማና በትዕዛዝ ሁሉንም ይፈጽም ስለነበር ልክ እንደ ዛሬው ያኔም የትህነግ ህጻናትን በጦርነት የመማገድ ወንጀል ዝም ተባለ።

ኮ/ል ጎሹ ወልዴ ሳንቲም ሳያጎድሉ፤ የውሎ አበላቸውንና የመመለሻ ቲኬታቸውን ወደ አገርቤት በመመለስ አሜሪካ በስደት ለመኖር ሲወስኑ (በወቅቱ ቪኦኤ ላይ ቀርበው ተናግረዋል) ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ግን 300ሺህ ዶላሩን ከረሃብተኛ ሕዝብ ጉሮሮ ላይ ዘርፎ የተንደላቀቀ ኑሮውን በአሜሪካ ጀመረ። ለቀጣይ የሤራ ፖለቲካም ራሱን አዘጋጀ። 

በግንቦት ወር 1980ዓም ወታደራዊ መኮንኖች መፈንቅለ መንግሥት ሲያቅዱ የውጭውን ሤራ ሲመራ የነበረው ዳዊት ራሱ እንደነበር በተደጋጋሚ ሲናገር የነበረው ሃቅ ነው። እስከ ሱዳን ድረስ በመምጣት ከሻዕቢያ፣ ከትህነግና ከኦነግ መሰል ድርጅቶች ጋር ተደራድሮ፣ ሰነዶችን ፈርሞ የሄደው ራሱ እንደሆነ በአንደበቱ መስክሯል። ይህ መፈንቅለ መንግሥት እንዲከሽፍ ካስደረጉትና ኮ/ሎ መንግሥቱ በዕልህ ተነሳስተው ጄኔራሎቹን ገድለው የጦሩ ሞራል እንዲላሽቅ፤ በቀጣይም ትህነግ (ወያኔ) ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገው ጉዞ የጽጌረዳ ምንጣፍ የተነጠፈበት እንዲሆን በማስደረግ የዳዊት የውጪ ሚና እጅግ የጎላ ነው። መፈንቅለ መንግሥቱም ከሽፎ የቀረው ዓላማው መንግሥቱን ፈንቅሎ ነጻነት ለሕዝብ ለማምጣት ሳይሆን ኤርትራን ለማስገንጠልና ኢትዮጵያን ለምዕራባውያን አሻንጉሊትና ተላላኪ ለሆነው ትህነግ አሳልፎ ለመስጠት ነበር።

ትህነግ ከተወገደ በኋላ ከማንኛውም ፖለቲከኛ በመቅደም አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት የሽግግር መንግሥት ምሥረታን ሃሳብ በይፋ ያቀረበው ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ነበር። “ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሻግራችኋለሁ ብለዋል፤ መልካም ነው ያሻግሩን፤ ግን እንዴት እንደምንሻገር ሮድማፕ ያስፈልገናል” በማለት እኔ ላሻግራችሁ ብሎ ለምዕራባውያን ሊሸጠን ሲያስማማን የነበረው ዳዊት ነበር። ዕቅዱን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለማቅረብ አዲስ አበባ ለአንድ ወር ደጅ ሲጠና በስውር አጀንዳው መነሻነት “ወግድ” ተባለ። ትንሽ ቆይቶ አምርሮ የሚጠላቸው አቶ ካሣ ከበደ በኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ አገር ቤት ገብተው በቀጣይ መደረግ የሚገባውን ከልምዳቸው አካፍለው በክብር መሸኘታቸው አንጨረጭሮት አሜሪካ እንደገባ በገሃድ በኢትዮጵያ ላይ ዘመቻውን አወጀ።

ትህነግ በኢትዮጵያ በየቦታው የቀበረውን ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ የብሔር (የዘውግ) ቦምብ ምን እንደሆነ እያወቀ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ የመሸጋገሪያ ዕቅድ ብሎ ያቀረበው አንዱ ሃሳብ “በብሔር ላይ የተመሠረቱ ድርጅቶችን በሙሉ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይሠሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዋጅ ማገድ አለባቸው” የሚል ነበር። ይህንን ረቂቅ በየዋህነት የተቀበሉ የዛሬ ሦስት ዓመት ጀምረው “የሽግግር ሮድማፕ (ፎኖተካርታ)” እያሉ ዳዊታዊ ዝማሬ ሲያሰሙ ሰኔ 15 ቀን በተደረገው ምርጫ የሕዝቡን ምላሽ አግኝተዋል።

በሕዝብ ቅቡልነት ያለው መንግሥት መስከረም ላይ ከመመሥረቱ በፊት ዳዊት የመጨረሻ የምትመስለውን ካርድ በመምዘዝ ዘመቻውን እያጡዋጧፈ ነው። እንደ ቤት ጥራጊ ተሰብስበው አንድ ቦታ ላይ የተከማቹትን እነ ታምራትን በአንድ በኩል በመሰብሰብ በሌላ በኩል ደግሞ አሁንም በዕርዳታ ስም ምዕራባውያን ሰላዮች ዳግም ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ለማድረግ እያሤረ ይገኛል። ዳሩ ግን ዳዊት ለዚህ ዘመቻው ካሰባቸው መካከል “ዛሬ ላይ ቅድሚያ አገሬ” ያሉ አንድ አገር ወዳድ ሰነዱን ለመንግሥት አቅርበዋል። አስቀድሞ መረጃ የነበረው መንግሥት ይህ ሰነድ የተበላበት መሆኑንን ይፋ አድርጎ ሌላ ሙከራ እንዲሞክሩ ጋብዟቸዋል። 

መረጃውን ያካፈሉን እንዳሉት ይህ ዳዊት ያዘጋጀውና አሜሪካ “እንቅልፍና ሰላም አጥታ ልትተገብረው ነው” የሚባለው ሰነድ ልክ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ማመልከቻቸውን እንደሚያቀርቡ ዜጎች የቀረበ ሰነድ ነው። የቀረበውም ትህነግ በቀጠራቸው የወስዋሽ ድርጅቶችና በውጭ ጉዳይ መ/ቤቱ (ስቴት ዲፓርትመንት) የትህነግ ውክልና ባላቸው የህዝብ ግንኙነት ኤጀንቶች አማካይነት ነው።

ይህ አሜሪካ እንደ መንግሥት አንዳችም ዓይነት ምላሽ ያልሰጠችበት ሰነድ ውስጥ ስማቸው የተካተተው አቶ ለማ መገርሳ የዜና ማሟሟቂያ እንደተደረጉ የዲሲ ተባባሪያችን አረጋግጧል። አቶ ለማ አሜሪካ ቢሆኑም አንድም ጊዜ ስዬ አብርሃንም ሆነ ዳዊት የሚባለውን ኢትዮጵያ ላይ የተጣበቀ ኩርንችት አግኝተው አናግረው አያውቁም።

በእርግጥ ሰነዱ እንደተላከላቸው መሸሸግ እንደማይቻል ያስታወቀው የመረጃ ምንጭ ከዚያ ባለፈ ግን የሳቸው ተሳትፎ ምንም ነው። አሁን አሜሪካ ሆነው ሰርግ፣ ቤተክርስቲያንና ማህበራዊ ግንኙነት ላይ አተኩረው ያሉትና ብዙ ጊዜያቸውን ከትዳር ጓዳቸው ጋር የሚያሳልፉት አቶ ለማ ስማቸው ከዚህ ያለቅጥ ከተወራለት ንቅናቄ ጋር የተነሳው “የኦሮሞ ውክልና አለን” ለማስባልና በዚሁ ሰበብ ከትህነግ ጋር መቀሌ ድረስ በመሄድ አብረው ለመሥራት ደጅ ሲጠኑ የነበሩ ጽንፈኛ ኦሮሞዎችን ለማስገባት ታስቦ እንደሆነ ዘግቧል።

“ወለጋ የአማራ ነው! አማራ መሬቶቹና ርስቶቹን ያስመልሳል!” በማለት ግራ በሚያጋባና በሚታወቁ ባለሃብቶች በሚታገዘው መረጃ ቲቪ የእርስ በእርስ ዕልቂት እንዲከናወን ቅስቀሳ ሲያደርግ ከነበረው ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ጋር አቶ ለማ ለጊዜው ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌላቸው የቅርብ ወዳጃቸው ለጎልጉል አስታውቋል። በቅርቡም ወደ ጣሊያን አምርተው ሥራ እንደሚጀምሩ አመልክቷል።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Politics Tagged With: dawit, dawit woldegiorgis

Reader Interactions

Comments

  1. Bekele Gebre says

    July 26, 2021 05:03 am at 5:03 am

    This indicates that the writer is fully charged with and strongly linked with the Ethiopian authorities in power. Even if it is necessary to write about the matter why in such full of insult manner? May be “hod-ader ” personality.

    Reply
  2. Tesfa says

    July 26, 2021 08:20 am at 8:20 am

    ጎበዝ አብደናል። ጠበሉም መድሃኒቱም ሊያሽለን አልቻለም። አሁን አሁንማ ችግራችን እጅግ ከመወሳሰቡ የተነሳ ረጋ ብሎ በሃገርና በውጭ ስለ ኢትዮጵያ የሚሰራጩ ዜናዎችን ላዳመጠ ተነሱ፤ ታጠቁ፤ ዝመቱ፤ ተወረናል፤ ወረውናል፤ ተፈናቀሉ፤ ተገደሉ፤ ሃገር ጠለው ወጡ በማለት ውሸትን ከእውነት ጋር እየቀየጡ እብደታችን ጣራ ላይ አድርሰውታል። እኔ በግሌ ሻለቃ ዳዊትን አላውቀውም። የማውቀው በሚዲያና በጻፋቸው መጽሃፎች በኩል ነው። በተለይም “Red Tears” እና ክህደት በደም መሬት በተሰኙት መጽሃፍቶቹ በኩል። ሻለቃ ዳዊት ሃገርን የሚያፈርስ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚጎዳ ነገር ያደርጋል ብዬ ጭራሽ አላምንም። ታዋዊው አባቱ ጠላትን የተፋለሙ፤ ሃገር ወዳድ ጀግና ናቸውና የእርሳቸውን አጽም መርገጥ ይሆናል። ግን መስሎትና በውጭ የስለላ መረብ ሃይሎች ተታሎ የተባለውን ነገር እየሞከረ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ከሻለቃ ዳዊት በላይ የነጮችን ተንኮል የሚያውቅ ሰው አለ ብዬ እኔ አላምንም። ስለሆነም ከአፍራሾች ጋር አብሮ ሃገርና ህዝብን ይጎዳል ብየ አላምንም። ግን ዘመኑ Disinformation/Misinformation እየተለቀቀ ሆን ተብሎ የሰዎችን ገጸ ባህሪና ነባርና የአሁን ለሃገርና ለህዝብ ያደረጉትንና በማድረግ ላይ ያሉትን አስተዋጾ ለማጠልሸት የሚለቀቅበት በመሆኑ የምናናፈሰው ወሬ ሁሉ ተቀባይነት እንዲኖረው መረጃ ተመርኩዞ ቢቀርብ የተሻለ ነው።
    ክዚህ ባሻገር አሁን በሃገራችን አማራው እና የወያኔው ቁንጮ ደ/ጽዪን ዛሬ የክተት አዋጅ ማድረጋቸው ለመተላለቅና የሰው መሳቂያ ለመሆን እንደተዘጋጀን ያሳያል። የእብድ ገላጋዪች የነጩ ዓለምና አረቡ እሳት እያቀበሉ እኛ ራሳችን ስንገዳደል ሞታችንን የዜና ማሟያ በማድረግ ይሳለቁብናል። በቅርቡ የትግራይን ህዝብ የመለመኛ ስልቻ ለማድረግ በሱዳን ተነድባ በተባለ የስደተኞች ጣቢያ ቆመው ያሳዪን የነበሩትን ብቻ እማኝ ማቆም ይቻላል። መስሎን እንጂ ነጩም ሆነ አረቡ ዓለም እኛን መነገጃ ነው ያደረጉን። በትግራይ ህዝብ ስም የተለመነው ጥሬ ገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ እቃ ለተረጂዎች የሚደርሰው ሲሶው ብቻ ነው። ግን መሪዎቻችን እናውቅላችሁሃለን የሚሉን እንዴት ይህን በገሃድ የሚታይ ነገር ማመን ተሳናቸው? መልሱ ቀላል ነው። የሚኖሩት ለራሳቸው ብቻ በመሆኑ ነው። አሁን እንሆ የአማራው ክልል መሪ የክተት ጥሪ ሲያረጉ የወያኔ መሪ ደግሞ የትግራይን ህዝብ “ትግራይን ከካርታ ላይ ለማጥፋት” በተነሱ ጠላቶቻችን ላይ ዝመት፤ ተነስ በማለት በሰለለና በተዳከመ ድምጽ ትላንት በጊዜአዊ አስተዳደሩ አልሰራ ያለው ቴለቪዥን ትግራይ ላይ ብቅ ብለው ደስኩረዋል። ወንድም ወንድሙን እህት እህቷን እንድትገል ተነስ የሚባልበት ሃገር የሃበሻው ምድር ብቻ ነው። ጉረኛው ጄ/ጻድቃን አዲስ አበባ ለመግባት የያዝነው ስትራቴጂን ተከትለን እየተገበርን ነው ይለናል። እውነት ወያኔዎች ታመዋል ወይስ በህልም ዓለም ነው የሚኖሩት። በምንም ሂሳብ ወያኔ ዳግም አዲስ አበባን አይረግጥም። ሰው በጣም ጠልቷቸዋል። እንኳን አዲስ አበባ መቀሌ ላይ ነጻ ምርጫ ቢደረግ 100% የትግራይ ህዝብ ወያኔን አይፈልግም። ግን በአፈሙዝ የታፈነ ህዝብ ነው። ልጅህን/ልጅሽን ለጦርነት ካላመጣሽ የእርዳታ እህል እንዳይሰጥ መመሪያ የሚያወጣ ድርቡሽ ድርጅት ነው። እብደታችን ሰማይ ጠቀስ በመሆኑ በተውሶ መሳሪያ እየተገዳደልን ምድሪቱን ሰው አልባ ልናረጋት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ወያኔ ነው። የትግራይ ህዝብ ጠላት ሻቢያም አማራም አይደለም። ወያኔ ነው። ይህ ግን ለትግራይ ልጆች ገና አልገባቸውም። የሃጎስ ሞት ከአማራው ገብሬ ሞት የሚለየው የለም። ሁለቱም ኢትዮጵያዊያን ናቸው። በዘርና በቋንቋው ላበደና ለሰከረ ትውልድ ግን ለቅሶም ዘር ተጠይቆ ሆኗል። ሰው በሰውነቱ መመዘኑ ተሰርዟል። የዚህ ክፉ ሃሳብ አመንጪና መከፋፈልን የዘራው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነው። ሰው ከሰው ጋር ተላትሞ ደም ካልፈሰሰ ወያኔ መኖር አይቻለውም። ጌታቸው ረዳ ከዘመናት በፊት ለሃገር ውስጥ ለጋዘጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲህ ብሎ ነበር። ስለ አማራና ኦሮሞ አንድ ላይ መቆም ጋዜጠኛው ላቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ “አማራና ኦሮሞ አንድ ሆኑ ማለት እኛ የቤት ስራችንን አልሰራንም ማለት ነው” በማለት ነበር የመለሰው። ያ ማለት ማተራመሱ ይቀጥል። እናጣላቸው። እናባላቸው ነው። አሁን ደግሞ ያለቅጥ ወፍሮ ከተደበቀበት ዋሻ ከወጣ ወዲህ “ኢትዮጵያን ሲኦል እናወርዳታለን” በማለት ነው የደነፋው። እንዲህ አይነት ጭንቅላት ያላቸው እብዶች ናቸው የትግራይን ህዝብ እናውቅልሃለን የሚሉት። ክራራይሶ ያሰኛል።
    የዚህ እንደ ሰፈር ልጆች ኑና ይዋጣልን የጦር ነጋሪት ጥሪ በጣም የሚያሳዝንና የሚያሳፍር በ21ኛው ክፍለ ዘመን በረጋ መንፈስ ቁጭ ብሎ በመነጋገር ቅራኔዎችን ማላላት ወይም መፍታት ሲቻል ቧርቀው ያልጠገቡ ልጆችን ከመንገድ ላይ እያፈሱ ለጦርነት መማገድ ድርቡሻዊነት ነው። የዚህ ሁሉ ጉራና ጡሩንባ ውጤቱ ግን ሞትና የቆመን ማፍረስ ብቻ ነው። ለሃገር ለቆምኩለት ወገን አስባለሁ የሚል ማንም ባለስልጣን ወገኑን እየገደለ ለሃገር ነው፤ ለእናንተ ነው ማለት አይቻለውም። የጄ/ጻድቃን አዲስ አበባን ለመቆጣጠር መደንፋት በአሜሪካና በግብጽ እየተደገፉ ከሆነ ይሳካል። ወያኔ ብቻውን ግን እንኳን አዲስ አበባን ጎንደርን አያልፋትም። ሰው አምሯል። ሰው ወያኔን ጠልቷል። የዚህ ሁሉ ግርግርና የጦርነት ጥሪና የጦርነት አውድማ ውጤቱ በሚከተለው ግጥም ይጠቃለላል። ሌላው ሁሉ ፍሬ ፈርሲኪ ነው። በቃኝ!

    እነርሱም ይላሉ ከተኮስን አንስትም
    እኛም እንላለን ቃታ አናስከፍትም
    ይህን ብለን ብለን የተገናኘን ለት
    አሞራ ተሰብሰብ ትበላለህ ድለት

    Reply
  3. አምባው በቀለ says

    July 26, 2021 10:38 am at 10:38 am

    ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈጸመው እውነተኛ ታሪክ ይህ ነው። በተለይም የእርዳታ $300 መቶ ሺህ ዶላር ዘርፎ አሜሪካ መግባቱን የርዳታ ማስተባበሪያ ኮሚሺን የሂሳብ ሰራተኛ በመረጃ በ1989 በፍረንጅ አቆጣጠር አሳይቶኛልና በመሆኑም ይህ ጽሁፍ በተለያዩ ሚዲያዎች ቢሰራጭ መልካም ነው እላለሁ።

    Reply
    • Tesfa says

      July 27, 2021 09:44 am at 9:44 am

      ልጅ አምባው – በምንም የሂሳብ ስሌት ሻለቃ ዳዊት $300 ሺህ ዶላር ቀርቶ አንድ ሺህ ዶላር ሊሰርቅ የሚችልበት መንገድ የለም። ጊዜው እኮ የደርግ ዘመን ነው። በወያኔ ዘመን ቢሆን ቢሊዪን ዶላርም ትሰርቃለህ። የእርዳታ ማስተባበሪያው የሂሳብ ሰራተኛ ያሳየህ መረጃ የት አለ? ይህ የሂሳብ ሰራተኛስ ዛሬ በህይወት አለ? ቆሞ ሊመሰክር ይችላል። በፈጠራ ወሬ ሰውን ጭቃ መቀባት የሃበሻ የፓለቲካ ስልት ነው። የሻለቃ ዳዊት በደል ሃገሩንና ህዝቡን ከልቡ መውደድ ብቻ ነው። ይህን አቋሙን የሚጠሉ የፓለቲካ ነጋዴዎች በ 1989 ዓ.ም ሆነ የተባለ ጉዳይ ዛሬ ከተቀበረበት በማውጣት ይህን ስሙ የሚሉን የውስልትናቸው ምንጭ ማባሪያ በማጣቱ ነው። $300 ሺህ ዶላር የዘረፈ ሰው ሥራ ፍለጋ ከስፍራ ስፍራ አይንከራተትም። ሰራተኛም ሆኖ ለረጅም ጊዜ አይሰራም። ተዘረፈ የተባለው ገንዘብ በዛሬው የዶላር የመግዛት አቅም ወደ 2 ሚሊዪን ይጠጋልና። ስለሆነም ጊዜ ያለፈበት እጅ እጅ የሚል ወሬ ከማናፈስ ይልቅ አሁን ሃገሪቱ የገጠማትን የውጭና የውስጥ ፍትጊያ በጋራ ለመመከት አንድ ሆነን እንነሳ። ሌላው ሁሉ ለወፎች የሚሰጥ የእህል ፍሬ ነው። እንክርዳድ ወሬ!

      Reply
  4. ነፃ ሕዝብ says

    July 26, 2021 11:45 am at 11:45 am

    በሻለቃ ዳዊት ወ/ጊወርጊስ ላይ ያቀረባችሁትን ውንጀላ ደጋግሜ አየሁት/አነበብኩት/ የሚሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ ይላል የሀገሬ ሰው ! ይሄ ሁሉ የሀገራችን ውጥንቅጥና ምስቅልቅል ሊደርስ የቻለው በእናንተው የበሻሻው አውሬ በፈጠረው የድንቁርና አመራር መሆኑን መናገር አትፈልጉም ፥ ሻለቃ ዳዊት አውሬው አብይ ወደ ሥልጣን እንደመጣ መሆን ያለበትን ሁሉ ነግሮትና መክሮት ሊሰማና ሊቀበለው አልቻለም ፥ በዚያም የተንሳ የትግራይ ቅጥረኞችና ባንዶች ኢትዮጵያን ለመበተን የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም ፥ ተባባሪያቸውና ለዚህም ያደረሳቸው የበሻሻው አውሬ ፓስተር አብይ አህመድ ድኩማን አመራርና የደንቆሮ ሸፍጥ የአማራን ሕዝብ ለማዳከምና ብሎም ለማጥፋት ዕኩይ ሴራውን ሲያካሂድ ቆይቶ ለዚህ ዳርጎናል ፥ የበሻሻው አውሬ በአፉ የሚናገረውና በተግባር የሚተረጉመው በፍጹም የተለያዩ ናቸው ፥ በወለጋና በቤኒሻንጉል አያሌ የአማራ ተወላጆች በየቀኑ እየረገፉ ሲሆን ይህም አልበቃ ብሎት ጥንታዊቷን የአጣየ ከተማ በነፍሰ_ገዳዩ ኦነግ እንድትወድምና ከ200 በላይ የአማራ ሕዝብ እንዲያልቅ ብሎም ከአንድ ሚሊዮን በላይ እንዲፈናቀል ያደረገው አብይ አህመድና ተባባሪዎቹ የኦነግ አመራሮች መሆናቸው የአደባባይ ምሥጢር ሆኖ እያለ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደተባለው ሻለቃ ዳዊትን መወንጀል ፈለጋችሁ ፥ በጣም የማታፍሩ ውሸታሞች መሆናችሁን የተረዳሁት ደግሞ “ወለጋ የአማራ ነው” ብሎ ሻለቃ ዳዊት ተናግሮዋል ስትሉ ነው ፥ እጅግ በጣም ያሳፍራል ፥ እኔ እርሱ ሲናገር ሰምቼዋለሁ ፥ በፍጹም እንዲህ የሚል ቃላት አልተናገረም ፥ በጣም አሳፋሪዎች ናችሁ ፥ ሻለቃ ዳዊት $300ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወስዶዋል አላችሁ ፥ ይህም 100% ውሸትና ቅጥፈት ነው ፥ የምትጽፉት መቶ በመቶ ባልተጨበጠና ምንም ዓይነት ማስረጃ በሌለው ነገር ነው ፥ ያሳፍራል ፥ ያሳዝናል ፥ ትናንት ለባንዳውና ቅጥረኛው የትግራይ ነፍሰ_ገዳይ ህወሃት ስታደገድጉና ስታፈደፍዱ የነበራችሁ ሎሌዎችና ነዳያኖች ዛሬ ደግሞ ለተረኛው የኦሮሙማው አፓርታይዳዊ አገዛዝ ፀረ_ኢትዮጵያ ለሆነው ከፋፋይና ዘረኛ ሥርዓት ነው ፥ ሻለቃ ዳዊት ኢትዮጵያዊ ስብዕና ያለው ምርጥ የአማራ ልጅ ያውም የሰሜን ሸዋ ተወላጅ ነው ፥ የበሻሻው አውሬ ከሰበሰባቸው አያሌ ግዑዛን ውስጥ ከሻለቃ ዳዊት ጫማ ሥር የሚደርስ አንድም ሰው የለም ፥ ሻለቃ ዳዊት ጥልቅ የውትድርና ዕውቅት ያለው ሲሆን በፖለቲካው ዓለም ደግሞ በምድራችን ላይ ካሉት እውቅ ፖለቲከኞች መካከል አንዱና ዋንኛው የዳበረ አስተምህሮ ያለው ኢትዮጵያዊ የአማራ ልጅ ነው ፥ በኦሮሙማው አፓርታይዳዊ አገዛዝ ውስጥ ያለው አመራር እንደ ደረም አህያ ከሚጋፋውና ኢትዮጵያን እየዘረፈ በድንቁርና ከሚግተለተለው መሃይማን ውስጥ በአንድ ቢጨፈለቁ ሻለቃ ዳዊትን አያህሉም ፥ የበሻሻው አውሬና መሰሪው አብይ አህመድ የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላትና ፀረ_ኢትዮጵያ ነው ፥ ለዚህም ማሳያው የአማራ ሕዝብ መሪዎች በአንድ ቀን እንዲገደሉና የአማራን ሕዝብ መሪ አልባ ለማድረግ ያላደረገው ሴራ አልነበረም ፥ ስለዚህ ጎልጉሎች ከእውነት የራቀ ሰው መጨረሻው ውርደትና ሃፍረት ስለሆነ ከእውነት ጋር አትፋቱ ፥ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አብዝቶ ይጠብቅልን ፥ የራቀውን ሠላሟንና አንድነቷን ያምጣልን ፥ ሞት ለውሸታሞችና ለፀረ_ኢትዮጵያን ይሁን ፡፡

    Reply
  5. Akalu Tadesse says

    July 26, 2021 01:58 pm at 1:58 pm

    Why doesn’t Ato. lemma come out on any media and show his cleanness from this drama. It will expose and also will discredit the instigators, for once and all. Otherwise it is going to divide the people. I personally suggest, Immediate action from Ato Lemma is needed to show he is not part of this heinous drama

    Reply
  6. ሥርጉተ ሥላሴ says

    July 28, 2021 01:35 pm at 1:35 pm

    አዝኜባችሁ አለሁ ከልቤ። ዕውነት መንጋ የለውም። የዕውነት አምላክ ይፈርዳል። አንድ እሳቸው ቢኖሩን እሳቸው ላይ ተዘመተ። ፖለቲካ ለእናንተ ጥርጣሬ ቁማር፣ ኢንትሪግ ነው። አዝናለሁ። በህወሃት ህገ መንግሥት በህውኃት አርማ፣ በህወኃት ውራጅ አባል ላለ ዕብን ጥብቅና ቆሞ ትናንት ከእኛ ጋር አፈር ድሜ ግጦ ለታገለ ምስጋና ቢቀር ወቀሳ? እርግጥ ነው ሻለቃ ካሉበት ከዚህ ስብስብ እኔም ይከፋኛል። ነገር ግን በሥማ በለው ይህ ሁሉ ማዕት እርግማን ነው። ሰርክ ሰኔል እና ቹቻ ለታደለች አግር ይህን ያህል ትርምስ አያስፈልግም። ኢትዮጵያ ከብዳናለች። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule