ኃያላን በአፍሪካ ስለሚያደርጉት ሽኩቻ አፍሪካ የአለም አቀፍ ሽኩቻ መድረክ መሆን የለባትም ሲሉ የተናገሩት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ገንግ፤ በአምስት የአፍሪካ ሀገራት የሚያደርጉት ጉብኝት መጀመሪያ ላይ አዲሱን የአፍሪካ CDC ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው። ቻይና ባለፉት አስር በላይ አመታት የአፍሪካ ትልቋ የንግድ አጋር ሆና የቆየች ስትሆን፤ በአህጉሪቱ ብሎም በአለም ኃያልነት ግስጋሴዋ ባለፈው ወር 49 የአፍሪካ መሪዎችን ካስተናገደችው ከአሜሪካ እንዲሁም ከቀድሞ ቅኝ ገዥ አውሮፓውያን በተለይም እንደ ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ ካሉ የአሜሪካ አጋሮች ጋር ትፎካከራለች። ቺን ገንግ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "አፍሪካ ለዓለም አቀፍ ትብብር ትልቋ መድረክ እንጂ ለጉልበተኛ ሀገራት የውድድር … [Read more...] about የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር?
world bank
በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ
በቀጣይ በጀት ዓመት ደግሞ 20 ቢሊዮን ብር ተመድቧል የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር (300 ሚሊዮን ዶላር) ድጋፍ ለማድረግ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና የኤርትራ ዳይሬክተር ኦስማኔ ዶኔ ጋር ተፈራርመዋል። የድጋፍ ስምምነቱ በጦርነቱ በአማራ፣ አፋር፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችና ማህበረሰብ ለመልሶ ግንባታና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን በአስቸኳይ ለመደግፍ ያለመ ነው። ድጋፉ በተመረጡ የግጭት ተጎጂ ወረዳዎች የጤና፣ የትምህርትና የውሃ መሰረት ልማት መዘርጋት ብሎም ለፆታዊ ጥቃት የተጋለጡ ሴቶችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም ይውላል ተብሏል። የፌዴራል መንግስት … [Read more...] about በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ
የዓለም ባንክ የ907 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ አደረገ
የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሚተገበሩት ሶስት ፕሮጀክትች የሚውል የ907 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ዛሬ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና ዓለም ባንክ ግሩፕ ምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሚ/ር ዲዮን ነው የተፈራረሙት። የገንዘብ ድጋፉ በኢትዮጵያ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ፤ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎትን አሰጣጥንና ተደራሽነትን ለማሳደግ እንዲሁም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚውል ነው ተብሏል። የመጀመሪያው የ200 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚውል ነው። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ክፉኛ የተጎዱ እንተርፕራይይች አዋጭ በሆነ መንግድ እንዲቀጥሉና በንግድ ውስጥ እንዲቆዩ ለማድረግ … [Read more...] about የዓለም ባንክ የ907 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ አደረገ
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ400 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ማፅደቁን የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል። የገንዘብ ድጋፉ በኢትዮጵያ የከተማ የሴፍቲ ኔት ፕሮጀክትን ለመደገፍ ይውላል ተብሏል። ከድጋፉ ውስጥ 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላሩ ስደተኞች ለሚገኙበት አካባቢና እና በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ስደተኞች የስራ እድል ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ነው የገንዘብ ሚነስቴር በትዊተር ገፁ ያስታወቀው። ከዚህ በፊት የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ገንዘብ አገደ፤ ከለከለ እየተባለ በተለያየ ሚዲያ ሲወራ ቆይቷል። ይህ ባንኩ የፈቀደው ገንዘብ ኢትዮጵያ ከባንኩ የምታገኘው ሁሉንም የሚጠቀልል ባይሆንም ባንኩ ከኢትዮጵያ ጋር የገባው ውዝግብ እንደሌለውና ቀሪውንም ገንዘብ በወቅቱ እንደሚፈቅድ ጠቋሚ ነው ተብሏል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ