የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ400 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ማፅደቁን የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል። የገንዘብ ድጋፉ በኢትዮጵያ የከተማ የሴፍቲ ኔት ፕሮጀክትን ለመደገፍ ይውላል ተብሏል። ከድጋፉ ውስጥ 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላሩ ስደተኞች ለሚገኙበት አካባቢና እና በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ስደተኞች የስራ እድል ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ነው የገንዘብ ሚነስቴር በትዊተር ገፁ ያስታወቀው። ከዚህ በፊት የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ገንዘብ አገደ፤ ከለከለ እየተባለ በተለያየ ሚዲያ ሲወራ ቆይቷል። ይህ ባንኩ የፈቀደው ገንዘብ ኢትዮጵያ ከባንኩ የምታገኘው ሁሉንም የሚጠቀልል ባይሆንም ባንኩ ከኢትዮጵያ ጋር የገባው ውዝግብ እንደሌለውና ቀሪውንም ገንዘብ በወቅቱ እንደሚፈቅድ ጠቋሚ ነው ተብሏል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ