ለሁለት ዓመታት የተደረገው ድርድር ያስገኘው ውጤት ነው የዓለም ባንክ በዛሬው ዕለት (ማክሰኞ) “የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዘላቂና ሁሉን ዓቀፍ የልማት ፖሊሲ ዘመቻ” (Ethiopia First Sustainable and Inclusive Growth Development Policy Operation) በሚል ለሚጠራው የልማት ፖሊሲ ማስፈጸሚያ የሚሆን ድጋፍና ብድር መፍቀዱን ይፋ አድርጓል።በወጣው መግለጫ መሠረት ባንኩ የሚያደርገው ድጋፍ ሦስት ዓላማዎችን ያካተተ ነው፤ (ሀ) ለመዋቅር መልሶ ማዋቀርና ንግድን ለማሳለጥ (ለ) በጀትን በተመለከተ ዘላቂነትንና ግልጽነትን ለማስፋፋት እና (ሐ) የአካባቢ ጥበቃን እና ማኅበራዊ አይበገሬነትን ለማበረታታት እንደሆነ ተገልጾዋል። በተለምዶ የዓለም ባንክ የሚባለው ቡድን ሲሆን በሥሩም የተለያዩ ድርጅቶች አሉት፤ ብድርም ሆነ ሥጦታ ሲፈቀድ … [Read more...] about ኢትዮጵያ 16.6 ቢሊዮን ዶላር ከዓለም ባንክ አገኘች