ባለፈው ሳምንት “ከሃዲው ዳዊት ወልደጊዮርጊስን” አስመልክቶ “ዳዊት ወልደጊዮርጊስ – የጸረ ኢትዮጵያዊነት መገለጫ” በሚል እርዕስ ዜና ማቅረባችን ይታወሳል።
በዜናው ግንባር የተጠቀሰው ሳይጀመር በከሸፈው “የሽግግር መንግሥት” ማመልከቻ ጉዳይ ነበር። ያተምነውን ዜና ተከትሎ አቶ ለማ መገርሳ “ተውኝ። ልኑርበት” ሲሉ ስለጉዳዩ ምንም እንደማያውቁ በይፋ መናገራቸው፣ ፕሮፌሰር ተዘራ ዳዊት የሤራው ስብስብ አገር ለመርዳት መስሏቸው ከገቡ በኋላ ሲያዩት ሃያ ሰባት ዓመታት ኢትዮጵያን ሲዘርፍና ሲያደማ የኖረውን ትህነግን ወደ ስልጣን ለመመለስ እንደሆነ ሲረዱ ራሳቸውን ማግለላቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ራሱ አስተባባሪውም “የለሁበትም” ሲል ዳግም ክህደቱን አሳይቷል።
በዚህ ዜና ላይ ዳዊት ከሃዲና ዘራፊ መሆኑን ለማሳየት ከረሃብ ሰለባዎች ጉሮሮ መንትፎ አገር ስለመክዳቱ መግለጻችን ከተራ የጥላቻ ስሜት የተቀዳ እንደሆነ ለዳዊት የተቆረቆሩ አስተያየት ሰጥተዋል። በመሆኑም ዳዊት ዘራፊ መሆኑንን፣ የዘረፈውም ረሃብ ከሚጠብሳቸው ዜጎች ጉሮሮ ላይ ስለመሆኑ በወቅቱ የቀረበውን ማስረጃ ማተም አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
የዛሬ 35 ዓመት ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ከነበረበት የዕርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ ኮሚሸን ስራው በመጠናቀቁ ለቅቆ አሜሪካን አገር የ”አስጠጉኝ” ጥያቄ አቅርቦ ነበር። በወቅቱ ከማይታወቀው ሌብነቱ በተጨማሪ በርሃብ ከተጠበሱ ዜጎች ጉሮሮ በቁጥር የተገለጸ የዕርዳታ ገንዘብ ዘርፎ ወደ አሜሪካ እንዳሸሸ የኢትዮጵያ መንግሥት በይፋ አስታውቋል።
ዳዊት ዘረፈ ስለተባለውና የኢትዮጵያ መንግሥት በይፋ ያስታወቀው ዜና ከዚህ በታች በቀረበው የአሶሺዬትድ ፕሬስ ዘገባ ላይ በግልጽ ተቀምጧል። በወቅቱ ጥቂት ነገር ከመናገር ሌላ ስለ ገንዘቡም ሆነ በውጭ አገራት ስለገዛቸው የግል መኖሪያ ቤቶች በማስረጃ ወይም አሳማኝ በሆነ መልኩ ሲያስተባብል አልተሰማም።
አሶሺዬትድ ፕሬስ ያነጋገራቸው የዳዊት የቅርብ ሰው ዳዊት በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ጠቅላይ ግዛትና በእንግሊዝ አገር ሎንዶን የግል መኖሪያ ቤት እንዳለው መስክረውበታል።
ዳዊት በተለያዩ ጊዜያት በራሱ አንደበት እንደተናገረው በ1980 የተደረገውን መፈንቅለ መንግሥት ካከሸፉት ተባባሪዎቹ አንዱ ቁምላቸው ደጀኔ በድብቅ ከአገር ወጥቶ አሜሪካ ጥገኝነት በጠየቀበት ጊዜ ዳዊት ቤት ተቀምጦ እንደነበርና እንደረዳው አስረድቷል።
የዚህ ሁሉ ገድል ባለቤት ነው እንግዲህ ዛሬ “አገር ካልመራሁ” በሚል የዘረፈውን እየረጨ በሚዲያ በተለይም ባለሃብቶች ስፖንሰር በሚያደርጉት የመረጃ ቴሌቪዥን የርስ በርስ እልቂት ክተተ የሚያውጀው።
የዛሬ 35 ዓመት በዳዊት ወልደጊዮርጊስ ላይ የወጣው የዜና ዘገባ ከዚህ በታች ይገኛል።
Ethiopia Says Former Aid Chief Fled to United States with Money
JAMES R. PEIPERTMay 7, 1986
NAIROBI, Kenya (AP) _ Ethiopia said its top relief official during the 1984-85 famine has fled to the United States with at least $300,000 in famine aid money.
In Washington, the State Department on Wednesday confirmed that Dawit Wolde Giorgis was in the United States. Deputy spokesman Charles Redman had no comment on whether Dawit had sought political asylum.
A Voice of America official said Dawit was in New York where he told VOA by telephone there was no foundation to Ethiopian government charges that he had ″betrayed his country and exchanged his dignity for personal gain.″
The VOA official, Brian McClure, said the conversation with Dawit did not go beyond the denial and that Dawit declined an on-the-record interview.
The accusations against Dawit, who headed the Relief and Rehabilitation Commission, was made in a lengthy statement in the Amharic language late Tuesday by Ethiopia’s state-run radio. An English version of the statement was broadcast Wednesday and monitored in neighboring Kenya.
Asked about the allegations against Dawit, Redman said extensive U.S. government monitoring shows ″no indication any U.S. assistance has been diverted.″
The radio announcement was the first official acknowledgement that Dawit had defected. He was last heard of on Oct. 25, when he left Ethiopia for Europe and the United States to solicit famine relief funds.
Western diplomats and Ethiopian and foreign relief officials in Ethiopia generally assumed late last year that he had left for good and was in the United States. Last December, however, the State Department said no asylum request had been received.
The broadcast indicated Dawit was in the United States, referring to ″those like him who are living in luxury in the cities of America.″
An acquaintance of Dawit told The Associated Press last December in Addis Ababa, the Ethiopian capital, that Dawit had homes in California and London. Other sources said he settled in Santa Barbara, Calif.
Dawit’s defection was considered a severe embarrassment to the Ethiopian government. He had been an army major, a senior government figure and a close friend of the country’s military leader, Mengistu Haile Mariam.
The Ethiopian government statement said Dawit, a bachelor in his mid-40s, had ″engaged in personal profiteering at a time when every minute had to be used in the campaign to save lives.″
It said the embezzled funds included $300,000 from a Relief and Rehabilitation Commission bank account in New York, and that Dawit had distributed thousands of dollars to relatives in California and Maryland.
For two years Dawit was head of the commission, the main government agency coordinating the international famine relief operation. He was known internationally for his impassioned pleas for aid to his drought-stricken nation, where it was estimated that famine affected 8 million of its 42 million people.
″The money stolen by Dawit was stolen from the mouths of hungry infants, mothers and elderly citizens of Ethiopia,″ the government statement said.
″He misappropriated funds allotted to the work of saving the lives of our compatriot children and youth who were on the brink of death, thereby committing an act which will never be forgiven by history, and has fled from the country after betraying it.″
The government has never officially estimated the death toll in the famine. But relief officials have said privately they believe about a million Ethiopians died.
The statement called Dawit ″an urgently wanted criminal″ and an ″enemy of the people.″ It said that ″those who stand for justice and truth will cooperate with us in bringing him to punishment.″
When Dawit left Ethiopia last October, the itinerary for his fund-raising mission was not announced. But sources in Addis Ababa, including diplomats and relief officials, said he went to Britain, Belgium and the United States. They said his last contact with the Ethiopian government was from Brussels, the Belgian capital.
The sources said one of Dawit’s brothers defected to the United States last September.
The government statement said Dawit had arranged for commission bank accounts to be set up in foreign cities, including New York and London, for deposit of aid donations.
″The money deposited in the commission’s foreign bank accounts was then pocketed by the traitor,″ it said.
ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ
ነፃ ሕዝብ says
ጎልጉል የቅጥረኛውና ባንዳው ህወሃትና የፋሽስቱና ዘረኛው ኦሮሙማው አፓርታይዳዊ አገዛዝ የውሸት ፕሮፖጋንዳ ፊሻካ ድህረ_ገጽ መሆኑን በትክክል የተረዳሁት ዛሬ ነው ፥ የበሻሻው አውሬና ፀረ_ኢትዮጵያ የሆነው አብይ አህመድ ካልተወገደ በስተቀር ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የማትቀጥል መሆኗን በሶስት ዓመታት ውስጥ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል ፥ አውሬውና አስመሳዩ ፀረ_ኢትዮጵያው አብይ አህመድ ከትግራዩ የምዕራባውያን ቅጥረኛና ባንዳ ህወሃት የባሰ ሴረኛና በዘረኝነት የተበከለ ሲሆን እርሱ ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት መሆኑን በገሃድ አሳይቶናል ፥ በሀገሪቱ የተለያዩ ክ/ሀገሮች አማራው ተገድሏል ፥ ተሳዷል ፥ ከእነ ህይወቱ በእሳት እንዲቃጠል ተደርጓል ፥ ታሪካዊቷ የአጣየ ከተማ በአብይ ትዕዛዝ ኦነግ እንዲያወድም አድርጎዋል ፥ ጎልጉል ፋሽስቱና ነፍሰ_ገዳዩ ህወሃት በውሸት ኮትኩቶ ያሳደጋቸው የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላቶች ጥርቅም ያሉበት ፍጹም ውሸታሞች ናቸው ፥ ታላቁን የአማራ ልጅ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስን ለመወንጀል የውሸት መዓት ለቃቅመው ያስቀመጡት ማንን ለማሳመን እንደሆነ እናውቃለን ፥ እንደ እናንተ ያለውን ውዳቂና ደካማ በዘረኝነት የተበከለ ውራጆች የሚሰማም የለም ፥ ከዛሬ ጀምሮ ይህንን የዘረኞች ድህረ_ገጽ unsubscribe አድርጌዋለሁ ፥ የኦሮሙማው ደንገጡሮች ስለሆናችሁ ገፃችሁን ማየት አልፈለግም ፡፡
Mesber says
አንተ ራስህ በአማራ ዘረኝነት ውስጥ ሆነህ ሌላውን ዘረኛ ትላለህ! አመድ በዱቀት ሳቀ እንደሚባለው
Tesfa says
ነጻ ህዝብ – ዝም ብሎ ጉልጉሎችን መዘንጠል ሥልጣኔ አይደለም። ረጋ ብሎ ነገሮችን ማየት ተገቢ ይሆናል። መረጃ ጠየቅን መረጃ አቀረቡ። ግንፍል ሃሳብ ለማንም አይጠቅምም። የሰከነና ነገሮችን ያመሳከረ እይታ ለአሁንም ለወደፊትም ይጠቅማል። አንተ ጎልጉሎችን ስትወነጅል ስሜታዊ የሆንክ ይመስለኛል። እርግጥ ነው ሃሳብህን/ሃሳብሽን የመግለጽ መብት ይኖራል። በሆነ ባልሆነው ነገር ሁሉ መራራ መሆን ግን ራስንም ይጎዳል። በመሰረቱ በጎልጉል የቀረበልን የሻለቃው ወንጀልና የመረጃ ጥንቅር በቂ አይደለም። ያው ግን ሻለቃውን አመድ ለመቀባት ይጠቅማል። እኔ ባጣራሁት መረጃ መሰረት ባንክ ውስጥ ያለ የእርዳታ ገንዘብ በአንድ ግለሰብ ብቻ ተፈርሞ የሚወጣ አለመሆኑን ነው። እንኳን 300 ሺህ ዶላር ቀርቶ ለኪስ የሚሆንም ገንዘብ በተናጠል ማውጣት አይቻልም። እኔ የህግ አዋቂ አይደለሁም። ግን የሃበሻውን ተንኮል ጠልቄ አውቀዋለሁ። ምን አልባት ዳዊት ወሰደው በማለት ራሳቸው የጊዜው ባለስልጣኖች ተከፋፍለውት ይሆናል። ማወቅ የሚገባን ደርግ ራሱ ከሶ ራሱ ፍርድ የሚሰጠጥ የዘመኑ የእብዶች ጥርቅም ለመሆኑ ባለቀ ሰዓት የመንግስት ለውጥ ለማድረግ የሞከሩትን ወታደራዊ መኮንኖች ያለ ፍርድ መረሸኑ በመሸ ሰአትም እንኳን ከራሱ ሌላ ለማንም እንደማያስብ ነው። የዚያ ዘመን ጦስ ነው ዛሬ እያባላን ያለው። ልብ ያለው ያስተውል።
ግራም ነፈሰ ቀን መረጃው ጎደሎ ነው። ምስክርነትም የሚጸናው በሶስት የአይን ምስክሮች ነው። አየንና ያኔ ነበርን የሚል ሰውም አልተገኘም። በእርግጥ ወጣ የተባለበት ባንክ፤ ሃገርንና ስፍራ ከታወቀ አሻራውን ለማየትም የሚቻል ይመስለኛል። ግን ይህ ሁሉ መዘባዘብ ነው። ከሞትና ከእስራት ከተረፉት የቀድሞ መኮንኖች መካከል ሻለቃ ዳዊት ሃገሩን የሚወድና አሁንም በሚችለው ሁሉ አስተዋጾ የሚያደርግ ወገን ነው። ምድሪቱ አሁን ምጥ ላይ ባለችበት የአስረሽ ምቺው ጊዜ እንዲህ አይነት በእድሜ የገፋን ነባርና ሃገር ወዳድ ሰው የሚያጠለሽ ነገር ጎልጉል መለጠፉ ብልህ አያደርጋቸውም። ይሁን እንጂ የድህረ ገጽ አዘጋጆች እነርሱ በመሆናቸው ለምን ብሎ ከመጠየቅ ያለፈ እጣት ቀስሮ ቃል መወራወሩ የድህረ ገጽን ገጽታ የመሸታ ቤት በራፍ ያስመስለዋል። አይበጅምና! ጎልጉሎች ብዙ ጠቃሚ ሃሳቦችን ያካፈሉን፤ አሁም የሚያካፍሉን ስለሆኑ ራስን ፍጽም ሰው አድርጎ ጎልጉልን በመኮነን መጨስ አይገባም። የሻለቃው ታሪክ እዚሁ ላይ ይዘጋ። በሌላ ጉዳይ እንደ ተለመደው በጠራ አቀራረባችሁ እንደማያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። ጎልጉሎች በርቱ። ነጻ ህዝብም ልብ ይስጥህ/ሽ። በምንሰማውና በምናነበው ሁሉ ከጨስን አንድ ቀን መንደዳችን አይቀሬ ነው። የሚተርፈው ያኔ አመድ ብቻ ይሆናል። ያ ደግሞ ለቀሪም ለቋሚም አይጠቅምም። እናስተውል። በቃኝ!