ሁሉም ባይባልም አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዋና የፖለቲካ ፕሮግራም ሶሻል ዴሞክራሲ ወይም ሊበራል ዴሞክራሲ ወይም ምርጫን ማዕከሉ ያደረገ ዴሞክራሲያዊ ፖሊሲ ነው። የኢኮኖሚ ፕሮግራማቸው ደግሞ ገበያ መር ኢኮኖሚ ነው። እነዚሁ ፓርቲዎች በምርጫ ክርክር ሲደረግ በዋናነት እያነሱ የሚከራከሩት መንግሥት ኢኮኖሚውን ተቆጣጥሮታል፤ የዕዝ ኢኮኖሚ ነው አገሪቱን ለችግር የዳረጋት፣ የኢኮኖሚው አካሄድ በገበያ እንጂ በመንግሥት መመራት የለበትም በሚል የከረረ ተቃውሞ በማቅረብ ሲቃወሙ ላለፉት በርካታ ዓመታት ሰምተናል። ባለፈው ሰኞ መንግሥት የአገሪቱን ዐቢይ (ማክሮ) ኢኮኖሚ ወደ ገበያ መር የሚወስድ ውሳኔ ይፋ ሲያደርግ እነዚሁ ተቃዋሚዎች “እሰይ ስለቴ ሰመረ” ባይሉም ቢያንስ ለዓመታት ሲሟገቱለት የነበረው ሃሳብ ድል አድርጎ በማየታቸው ጥንቃቄ የተሞላበት ድጋፍ ሊያሰሙ የሚጠበቅ … [Read more...] about “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አእምሮና የደም ዝውውር ሊኖረው ነው”