ኢትዮጵያዊያን በሀገራችው ሰማይ ስር የመጣን ጠላት በማሽመድመድ ካስመዘገቡት ደማቅ ታሪክ ፊት ለፊት ትልቁን ድርሻ ከሚወስዱት አንዱ ናቸው። ለሀገራቸው በዋሉት ውለታ ከሚተረክላቸው ቀዳሚ ባለ ታሪኮች ቀድመው ይጠቀሳሉ። ሙሉ ህይወታቸውን ለሀገራቸው የሰጡ ናቸው። ጀግና ተዋጊ፣ የበቁ የጦር መሪ፣ የተሳካላቸው የጦር አዛዥ ሆነው አገልግለዋል። በበርካታ የጦር ሜዳ ውጊያዎች ተሳትፈው የሀገርን ሉዓላዊነት፣ የህዝብን ነፃነት ያስከበረ ደማቅ ድል አስመዝግበዋል። ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ ሃብተማርያም። ጄኔራል መኮንኑ በ1934 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ከቸሀ ወረዳ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሲሰ መንደር ተወለዱ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውንም እዚያው እምድብር ከተማ ተምረው በ1948 ዓመተ ምህረትም አጠናቀዋል። ከ1949-1952 ዓ.ም ድረስ አምቦ የእርሻ ልማት … [Read more...] about “ውትድርና ሕይወቴ ነው”
general tesfaye
“ኢትዮጵያ በየዘመኑ ጀግና የምታፈራ የጀግኖች ሀገር ናት” ጀግናው ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም
ኢትዮጰያ በተለያዩ ጊዜያት ከውሰጥም ከውጪም በሚነሱ ጠላቶች ፈተና ቢገጥማትም በድል የምትሻገርና በየዘመኑ ጀግና የምታፈራ የጀግኖች ሀገር መሆኗን የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ወደር የሌለው ጀግንነት ሜዳይ ተሸላሚ ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ተናገሩ። ጀግንነት በኢትዮጵያውያን ደም ውስጥ ያለ ከአባት እናቶቻችን የወረስነው ዕሴታችን ነው ብለዋል። ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት ኢትዮጰያ በተለያዩ ጊዜያት ከውሰጥም ከውጪም በሚነሱ ጠላቶች ምክንያት የተለያዩ ጦርነቶችን አድርጋለች። በእንደዚህ ፈታኝ ጊዜያት ህዝቡ ወደጦር ግንባር የሚሄደው ተለምኖ ሳይሆን ሀገሬ ስትወረር ቁጭ ብዬ አለይም በማለት በራሱ ፍላጎትና ተነሳሽነት በነቂስ በመውጣት ተካፍሎ ብዙ አኩሪ የጀግንነት ታሪኮችን የፈጸመና እየፈጸመ ያለ ነው ብለዋል። ወጣቱ … [Read more...] about “ኢትዮጵያ በየዘመኑ ጀግና የምታፈራ የጀግኖች ሀገር ናት” ጀግናው ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም