
ኢትዮጰያ በተለያዩ ጊዜያት ከውሰጥም ከውጪም በሚነሱ ጠላቶች ፈተና ቢገጥማትም በድል የምትሻገርና በየዘመኑ ጀግና የምታፈራ የጀግኖች ሀገር መሆኗን የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ወደር የሌለው ጀግንነት ሜዳይ ተሸላሚ ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ተናገሩ።
ጀግንነት በኢትዮጵያውያን ደም ውስጥ ያለ ከአባት እናቶቻችን የወረስነው ዕሴታችን ነው ብለዋል።
ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት ኢትዮጰያ በተለያዩ ጊዜያት ከውሰጥም ከውጪም በሚነሱ ጠላቶች ምክንያት የተለያዩ ጦርነቶችን አድርጋለች። በእንደዚህ ፈታኝ ጊዜያት ህዝቡ ወደጦር ግንባር የሚሄደው ተለምኖ ሳይሆን ሀገሬ ስትወረር ቁጭ ብዬ አለይም በማለት በራሱ ፍላጎትና ተነሳሽነት በነቂስ በመውጣት ተካፍሎ ብዙ አኩሪ የጀግንነት ታሪኮችን የፈጸመና እየፈጸመ ያለ ነው ብለዋል።

ወጣቱ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ጀግንነት በደሙ ውስጥ ያለ መሆኑን አስመስክሯል ያሉት ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ ኢትዮጵያን በዚህ መልኩ የሚገዳደራት ሀይል ሲመጣ ያለማንም ቀስቃሽ ሆ ብሎ በመውጣት የሀገር ፍቅሩን በሚገባ አሳይቷል።
ለዚህም መላው የሀገሪቱ ህዝብ ትልቅ ኩራት ሊሰማውና ተስፋ ሊሰንቅ እንደሚገባም ገልጸዋል።
የሀገሪቱን አድገት ጎታች ሆኖ ፈተና ውስጥ የከተተን ነገር የእናት ጡት ነካሽ በሆኑ ከሀዲዎች የተከፈተብን ጦርነት ነው። ይህንን የህልውናችንን ጠላት ለመዋጋት ደግሞ ወጣቱ ከጦር ሜዳው ተሳትፎ ባልተናነሰ መልኩ መነሳትና አንድነት መፍጠር ይኖርበታል ብለዋል። (ኢፕድ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply