በ116ኛው የሠራዊት ቀን ሲከበር ንግግር ያደረጉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ “ዐጼ ምኒልክ የጦር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ያቋቋሙበትን ቀን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን ኾኖ እንዲከበር ተደርጓል” በማለት ቀኑ ለምን እንደተመረጠ ይፋ አደረጉ። ከዚህ ሌላ ፊልድ ማርሻሉ በንግግራቸው፤ ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ ከጀግኖች የተረከብናትን ኢትዮጵያ እንደተከበረች እና ማንነቷ እንደተጠበቀ ለማስቀጠል ወታደራዊ ዝግጁነታችንን አሳድገንና ቁመናችንን አዘምነን ማንኛውንም ተልዕኮ በላቀ ብቃት ለመፈጸም ሠራዊቱ ዝግጁ መሆኑን አሣውቀዋል። የሠራዊቱ አባላት የተሠጣቸውን ታላቅ አደራ በድል ለመወጣት የመፈጸም ብቃታቸውን በማሣደግ በዓላማ ጽናታቸው እንዲቀጥሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አሳስበዋል፡፡ ሠራዊቱ ሀገሩን እና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን … [Read more...] about የኢትዮጵያ መከላከያ መሥራች አጼ ምኒልክ መሆናቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናገሩ
116 anniversary of endf
ጥቅምት 15 ለምን?
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በአዲስ መልክ ጥቅምት 15 ቀን ላይ መከበሩ ለምን እንደሆነ ከዚህ በታች ለመረዳት እንዲቻል በቀላሉ የተሠራውን መግለጫ ይመልከቱ። ስለ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የማዕረግ ምልክቶች ምን ያህል ያውቃሉ? ከ"ፊልድ ማርሻል ጄነራል" ጀምሮ እስከ "ምክትል አስር ዓለቃ" ድረስ በአጠቃላይ 18 ማዕረጎች ይገኛሉ። የማዕረጎቹን ዝርዝር ከነምልክቱ እነሆ፦ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ጥቅምት 15 ለምን?
“በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት”
"በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት " በሚል መሪ ቃል ለሚከበረው ለዘንድሮ ለ116ኛው የሠራዊት ቀን እንኳን በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን። እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ የረዥም ዓመታት ሀገርን ከጠላት የመከላከል የተጋድሎ ታሪክ ካላቸው ሀገራት መካከል በጀግኖች ልጆቿ የአይበገሬነት ፊት የምትሠለፍ ታሪካዊት ሀገር ናት። ከቀደመው ዘመን ጀምረን አሁን ላይ ያለውን እውነታ እንኳ ብንቃኝ ኢትዮጵያ በርካታ የውጪ ወራሪ ሀገራት ያሠፈሠፉባት ጥቂት የማይባሉ የውስጥ እርስ በርስ ግጭቶች የተከሰቱባት በባንዳዎች የተፈተነችበትና በየትኛውም ዘመን ያልተንበረከከች የወራሪዎችን ፈተና አልፋ ዛሬ ላይ የደረሠች ሥለመሆኗ የታሪክ ድርሳናት መዝግቧል። በሀገራችን የጀግንነት የታሪክ መዝገብ ያልሠፈሩ ግን ደግሞ አለም ያወቃቸው ቱባ ባህሎችና ድንቅ ታሪኮች ያላት ኢትዮጵያ በታሪክ … [Read more...] about “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት”