የዛሬዋ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ስበት ማዕከል የሆነው አፄ ምኒልክ ዘመን ተሻጋሪ ውርሶች ለዘመናዊት ኢትዮጵያ ጥሎ አልፏል። ዘመናዊት ኢትዮጵያ ስንል ከጨረቃ የመጣች እያልን ሳይሆን ግዛታዊ ቅርጿ ሲጠብና ሲሰፋ የነበረችው ኢትዮጵያ በአንጻራዊ ዝማኔ መመራት የጀመረችበት አስተዳደራዊ ዘመን መገለጫ ማለታችን ነው። የዛሬዋ ኢትዮጵያ መልከዓ ምድራዊ ቅርጽ ከሞላ ጎደል የአፄው የንግሥና ዘመን ውጤት ናት። ከምንም በላይ የጥቁር ዘር የነጻነት ምልክት የሆነው የአድዋ ድል በምኒልክ መሪነት የመጣ ነው። በርግጥ ድሉ የአባቶቻችን የመደማመጥና የመተባበር ውጤት ነው። ምኒልክን አልባ የአድዋን ድል ማስመዝገብ ይቻል (ይሆን) ነበር ብሎ ማመን ይቻላል። ይሁንና በታሪክ የምናውቀውን የአድዋን ድል ያለ ምኒልክ ማሰብ ክርስትናን ያለክርስቶስ፣ እስልምናን ያለነብዩ መሐመድ እንደማሰብ ያለ ቅዥት ነው። ይህ … [Read more...] about ምኒልክ የድል መንፈስ!
emiye menelik
ምኒልክን ከዓድዋ ለመነጠል መሞከር ባርነት መምረጥ ነው
ጀግንነቱን ዓለም መስክሮለታል፣ ስሙን ከፍ አድርጎ ጠርቶታል፣ ታሪክ በማይጠፋ ቀለም፣ በማያረጅ ብራና አስፍሮታል፡፡ ጠላት ሮጦለታል፣ በስሙ ተሸብሮለታል፣ ከእግሩ ሥር ወድቆ ይማሩኝ ንጉሥ ኾይ ብሎለታል፡፡ በጀግንነቱ በጠላቶቹ ልብ ላይ የነገሠ፣ በዝናው ዓለምን ያዳረሰ፣ የጠላቶቹን አንጀት የበጠሰ፣ የወዳጆቹን አንጀት ያራሰ ጀግና ነው እርሱ፡፡ የማይገመት ልብ ያለው፣ ጠላት የማይችለው፣ ጀግንነት፣ ብልሃት፣ አሸናፊነትና ጽናት የታደለው ኃያል ንጉሥ፡፡ ነጭ ባየለበት ዘመን በነጭ ላይ የገነነ፣ የነጭን ኃያልነት የበጣጠሰ፣ የነጭን አብዮት ያፈራረሰ፣ የጥቁርን ክብር የመለሰ፣ ያለቀሱትን እንባቸውን ያበሰ፣ በጨለማ ውስጥ ለነበሩት የደረሰ፣ በድል ብቻ የገሰገሰ፣ በጨለማው ምድር ብርሃን ያበራ፣ ከተራራ የገዘፈ፣ ዘመናትን በክብር ያለፈ ታሪክ የሠራ፣ የጥቁር አባት፣ የነጻነት መሪ፣ … [Read more...] about ምኒልክን ከዓድዋ ለመነጠል መሞከር ባርነት መምረጥ ነው