በአዲስ አበባ እምብርት ፒያሳ፤ የሚኒሊክ ሀውልት እና የአራዳው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚያዋስኑት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው። በቅርቡ ከታደሰው እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ከሚገኝበት ማዘጋጃ ቤት ጋር ደግሞ በድልድይ ተገናኝቷል። እስከ ዛሬ ድረስ የራሱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሳይኖረው የቆየው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትም ቋሚ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚያገኘው በዚህ ፕሮጀክት ነው። እየተጠናቀቀ ያለው ይህ ፕሮጀክት ሁለት ሺህ ሰዎችን የሚይዝ የከተማ አዳራሽም በውስጡ ይዟል። ከሁሉም በላይ ግን የዓድዋ ሙዚየም ፕሮጀክት ግዙፍነት የሚነሳው ሊዘክረው ካሰበው ታሪካዊ ሁነት ነው። ይህ ግዙፍ መንግሥታዊ ፕሮጀክት፤ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት በተለየ የኢትዮጵያን ነጻነት ያስጠበቀው እና በተለያዩ አገራት የፀረ ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴን ያነሳሳው የዓድዋ ድል መታሰቢያ … [Read more...] about ስለ ዓድዋ ሙዚየም ዋና አርኪቴክቱ ምን ይላል?
adwa
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ ይመረቃል
ኢትዮጵያ ነጻነቷን ጠብቃ እንድትኖር ያደረጓት አባቶቻችንን የሚዘክር የዓድዋ ድል መታሰቢያ በአዲስ አበባ ፒያሳ ተገንብቶ ዛሬ ይመረቃል። መታሰቢያው የተገነባው ጀግኖች ወደ ጦርነቱ ሲተሙ በአንድነት ተሰባስበው ጉዟቸውን የጀመሩበት ቦታ ላይ ነው። የዓድዋ ድል መታሰቢያ ላይ የሚታየው 00 ኪሎ ሜትር መነሻ ቦታ የኮምፓስ ምልክት በአዲስ አበባ እንዲሁም በመላ ኢትዮጵያ ለሚገኙ ቦታዎች የርቀት መለኪያ መነሻ ነው። የዓድዋ ድል መታሰቢያ በ5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን 5 ወለል እና 8 በሮች አሉት። አጠቃላይ ከታች እስከ ላይ በ5ቱ ወለል ላይ ያለዉ መሬት ስፋት 12 ሄክታር ነው። ሙዚየሙ ከምድር በታች ያለውን ሁለት ደረጃዎችን ጨምሮ 5 ወለሎች አሉት። ከ1 ሺህ በላይ የመኪና ማቆሚያ፣ ሲሲቲቪ ካሜራ፣የራሱ መቆጣጠሪያ ያለው ስማርት ፓርኪን ሥርዓት … [Read more...] about የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ ይመረቃል
ምኒልክን ከዓድዋ ለመነጠል መሞከር ባርነት መምረጥ ነው
ጀግንነቱን ዓለም መስክሮለታል፣ ስሙን ከፍ አድርጎ ጠርቶታል፣ ታሪክ በማይጠፋ ቀለም፣ በማያረጅ ብራና አስፍሮታል፡፡ ጠላት ሮጦለታል፣ በስሙ ተሸብሮለታል፣ ከእግሩ ሥር ወድቆ ይማሩኝ ንጉሥ ኾይ ብሎለታል፡፡ በጀግንነቱ በጠላቶቹ ልብ ላይ የነገሠ፣ በዝናው ዓለምን ያዳረሰ፣ የጠላቶቹን አንጀት የበጠሰ፣ የወዳጆቹን አንጀት ያራሰ ጀግና ነው እርሱ፡፡ የማይገመት ልብ ያለው፣ ጠላት የማይችለው፣ ጀግንነት፣ ብልሃት፣ አሸናፊነትና ጽናት የታደለው ኃያል ንጉሥ፡፡ ነጭ ባየለበት ዘመን በነጭ ላይ የገነነ፣ የነጭን ኃያልነት የበጣጠሰ፣ የነጭን አብዮት ያፈራረሰ፣ የጥቁርን ክብር የመለሰ፣ ያለቀሱትን እንባቸውን ያበሰ፣ በጨለማ ውስጥ ለነበሩት የደረሰ፣ በድል ብቻ የገሰገሰ፣ በጨለማው ምድር ብርሃን ያበራ፣ ከተራራ የገዘፈ፣ ዘመናትን በክብር ያለፈ ታሪክ የሠራ፣ የጥቁር አባት፣ የነጻነት መሪ፣ … [Read more...] about ምኒልክን ከዓድዋ ለመነጠል መሞከር ባርነት መምረጥ ነው
፻፳፮ኛው የዓድዋ በዓል በፎቶ
“… የተተከለው ድንኳን ሲታይ ከብዛቱ የተነሳ አፍሪካ ኤሮጳን ለመጠራረግ የተነሳች ይመስላል፡፡ የጦርነቱ ዕለት ኢትዮጵያውያኑ ደማቅ ቀለም ያለው ካባ ለብሰው፤ ጠመንጃና ጦር ይዘው፤ ጎራዴ ታጥቀው፤ የነብር ያንበሳ ቆዳ ለብሰው፤ አዝማሪዎቹ እየዘፈኑ፤ ቄሶች፤ ልጆች፤ ሴቶች ሳይቀሩ ፀሐይዋ ፈንጠቅ ስትል በተራራው ላይ በታዩ ጊዜ የኢጣሊያን ክፍል አሸበሩት” የበርክለይ ምስክርነት፤ አጤ ምኒልክ በጳውሎስ ኞኞ፤ ገጽ 195 ዛሬ የተከበረው ፻፳፮ኛው የዓድዋ በዓል በእምዬ ምኒልክ አደባባይና በተለያዩ አካባቢዎች ተከብሯል። በፎቶ ይህንን ይመስላል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ፻፳፮ኛው የዓድዋ በዓል በፎቶ
125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው
125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በሰፊው ታስቦ እንደሚውል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገልጿል።125ኛው የአድዋ በዓል ከየካቲት 1 ቀን እስከ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።በዓሉ ሲከበር በወረዳዎች በመሰረተ ልማት ቦታዎች ላይ የጀግኖች ስም የሚሰየም እንደሚሆንና የመደመር የኪነጥበብ ትርኢቶች እደሚዘጋጁ የምሁራንና የህዝብ የውይይት መድረኮችም እንደሚካሄዱአድዋን ለአባይ በሚል መሪ ሀሳብም የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይካሄዳልም ሲሉ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሰው ዛሬ ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ወቅት ገልጸዋል፡፡የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የአድዋ ድል 125ኛ ዓመት አከባበር መለያ አርማ (Logo) ይፋ አድርጓል፡፡የአርማው መግለጫ፦- ጋሻ ጎራዴና ጦር፦ አባቶቻችን ጠላትን የተዋጉባቸው የጦር መሳሪያዎች፤- … [Read more...] about 125ተኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ሊከበር ነው