• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ምኒልክን ከዓድዋ ለመነጠል መሞከር ባርነት መምረጥ ነው

March 4, 2022 12:18 am by Editor Leave a Comment

ጀግንነቱን ዓለም መስክሮለታል፣ ስሙን ከፍ አድርጎ ጠርቶታል፣ ታሪክ በማይጠፋ ቀለም፣ በማያረጅ ብራና አስፍሮታል፡፡ ጠላት ሮጦለታል፣ በስሙ ተሸብሮለታል፣ ከእግሩ ሥር ወድቆ ይማሩኝ ንጉሥ ኾይ ብሎለታል፡፡ በጀግንነቱ በጠላቶቹ ልብ ላይ የነገሠ፣ በዝናው ዓለምን ያዳረሰ፣ የጠላቶቹን አንጀት የበጠሰ፣ የወዳጆቹን አንጀት ያራሰ ጀግና ነው እርሱ፡፡

የማይገመት ልብ ያለው፣ ጠላት የማይችለው፣ ጀግንነት፣ ብልሃት፣ አሸናፊነትና ጽናት የታደለው ኃያል ንጉሥ፡፡

ነጭ ባየለበት ዘመን በነጭ ላይ የገነነ፣ የነጭን ኃያልነት የበጣጠሰ፣ የነጭን አብዮት ያፈራረሰ፣ የጥቁርን ክብር የመለሰ፣ ያለቀሱትን እንባቸውን ያበሰ፣ በጨለማ ውስጥ ለነበሩት የደረሰ፣ በድል ብቻ የገሰገሰ፣ በጨለማው ምድር ብርሃን ያበራ፣ ከተራራ የገዘፈ፣ ዘመናትን በክብር ያለፈ ታሪክ የሠራ፣ የጥቁር አባት፣ የነጻነት መሪ፣ የጨለማ ዘመን አሻጋሪ፣ የአሸናፊነትን ድል አብሳሪ ነው ኃያሉ ንጉሥ፡፡

በደል ያልተገኘባቸው የአፍሪካ ሀገራት በበደለኞች እጅ ወድቀው ነበር፡፡ ቀኝ ገዢዎች በእርስታቸው በተቀመጡት ደጋግ ሕዝቦች ላይ ተነስተው የግፍ ግፍ ይፈጽማሉ፡፡ ሰዎችን እንደ ሸቀጥ ይሸጣሉ፣ ይለውጣሉ፡፡ እያሰሩ አያሌ በደሎችን ይፈጽማሉ፡፡ ባለ እርስት የሆኑት ጥቁሮች በባዕዳን መከራው ጠንቶባቸዋል፡፡ በበደለኞች ተገፉ፣ ተዳፉ፡፡ አፍሪካን የመከራና የስቃይ ምድር አድርገው ኃያልነታቸውን ማስፋት ፈለጉ፡፡ ኃያል ያደርገናል ያሉትን ሁሉ በአፍሪካ ምድር ላይ ፈፀሙ፡፡ ብዙዎችን ያለ በደላቸው በቀያቸውና በእርስታቸው በግፍ ገደሉ፡፡

አፍሪካን የደም ምድር አደረጓት፣ ብርሃኗን ነጥቀው በጨለማ ውስጥ እንድትኖር ፈረዱባት፣ ማንነቷን ወስደው የማይመስላትን ማንነት ልበሽ አሏት፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ታዲያ ጨለማ ያልደረሰባት፣ የባዕድ ማንነት ያልነካካት፣ ጨለማ የማይደፍራት፣ ብርሃን የከበባት፣ ጀግና ልጆች ያሏት፣ ደፋር ኩሩ ንጉሥ የነገሠባት ምድር ነበረች፡፡ በጨለማው መካከል ብርሃን ያበራች፣ በጠላት ያልተደፈረች፣ በደምና በአጥንት የተጠበቀች፣ ጀግና ልጆችን የወለደች ወልዳም ያሳደገች ምድረ ቀደምት ሀገር ናት፡፡

ጠላቶች እንደሌሎቹ ሁሉ ሊያጠፏት፣ ክብሯንና ማንነቷን ሊነጥቋት ወደ እርሷ ወሰንም ዘለቁ፡፡ እነዚያ የሮም መሪዎች ነጻ የሆነችው ሀገር ነጻነቷን ሊነጥቋት ቋመጡ፡፡ በሌሎች ሀገራት ድል ለምደዋልና በኢትዮጵያ ሰማይ ሥርም በድል እንደሚንበሸበሹ ተማምነዋል፡፡ ዳሩ ኢትዮጵያ ከሁሉም ትለያለች፣ ለአሸናፊነት የተፈጠረች እንጂ መሸነፍ በፍጹም አይነካካትም፡፡

በጦር ወግቶ ማሸነፍ ለእርሷ ብቻ የተፈጠረ እስኪመስል ድረስ በየዘመናቱ የተነሱትን ጠላቶቿን እየወጋች ድባቅ እየመታች ኖራለችና ማንም ቢነሳ አትበገርም፡፡ የጠላትን ፉከራና ድንፋታ አስቀድማ ሰምታ ነበር፡፡ ንጉሡ ምኒልክም የሀገሬው ሕዝብ ለዘመቻ እንዲነሳ በማርያም ምሎ አዋጅ አስነገረ፡፡ እንኳን በአዋጅ ተጠርቶ እንዲያውም ለሀገሩ መዝመት የሚወደው የሀገሬው ሰው የንጉሡን ቃል ከያለበት ሰምቶ ተንቀሳቀሰ፡፡

የሮም ሠራዊት በአፍሪካ ምድር የምታበራዋን ብኛዋን መብራት አጥፍቶ፣ አፍሪካን በድቅድቅ ጨለማ ሲያስውጣት ለማዬት የጓጉ የኢጣልያ ወዳጆች የድሉን ዜና ለማስማት ቸኮሉ፡፡

ድል ፈጽማ ከኢጣልያ ሠራዊት እንደማትርቅ ተማምነዋል፡፡ ጥያቄው ድሉ የሚበሰረው መቼ ነው የሚለው ነው፡፡ አይደርስ የለም ያ ቀን ደረሰ፡፡ ኢትዮጵያውያን ሳይደርሱባቸው አይደርሱም እንጂ ከደረሱባቸው አመላለሱን ያውቁበታል፡፡

አውግስቶስ ቄሳር በሮም ነግሦ በነበረበት በዚያ ዘመን ሮም ቁጥራቸው የበዙ የዓለም ሀገራትን አስገብራ ነበር፡፡ ይህም ንጉሥ ተከብራ እንጂ ተደፍራ የማታውቀውን ሀገር ኢትዮጵያን ለመውረር አይሎስ ጋሎስ በሚባል የጦር አበጋዙ የሚመራ ሠራዊት ወደ ኢትዮጵያ ምድር ላከ፡፡ ያም ዘመን ከክርስቶስ ልደት አስቀድሞ በ29 ዓ.ዓ እንደበር ይነገራል፡፡ በዚያ ዘመን ኃያል የነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት ፈጽሞ ለጠላት የሚቀመስ አልነበረም፡፡ የአይሎስ ጋሎስ ሠራዊትም ከንጉሡ በታዘዘው መሠረት የኢትዮጵያን ወሰን ለመድፈር ጦርነት ከፈተ፡፡ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ሀገር ሊወር የመጣውን ጠላት ነዲድ እሳት ሆነው ጠበቁት፣ እንደ አመጣጡ እየለበለቡ አቃጠሉት፡፡

አውግስቶስ ቄሳር ያሰበው ሳይሳካ ሠራዊቱን አስጨረሰ፡፡ ከኢትዮጵያውያን ጦርና ጎራዴ የተረፈውን ሠራዊት ይዞ እንዲመለስ ለአይሎስ ጋሎስ ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡

ከኢትዮጵያውያን ጎራዴ የተረፈው ሠራዊትም ብዙዎችን በጎራዴ አስበልቶ፣ በሳንጃ አስወግቶ፣ በበረሃ ትቶ በሐዘን ወደሀገሩ ተመለሰ፡፡

በአውግስቶስ ቄሳር ዘመን የደረሰባቸውን ሽንፈት ያካክሱ ዘንድ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ54 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ሌላ ወራሪ ሠራዊት ላኩ፡፡ በዚያም ዘመን የነገሰው ኔሮ ነበር፡፡ እርሱም ኢትዮጵያን አስገብራታለሁ ሲል ፎክሮ ተነሳ፡፡ አማካሪዎቹ ኢትዮጵያውያንን ማስገበር ፈጽሞ እንደማይቻል አስቀድመው ነገሩት፡፡ እርሱ ግን አሻፈረኝ አለ፡፡ መጣም ተሸንፎ ተመለሰ፡፡

ከአባቶቻቸው የወረሱትን የዘር ሽንፈት ልጆቹ ሊደግሙ በዘመነ ምኒልክ ኢትዮጵያን ሊወሩ ገሰገሱ፡፡ ምኒልክም ሠራዊቱን አስከትሎ፣ ጀግኖቹን የጦር አበጋዞችን ይዞ፣ ከብርሃን ዘ ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ጋር ጠላት ወዳለበት ገሰገሰ፡፡ በዚያም ጠላትን ድባቅ መታው፡፡ ከዘር የመጣው የኢጣልያ ሽንፍትም በዓድዋ ከፍ ብሎ ተሰማ፡፡ ኢጣልያ አፈረች፣ ኮሰመነች፣ የአፍሪካን ብቸኛ ብርሃን ልታጠፋ ስትቋምጥ የራሷን ብርሃን አጠፋች፣ በዓለም ፊት ተዋረደች፣ ምኒልክ ኃያላን ነን በሚሉት ሁሉ ተፈራ፤ ተከበረ፡፡

በአንድ ጀንበር ዓድዋ ላይ የዓለም ታሪክ ተቀየረ፡፡ አፍሪካ መውጫ ብርሃኗን ከወደ ኢትዮጵያ አየች፡፡ በዚያ መንገድም ለመጓዝ ተነሳች፡፡ ታላቁ ንጉሥ በዓድዋ ተራራ ላይ ጠላትን እንዳልነበር አደረገ፡፡

የኢጣልያ ሠራዊት አብዛኛው በኢትዮጵያውያን ጎራዴ ተበልቶ ላይመለስ አሸለበ፡፡ የቀረው እጁን ሰጠ፡፡ ጥቂቱም ፈርጥጦ አመለጠ፡፡ ጀግና አስታወይና ብልህ ነውና ምኒልክ የኢጣልያ ምርኮኞች በሰላም እንዲኖሩ አደረገ፡፡

ኒኮላስ ኒዎንቲቭን ጠቅሰው ጳውሎስ ኞኞ ሲጽፉ ʺ ንጉሡ ድል ማድረጋቸውን እንዳወቁ እጅ የሰጡትን ጣልያኖች ሠራዊታቸው እንዳይገድል አስጠነቀቁ፡፡ እንስራ ተሸክመው ለሠራዊቱ ውኃ ያቀብሉ የነበሩ የኢትዮጵያ ሴቶች ሁሉ ሸክማቸውን እያስቀመጡ ምርኮኞቹን በማገዝ ይረዱ ጀመር፡፡ አስክሬኖች በብዛት ተከምረዋል፡፡ በሜዳው ላይ በትንሹ ይወርድ የነበረው ደም ወደ ወንዝነት ተለውጧል” ብለዋል፡፡

ምኒልክ በጠላቶቹ ላይ አይጨክንም፡፡ መሸነፋቸውን አውቀው እጅ ከሰጡ ይንከባከባቸዋል እንጂ፡፡ ጀግና እጁን በሰው ክብር ላይ የሚዘረጋውን ይቀጣል እንጂ እጅ የሚነሳውን አይቀጣም ምኒልክም ጀግና ነውና ጠላት ስለሆኑ ብቻ ይገደሉ አላለም፡፡ ለምርኮኞች እንክብካቤ እንዲደረግ አዘዘ እንጂ፡፡

ʺበዚያ ጊዜ ምኒልክ አንድ መጠለያ አቋቁመው ስለነበር ልብስ፣ ምግብና ውኃ ይሰጣል፡፡ ለቁስለኞችም የሕክምና እርዳታ ይደረግ ነበር፡፡ የቆሰሉት ምርኮኞች የሚጓዙበት ተሰጥቷቸዋል” ሲሉ ጳውሎስ ግሊከንን ዋቢ አድርገው ጽፈዋል፡፡ ምኒልክ ጀግና ብቻ ሳይሆኑ ሩህሩህም ናቸው፤ ቆፍጣና እንጂ ጨካኝ አይደሉም፡፡

“እርር ቅጥል ቢሉም የእርሱ ጠላቶቹ፣
ምኒልክ ጀግና ነው እስከ ዘመዶቹ”

ባሕር ዳር: የካቲት 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, Opinions Tagged With: 126 adaw, adwa, emiye menelik, menelik

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule