ጀግንነቱን ዓለም መስክሮለታል፣ ስሙን ከፍ አድርጎ ጠርቶታል፣ ታሪክ በማይጠፋ ቀለም፣ በማያረጅ ብራና አስፍሮታል፡፡ ጠላት ሮጦለታል፣ በስሙ ተሸብሮለታል፣ ከእግሩ ሥር ወድቆ ይማሩኝ ንጉሥ ኾይ ብሎለታል፡፡ በጀግንነቱ በጠላቶቹ ልብ ላይ የነገሠ፣ በዝናው ዓለምን ያዳረሰ፣ የጠላቶቹን አንጀት የበጠሰ፣ የወዳጆቹን አንጀት ያራሰ ጀግና ነው እርሱ፡፡ የማይገመት ልብ ያለው፣ ጠላት የማይችለው፣ ጀግንነት፣ ብልሃት፣ አሸናፊነትና ጽናት የታደለው ኃያል ንጉሥ፡፡ ነጭ ባየለበት ዘመን በነጭ ላይ የገነነ፣ የነጭን ኃያልነት የበጣጠሰ፣ የነጭን አብዮት ያፈራረሰ፣ የጥቁርን ክብር የመለሰ፣ ያለቀሱትን እንባቸውን ያበሰ፣ በጨለማ ውስጥ ለነበሩት የደረሰ፣ በድል ብቻ የገሰገሰ፣ በጨለማው ምድር ብርሃን ያበራ፣ ከተራራ የገዘፈ፣ ዘመናትን በክብር ያለፈ ታሪክ የሠራ፣ የጥቁር አባት፣ የነጻነት መሪ፣ … [Read more...] about ምኒልክን ከዓድዋ ለመነጠል መሞከር ባርነት መምረጥ ነው