በዳግማዊ ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው እና በቀን እስከ 35 ወይም በሳምንት ለ100 ያህል ዜጎች አገልግሎት ይሰጣል የተባለው የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
ማዕከሉ በዳግማዊ ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል ዓለም ዐቀፍ ደረጃውን ባሟላው አዲስ ህንፃ ላይ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ ነው የተገለፀው።
በኩላሊት ህመም ለሚሰቃዩ ወገኖች ትልቅ እፎይታ ይሰጣል የተባለለት ማዕከሉ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎች በነፃ አገልግሎቱን በመስጠት ተስፋ እንደሚሆንም ተጠቁሟል።
ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ማዕከሉ በዛሬ ዕለት (ሰኞ) ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ይመረቃል። (አዲስ ሚዲያ)
ማስተካከያ፤ ይህ ዜና በተለጠፈበት ቀን እጥበት ማዕከሉ በሳምንት 240 ሺ ሕሙማንን ያስተናግዳል ነበር የሚለው። ቁጥሩ በወቅቱ አሳማኝ ባይሆንልንም ከመንግሥትም ሆነ ከግሉ ሚዲያ ያገኘነው መረጃ ከዚህ ውጭ አልነበረም። አሁን ግን ከእጥበት ማዕከሉ ባገኘነው መረጃ መሠረት በቀን እስከ 30 በሽተኞችን የሚያስተናግድ ሲሆን ቁጥሩ በሳምንት ከ100 እንደማይበልጥ ተነግሮናል። ይህም ሕክምናው ወይም እጥበቱ የሚካሄደው በሳምንት ሦስት ቀናት ማለትም ሰኞ፣ ረቡዕና አርብ ሲሆን ሌሎቹን ቀናት ማዕከሉ ልዩ ነርሶችን ለማሰልጠንና የጎደሉ ዕቃዎችን በመተካት ለቀጣዩ ቀን እጥበት የሚዘጋጅበት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Mesber says
I think the numbers given might be wrong. 35,000 persons per day and 240000 persons per week? If we assume one machine can serve 6 persons in 24 hours, then there must be over 5800 dialysis machines. Is it possible? If this data is correct then there are over 12 million persons with kidney disease.
Editor says
Dear Mesber
Thanks for the comment. We were not confident even when we posted the news. But it was posted like that by almost all private and public media outlets.
Our effort to find out the correct number was not successful at the time. However, we have confirmed from the center that the daily maximum capacity is 30 patients. And dialysis is provided only three days a week: Mondays, Wednesdays and Fridays. The Center needs the other days to train special nurses and refill resources and prepare for the next dialysis. So the weekly maximum capacity is not over 100 patients.
Editor