• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ ይመረቃል

February 11, 2024 04:04 am by Editor Leave a Comment

ኢትዮጵያ ነጻነቷን ጠብቃ እንድትኖር ያደረጓት አባቶቻችንን የሚዘክር የዓድዋ ድል መታሰቢያ በአዲስ አበባ ፒያሳ ተገንብቶ ዛሬ ይመረቃል።

መታሰቢያው የተገነባው ጀግኖች ወደ ጦርነቱ ሲተሙ በአንድነት ተሰባስበው ጉዟቸውን የጀመሩበት ቦታ ላይ ነው።

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ላይ የሚታየው 00 ኪሎ ሜትር መነሻ ቦታ የኮምፓስ ምልክት በአዲስ አበባ እንዲሁም በመላ ኢትዮጵያ ለሚገኙ ቦታዎች የርቀት መለኪያ መነሻ ነው።

የዓድዋ ድል መታሰቢያ በ5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን 5 ወለል እና 8 በሮች አሉት። አጠቃላይ ከታች እስከ ላይ በ5ቱ ወለል ላይ ያለዉ መሬት ስፋት 12 ሄክታር ነው።

ሙዚየሙ ከምድር በታች ያለውን ሁለት ደረጃዎችን ጨምሮ 5 ወለሎች አሉት። ከ1 ሺህ በላይ የመኪና ማቆሚያ፣ ሲሲቲቪ ካሜራ፣የራሱ መቆጣጠሪያ ያለው ስማርት ፓርኪን ሥርዓት አለው።

በአንድ ጊዜ 2 ሺህ 500 ሰዎችን መያዝ የሚችል የፓንአፍሪካኒዝም አዳራሽ፣ 2 ሺህ 300 ሰዎችን መያዝ የሚችል ዘመናዊ ሁለገብ አዳራሽ፣ 4 ሺህ ሰዎችን መያዝ የሚችል የቤት ውስጥ የስፖርት ሜዳ እና አዳራሽ ይዟል።

የህፃናት መጫወቻ፣ የንግድ ሱቆች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ፣ ካፌና ሬስቶራንት፣ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቢሮዎች እና የአርት ጋላሪ አለው።

ለዓድዋ ጦርነት ሰበብ የሆነው የውጫሌ ውል አንቀፅ 17ን እንዲሁም ከድሉ በኋላ የአዲስ አበባ ውል በሚል ኢትዮጵያ እና ጣሊያን ካደረጉት ስምምነት ውስጥ ሁለት አንቀፆች ይገኙበታል። እነሱም ኢትዮጵያ ሉዓላዊ አገር መሆኗን እና የውጫሌ ውል በዚህ ውል መሰረዙን፣ የውጫሌው ውል ምንም የሕግ ውጤት እንደማይኖረው የሚያረጋግጡ አንቀፆች ናቸው።

የዓድዋ ድል ታሪክን የኢትጵዮያዊነት እሴቶችን የሚገልፁ ቅርፃ ቅርፆች፣ የሥዕል ሥራዎች ለእይታ ቀርበዋል።

መታሰቢያው እያንዳንዳቸው 280 ሰዎችን መያዝ የሚችሉ 2 ሲኒማ ቤቶች አሉት። ቤተመጻሕፍት፣ የቤት ውስጥ ውድድሮች ሜዳ፣ የህፃናት መጫወቻ ስፍራ እና ጂምናዚየም ተሰርቶለታል።

የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓንአፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ስምንት በሮች አሉት።

በ4ቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል። የአንድነት ድልድይ ሙዚየሙን ከማዘጋጃ ቤቱ ጋር እንዲያገናኝ ታስቦ የተሰራ እና ትናንት ከዛሬ ዛሬን ከነገ ያሚያገናኝ ነው።

የኢትዮጵያ ታሪክን፣ የባህል አሻራዎችን፣ የጦር ሜዳ ስፍራዎችን የሚያሳዩ እና የዓድዋ ድል የክተት አዋጅ የታወጀበት ነጋሪት በነሐስ ተሰርቶ በሙዚየሙ ውስጥ ይገኛሉ።

የዓድዋ ድል መሃንዲሶች አፄ ምኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልት፣ የ12ቱን የጦር መሪዎች ሀውልት፤ በጦርነቱ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን እና የቤት እንሰሳት መታሰቢያ የቅርፃ ቅርፅ እና የአርት ሥራዎችንም ይዟል።

በጦርነት ግንባር ከዘመቱ 120 ሺህ ጀግኖች መካከል 45 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን እና በዐውደ ውጊያው ከመሳተፍ አልፈው ምግብ ዝግጅት እና ቁስለኞችን በመንከባከብ ሴቶች ለድሉ ቁልፍ ሚና መጫወታቸውን የሚዘክር ማስታወሻ ተቀምጧል።

የጀግኖች መታሰቢያ ሀውልት ማስታወሻ፣ የዓድዋ ድል ለፓንአፍሪካኒዝም ንቅናቄ ያበረከተውን አስተዋጽኦ የሚዘክር የአፍሪካ ከርታ እና የኅብረቱን አርማ እንደፀሐይ ብርሃን ፈንጣቂ ማሳያ ይዟል።

ከዓድዋ ጀግኖች መታሰቢያ ሐዉልት አጠገብ ደግሞ የአሁኑ ትውልድ በገንዘቡ በጉልበቱ በእውቀቱ ያለምንም ብድር እና እርዳታ በራሱ አቅም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እውን ማድረጉን የሚያመለክተው ፋውንቴን ተሰርቶለታል።

በነጋሪት ቅርጹ ትይዩ ያለው ስፍራ የዓድዋ ድል በዓል ማክበርያ ቦታ ነው። መታሰቢያ ዲዛይኑም ግንባታውም የግንባታ ቁጥጥሩም በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተሰራ እና የከተማዋን ገፅታ የቀየረ ነው።

default

በኢትዮጵያ የተሰራችው እና ከ88 ዓመታት ስደት በኋላ ወደ ሀገሯ የተመለሰችው ፀሀይ አውሮፕላን በዓድዋ ድል መታሰቢያ እንድትቀመጥ ተደርጓል።

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እና የዓድዋ ድል ትስስር የዓድዋ ዘመን ትውልድ በአንድነት እና በተባበረ ክንድ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት አስከብረው ነፃ አገር እንዳስረከቡን ሁሉ የዚህ ዘመን ትውልድ ደግሞ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በአንድነት እና በተባበረ ክንድ በመላ ኢትዮጵያውያን ርብርብ የኢትዮጵያን ሕዳሴ ያበሰረ የዘመናችን ዓድዋን ገንብቷል። ተምሳሌቱም የአኩሪ ታሪክ ግንባታችን ይቀጥላል የሚል ነው። (በላሉ ኢታላ፤ ኢቢሲ)

  • default
  • default
  • default
  • default
  • default
  • default
  • default
  • default
  • default
  • default

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News, Right Column Tagged With: adwa, African Victory, emperor menelik, Queen Tayitu

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule