ኢትዮጵያ ነጻነቷን ጠብቃ እንድትኖር ያደረጓት አባቶቻችንን የሚዘክር የዓድዋ ድል መታሰቢያ በአዲስ አበባ ፒያሳ ተገንብቶ ዛሬ ይመረቃል። መታሰቢያው የተገነባው ጀግኖች ወደ ጦርነቱ ሲተሙ በአንድነት ተሰባስበው ጉዟቸውን የጀመሩበት ቦታ ላይ ነው። የዓድዋ ድል መታሰቢያ ላይ የሚታየው 00 ኪሎ ሜትር መነሻ ቦታ የኮምፓስ ምልክት በአዲስ አበባ እንዲሁም በመላ ኢትዮጵያ ለሚገኙ ቦታዎች የርቀት መለኪያ መነሻ ነው። የዓድዋ ድል መታሰቢያ በ5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን 5 ወለል እና 8 በሮች አሉት። አጠቃላይ ከታች እስከ ላይ በ5ቱ ወለል ላይ ያለዉ መሬት ስፋት 12 ሄክታር ነው። ሙዚየሙ ከምድር በታች ያለውን ሁለት ደረጃዎችን ጨምሮ 5 ወለሎች አሉት። ከ1 ሺህ በላይ የመኪና ማቆሚያ፣ ሲሲቲቪ ካሜራ፣የራሱ መቆጣጠሪያ ያለው ስማርት ፓርኪን ሥርዓት … [Read more...] about የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ ይመረቃል