አንድ ሽማግሌ የነገሩኝ ታሪክ ትዝ አለኝ። ሰውዬው ጀግና ነኝ፣ አንበሳ በጡጫ ነብርን በእርግጫ እገላለሁ እያለ ይጎርራል። በኋላ ራሱ ደጋግሞ ያወራውን ጉራ እውነት ነው ብሎ ራሱ አመነው። አምኖም አልቀረ በጉራው የተሳቡ፣ በወሬው የተሰባሰቡ፣ አድናቂዎቹን አስከትሎ በረሃ ወረደ። እሱ ጀብድ ሊሠራ ሌላው ጀብድ ሊያወራ፣ ምን ለምን አብረው አዘገሙ። አድናቂዎቹን ከፍ ያለ ኮረብታ ላይ አስቀመጠና "ዛሬ ሶምሶንን በዓይናችሁ ታያላችሁ" አላቸው። እነርሱም አድንቀውና አዳምቀው እንዴት እንደሚያወሩት እያሰቡ ወደ አንበሳ መንጋ የሚወርደውን ጀብደኛ በማዶ ይመለከቱ ያዙ። ወረደ ጀብደኛው። አንበሶች ሰብሰብ ብለው ተኝተዋል። በሩቁ ድንጋይ ወረወረባቸው። ሁሉም አንበሶች ቀና ቀና አሉ። አንዱ በድንጋይ የተመታ ደቦል ዘሎ ወጣበትና በቅጽበት ሌሎች ገነጣጠሉት። ታሪኩም ከጄት ፈጥኖ ከውኃ ቀጥኖ … [Read more...] about ጀብደኛው