አንድ ሽማግሌ የነገሩኝ ታሪክ ትዝ አለኝ። ሰውዬው ጀግና ነኝ፣ አንበሳ በጡጫ ነብርን በእርግጫ እገላለሁ እያለ ይጎርራል። በኋላ ራሱ ደጋግሞ ያወራውን ጉራ እውነት ነው ብሎ ራሱ አመነው። አምኖም አልቀረ በጉራው የተሳቡ፣ በወሬው የተሰባሰቡ፣ አድናቂዎቹን አስከትሎ በረሃ ወረደ። እሱ ጀብድ ሊሠራ ሌላው ጀብድ ሊያወራ፣ ምን ለምን አብረው አዘገሙ። አድናቂዎቹን ከፍ ያለ ኮረብታ ላይ አስቀመጠና "ዛሬ ሶምሶንን በዓይናችሁ ታያላችሁ" አላቸው። እነርሱም አድንቀውና አዳምቀው እንዴት እንደሚያወሩት እያሰቡ ወደ አንበሳ መንጋ የሚወርደውን ጀብደኛ በማዶ ይመለከቱ ያዙ። ወረደ ጀብደኛው። አንበሶች ሰብሰብ ብለው ተኝተዋል። በሩቁ ድንጋይ ወረወረባቸው። ሁሉም አንበሶች ቀና ቀና አሉ። አንዱ በድንጋይ የተመታ ደቦል ዘሎ ወጣበትና በቅጽበት ሌሎች ገነጣጠሉት። ታሪኩም ከጄት ፈጥኖ ከውኃ ቀጥኖ … [Read more...] about ጀብደኛው
Fake Fano
ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል
በአማራ ክልል የተነሳውን ብጥብጥ አስመልክቶ በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ መታወጁ ይታወቃል። በመሆኑም በርካታ ከተሞች አገልግሎት መስጠት አቁመው ተዘግተው ቆይተዋል። ሆኖም የመከላከያ ኃይል የክልሉን ሰላም ማስጠበቅ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ከተሞች ሰላማቸውን እያገኙ ነው። በተለይ የክልሉ ዋና ከተማና ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ወደ ቀድሞ ሰላማቸው መመለሳቸውን ኢቢሲ በፎቶ አስደግፎ ዘግቧል። ወጣቶች ወደ መጫወቻ ቦታ እየሄዱ ጊዜያቸውን እያሳለፉ ነው፤ ዜጎች ወደ ቤተክርስቲያን መበሄድ በተለይ የፍልሰታን ጾም ሲካፈሉ ታይተዋል፤ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀምሯል፤ ንግድ ቀጥሏል፤ ዜጎች እየመጣ ባለው ሰላም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ፎቶዎቹ እሁድ ዕለት የተወሰዱ ናቸው። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል
የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል
በደብረ ታቦር 800 መቶ ብር የነበረ የምግብ ዘይት እስከ 1500 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው በአማራ ክልል በትልልቆቹ ከተሞች በዛሬው ዕለትም ተኩስ ሳይሰማባቸው መዋላቸውን፤ ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነዋሪዎች ምን አሉ? ባሕር ዳር ዛሬ የተኩስ ድምጽ አለመሰማቱን ፤ ግጭትም ይሁን ውጊያ እንዳልነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ አልጀመረም። የንግድና የተለያዩ ቋማት በአብዛኛው ባለመከፈታቸው ከተማዋ ጭር ብላ ነው የዋለችው። የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ መኪኖች እና ባጃጆች ወደ ሥራ ባለመመለሳቸው የነዋሪው እንቅስቃሴ ተገትቶ ውሏል። ተቋርጦ የነበረው የ 'ኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ' ወደ ባሕር ዳር መጀመሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነገር ግን ከአውሮፕላን ማረፊያ ወደ ከተማ የሚወስድ ትራንስፖርት … [Read more...] about የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል