"... አሁን ቱሪስት የለም" የላሊበላ ነዋሪ እስከ 2 ቢሊዮን የሚጠጋ ብርም ከዘርፉ ይገኝ ነበር የአማራ ክልል ቱሪዝም በግጭቱ ምክንያት ሥራ ለማቆም መቃረቡን የክልሉ የባህልና የቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ‼️ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የዐማራ ክልልን ይጎበኛሉ ተብለው ከታቀዱት የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ቁጥር የመጡት 20 በመቶ ብቻ መኾናቸውን የገለጸው የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ፣ የክልሉ ቱሪዝም በእጅጉ በመዳከሙ ሥራ ለማቆም መቃረቡን አስታውቋል፡፡ የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር አየለ አናውጤ ትናንት ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በክልሉ ተለዋዋጭ ገጽታ እያሳየ የቀጠለው የትጥቅ ግጭት፣ “ዘርፉን ጨርሶ ለማስቆም እየተቃረበ ነው፤” ብለዋል፡፡ በቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶችም፣ በግጭቱ ሳቢያ ከሥራ ገበታ ውጭ መኾናቸውን አመልክተዋል፡፡ (VOA) ጥር 7 2016 የታተመው … [Read more...] about ቱሪዝም በአማራ ክልል ሊቆም ነው