• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ቱሪዝም በአማራ ክልል ሊቆም ነው

July 6, 2024 03:06 pm by Editor 1 Comment

“… አሁን ቱሪስት የለም” የላሊበላ ነዋሪ

እስከ 2 ቢሊዮን የሚጠጋ ብርም ከዘርፉ ይገኝ ነበር

የአማራ ክልል ቱሪዝም በግጭቱ ምክንያት ሥራ ለማቆም መቃረቡን የክልሉ የባህልና የቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ‼️

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የዐማራ ክልልን ይጎበኛሉ ተብለው ከታቀዱት የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ቁጥር የመጡት 20 በመቶ ብቻ መኾናቸውን የገለጸው የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ፣ የክልሉ ቱሪዝም በእጅጉ በመዳከሙ ሥራ ለማቆም መቃረቡን አስታውቋል፡፡

የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር አየለ አናውጤ ትናንት ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በክልሉ ተለዋዋጭ ገጽታ እያሳየ የቀጠለው የትጥቅ ግጭት፣ “ዘርፉን ጨርሶ ለማስቆም እየተቃረበ ነው፤” ብለዋል፡፡

በቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶችም፣ በግጭቱ ሳቢያ ከሥራ ገበታ ውጭ መኾናቸውን አመልክተዋል፡፡ (VOA)

ጥር 7 2016 የታተመው የጀርመን ድምጽ ዘገባ ችግሩ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን ዶ/ር አየለ አናውጤ ጠቅሶ ዘግቦ መዘገቡ ይታወሳል። በአማራ ክልል በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ ክስተቶች የክልሉ የቱሪዝም እንቅስቃሴ በእጅጉ ማሽቆልቆሉን ነዋሪዎችና በክልሉ ተደጋጋሚ ጦርነት ከመከሰቱ ቀደም ብሎ በ2010 ዓ.ም 210 ሺህ የወጪ ቱሪስች አማራ ክልልን የጎበኙት መሆኑ ተጠቅሷል ።

በክልሉ በነበሩና ባሉ ችግሮች ምክንያት በ2016 ዓ.ም ግማሽ ዓመት ክልሉን የጎበኙ የውጪ ጎብኝዎች ቁጥር ከ3ሺህ 500 ብዙም እንደማይበልጡ ጽ/ቤቱ አመልክቷል። ከዘርፉ የተገኘው ገቢም በእጅጉ ቀንሷል ተብሏል።

በዓለም ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ በሽታ ምክንት ተጎድቶ የነበረው የቱሪዝም እንቅስቃሴ ያገግማል ተብሎ ሲጠበቅ እንደገና በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ቱሪዝሙን ከድጥ ወደ ማጡ ከትቶት ቆይቷል፣ ከሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በአማራ ክልል የተፈጠረው የሰላም እጦት የባሰ ቱሪዝሙንና በአስጎብኝነት የተሰማሩ ወጣቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እንደጎዳ አንድ በጎንደር ከተማ በአስጎብኝነት የተሰማሩ ነዋሪ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡

ድምፃቸው እንዲቀየር የፈለጉ የላሊበላ ከተማ ነዋሪና አስጎብኝም በክልሉ የተከሰቱ ተደጋጋሚ ችግሮች በቱሪዝም እንዳስትሪው ላይ የፈጠሩትን ጫና አስረድተዋል፡፡ ለውጪ ጎብኝዎችን በተለያየ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ አስጎብኝዎች ያለሥራ መቀመጣቸውን ደግሞ አንድ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ነግሮናል፡፡

“… አሁን ቱሪስት የለም፣ ላሊበላ ሲከበር ቱሪስቶቹ ከላሊበላ ወደ ባህር ዳር፣ ከላሊበላ ወደ ጎንደር ይመጡ ነበር። መንገዱ፣ የሰላሙ ሁኔታ ያን አላደረገም፣ አሁን ጥምቀት እየመጣ ነው፣ ግን እንቅስቃሴ የለም፣ ቤት ቁጭ ብለን ነው ያለነው፣ ያለው የቱሪዝም እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የሞተ ነው፣ የምንሰጠው አገልግሎት ቱሪስቱን ወደ ገዳማት መውሰድና መመለስ፣ እንግዶቹን ከአየር ማረፊያ መቀበል፣ ወደ ቱሪስት መዳራሻ መውስድ፣ ባለው ሁኔታ ግን አሁን ቱሪስትም አይመጣም ስራችንም ቆሟል፡፡ ቱሪስቶችን ወደ ጣና ገዳማት የሚወስዱ ወደ 150 ጀልባዎች ነበሩ፣ ወደ 80 ለቱሪዝም አገልግሎት የተዘጋጁ ተሸከርካሪዎች ነበሩ ሌሎችም፣ ይህ ሁሉ ሥራ አሁን አቁመዋል” ብለዋል።

“ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከመግባታችን በፊት የነበረው የቱሪስት ቁጥር ካለው እምቅ ሀብት አኳያ ዝቅተኛ ነው ቢባልም ጥሩ የሚባል ነበር፣ ከጦርነቱ በኋላ ባሉት ጊዜዎች ግን ቁጥሩ ከዓመት ዓመት እየቀነሰ ነው የመጣው፣ ከጦርነቱ በፊት በዓመት እስከ 270ሺህ የውጪ ቱሪስት አማራ ክልልን  ይጎበኝ ነበር፣ እስከ 2 ቢሊዮን የሚጠጋ ብርም ከዘርፉ ይገኝ ነበር፣ ወደ 2016 ዓ ም ስንመጣ በ2016 ዓም ግማሽ ዓመት  84ሺህ የዉጪ ጎብኚ ወደ ክልሉ ይመጣል ተብሎ ታቅዶ ነበር፣ ግን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ባለፉት 6 ወራት 10ሺህ 500 ያህል ብቻ ናቸው ወደ ክልሉ የመጡ የውጪ አገር ቱሪስቶች፡፡ በገቢ ደረጃ 238 ሚሊዮን ብር ነበር በግማሽ ዓመቱ የታቀደው፣ በግማሽ ዓመቱ ከውጪ አገር ጎብኝዎች የተገኘው ገቢ ግን ከ40 ሚሊዮን ብር  የበለጠ አይደለም” ብለዋል፡፡  

እንደ ዶ/ር አየለ ባለፉት 6 ወራት 11 ሚሊዮን የአገር ውስጥ ጎብኝዎች የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ታቅዶ የነበረ ሲሆን 4 ሚሊዮን ያህል የአገር ውስጥ ጎብኝዎች ወደ ቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች መድረሳቸውን አመልክተዋል፡፡ ከአገር ውስጥ ጎብኝዎች በ6 ወሩ ወደ 8 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ሲሆን አፈፃፀሙ ግን 1.6 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው ብለዋል፡፡ ከጦርነቱ በፊት ከአገር ውስጥ ጎብኝዎች ብቻ በዓመት እስከ 5 ቢሊዮን ብር ይሰበሰብ እንደነበርም ኃላፊው በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡

በርካታ ወጣቶች በአስጎብኝነትና ተያያዥ ሥራዎች ተሰማርተው እንደነበር ኃላፊው አመልክተው መልሶ ለማደራጀት እንቅስቃሴ እየተደረገ ባለበት ወቅት በክልሉ ተፈጠረው የሰላም እጦት ስራዎችን እንዳናከናውን አድርጎናል ብለዋል፡፡

“በማህበር ተደራጅተው፣ አንዳንዶቹ የማህበረሰብ ኢኮ ቱሪዝም አቋቁመው፣ ሎጂዎችንም ገንብተው፣ እየሰሩ የነበሩ ነበሩ በብዙ ቦታዎች በጎብኝ እጦት ምክንያት ተበትነው ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ አንዳንዶቹ የሚሰሩባቸው ኢኮ-ሎጂዎች በጦርነት ምክንያት ፈርሶባቸው ሥራ ያቆሙ ናቸው፣ አንዳንዶቹ እስከ ስደት ደረጃ የደረሱ እንዳሉ መረጃዎች አሉን፡፡”

ከወራት በፊት ከአውሮጳ ዘመዶቿን ለመጠየቅ በባሕር ዳር አካባቢ ጉብኝት አድርጋ የነበረ አንዲት የክልሉ ነዋሪን በመጥቀስ የጎልጉል መረጃ አቀባይ እንዳለው ግለሰቧ ባሕር ዳር ስትሔድ ያየችው ሁሉ አስደንግጧታል። ከቦሌ አውሮጵላን ተሳፍራ ስትሄድ ለወትሮው ባንድ በረራ ውስጥ እስከ ግማሽ ያህል የውጭ አገር ሰዎች ይሳፈሩ ነበር፤ እሷ በሄደችበት ጊዜ ግን አንድም የውጪ ዜጋ ተሳፋሪ አላየችም።

እዚያ በቆየችበት ጊዜም የተመለከተችውን ስትናገር፤ “ከተማዋ ድንዛዜ የሰፈነባት፣ ጎስት ታውን (ghost town) ትመስል ነበር፤ ባጃጆች አንድ ሰው ሲያዩ ሥጋ እንዳየ አሞራ ነው ሰው የሚከብ ቡት፤ ወደ ዘጌ ደሴቶች ለሚደረገው ጣናን አቋርጦ የመሄድ ጉዞ ቢዚ ሆነው ይውሉ የነበሩት ጀልባዎች አሁን ላይ የውሃውን ዳርቻ በሙሉ ሸፍነውት የሥራ ማቆም ዓድማ የመቱ ነው የሚመስለው፤ ወደ አዲስ አበባ ስመለስ አውሮጵላኑ ሞልቶ የነበረ ቢሆንም ከተሳፋሪ ውስጥ የነበሩት የውጭ ዜጎች ሁለት ብቻ ነበሩ” በማለት ትዝብቷን አጋርታለች። ስትቀጥልም “ይህንን ያየሁት ኅዳር እና ታኅሣሥ አካባቢ ነበር፤ ያኔ ለጓደኞቼ የነገርኳቸው አማራ ክልል ቱሪዝም ይቆማል ብዬ ነበር፤ ዛሬ ይህንን እንደ ትንቢት ተፈጽሞ ስሰማ ምንም አልደነቀኝም” ብላለች።  

ራሱን ፋኖ ብሎ በሚጠራው ብረት ባነሳ ኃይልና በመንግሥት መካከል የተከሰተው ግጭት በጦርነትና በትህነግ ወረራ ወድሞ የነበረውን ክልል ሳያገግም አከርካሪውን ብሎ ያሽመደመደው ሆኗል። የትህነግ ዘረፋ ክልሉን 14 ዓመት ወደኋላ የወሰደው ሲሆን እስካሁን ቀጥሎ ያለው መሪና ዓላማ ዓልባ ግጭት እጅግ ብዙ ዓመታት ክልሉን ወደኋላ እየወሰደው መሆኑ በገሃድ የሚታይ ሆኗል። ጉዳዩ በቶሎ ካልተቋጨ በአማራና በሌሎች ክልሎች መካከል የሚኖረው ሁሉን ዓቀፍ ልዩነት “ተበደልን” በሚል ሰበብ እንደገና ክልሉን ለማያባራ መከራ ውስጥ እንዳያስገባው አስተያየት ሰጪዎች ሥጋታቸውን ይናገራሉ።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News, Politics, Social Tagged With: amhara region, ethiopian terrorists, Fake Fano, Fano, no tourism, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    July 11, 2024 09:47 am at 9:47 am

    ጉቶ ሃሳብ ይዘው ሰው በሚታመስበት ምድር ስለ ቱሪዝም ማውራት ቧልት ነው። ሰው ከቤቱ ወጥቶ በሰላም የማይገባበት፤ የመንገድና የሰፈር እገታው በተራባበት ስፍራ የለቅሶ ጭኾትና ረሃብ ብቻ ነው ያለው። ምድሪቱ ዛሬም ትላንትም በግፈኞችና በዘር ሰካራሞች ትታመሳለች። ይህ ደግሞ ዛሬ ካለንበት የከፋ መከራን ያመጣና ለውጥ ነው ብለን እንሰለፋለን። ቆሻሻ የቋንቋና የዘር ፓለቲካ ከራሱ ሌላ ለእኛ ብሎ አስቦ አያውቅም። እኛነትን ያመከነው የክልል ፓለቲካ የዘመኑ የአፓርታይድ ስልት ነው።
    የምድሪቱን ገመና በቅርብ ከደረሰኝ አንድ ልብ የሚነካ ወሬ ልጀምር – የብሄር ሰካራሞች ድንገት ስፍራውን ይወሩና ሰውን ገድለው ያለውን ዘርፈው የቁም ከብቶችን ከጋጣ አውጥተው ነድተው ይሄዳሉ። በሶስተኛው ቀን የተነድት ከብቶች ሁሉም ባይሆኑ የሚበልጡት ከበረታቸው መተው ይቆማሉ። በጊዜው ጥጆችም ነበሩና ቆመው ያጠቧቸዋል። ወዲያው ታጣቂዎች መተው ሁሉንም በድጋሚ ነድተው ወሰዷቸው። ለእኔ ከሚገድሉትና ከሚዘርፉት የሰው ውሾች ይልቅ ከብቶቹ ለጥጃዎቻቸው ማሰባቸው ከገልቱ ታጣቂዎቹ የተሻሉ እንደሆኑ ያሳያል። የአማራ ክልል እየተባለ በሚጠራው ፋኖና ብልጽግና መፋለም ከጀመሩ ወዲህ ሰው ሰላሙን ተቀምቶ፤ የሚሰራው ተቀምጦ፤ ተማሪው ትምህርቱን አቋርጦ፤ የመንግስትና የግል ተቋማት ተዘርፈውንና ወድመው እንደ ግመል ሽንት ነገር ሁሉ ወደኋሊት እየሄደ የአማራን ህዝብ ነጻ ልናወጣ ነው ይሉናል። ነጻ የሚወጣው ከማን ነው? ነጻነቱስ ለማን ነው? ነጻ እናወጣሃለን የሚባለውን ህዝብ እየገደሉና እያስገደሉ ነጻነት ብሎ ነገር የለም። እብድ ብቻ ነው የራሱን ቤት እሳት ለኩሶ አማረብኝ የሚል!
    ዛሬ በውጭም ሆነ በውስጥ በድጋፍም ሆነ በተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙ ሃበሾችም ሆነ ነጮች የየራስ አጀንዳ አላቸው። ነጩ ዓለም ለጥቁሩ ዓለም ደንታ እንደሌለው ከበፊት ተንኮላቸው የፓትሪስ ሉቡምቧን አሟሟት፤ ከቅርብ ታሪክ ደግሞ የሊቢያውን የጋዳፊን ሞት ማየት በቂ ነው። ነጩ ዓለም የጥቁር ህዝቦችን ልዕልና ተመኝቶ አያውቅም። አሁንም በአንድ በኩል ስለ ሰላም እየተናገሩ በሌላ በኩል የሽግግር መንግስት ይቋቋም የሚሉን በራሳቸው ስሌትና ትርፍ አስልተው እንጂ ለኢትዪጵያ ህዝብ ሰላምና ብልጽግናን ተመኝተው አይደለም። የኢትዮጵያ ትልቁ ችግሯ የብሄር ፓለቲካና የክልል (አፓርታይድ) የፓለቲካ ስሌት ነው። ሰውን በሰውነቱ ማስላቱ ቀርቶ በቋንቋውና በክልሉ ብቻ ማስጠጋትና ማባረር የራስን መከራም ማቃረብ እንደሆነ ለእነዚህ የብሄር ድርቡሾች አይገባቸውም። በሽታው የማይድን በመሆኑ ሞት ብቻ ነው ገላጋዪ።
    የብልጽግናው መንግስት ከደርግና ከወያኔ የአፈናና ግድያ ውድቀት የተማረ አይመስልም። ያንኑ ገመና ይደግመዋልና! አሁንም ያዘው ጥለፈው፤ እኛን ማንም ንቅንቅ አያደርገንም የሚባል ድንፋታ የሰላም ጥሪ ሳይሆን ክፋት እንዲራባ የሚያድርግ ነው። የሰው ልጅ በምድሩ በሌላው ወገኑ የፍጥኝ ታስሮ የሚገረፍበት፤ ጥፍሮቹ የሚወልቁበት፤ ምስማር ላይ በባዶ እግር እንዲራመድ ማድረግ፤ ከአንድ መንግስት የሚጠበቅ አይደለም። በዚህ ላይ በስማ በለው ወሬ ያለ መረጃ ሰዎችን ሁሉ እያጋፈፉ ለእስርና ለእንግልት መዳረግ ሰውን የባሰ መራራና ቁርጠኛ ያደርገዋል እንጂ አሜን ብሎ እንዲቀመጥ አያደርግም። ጊዜው ሳይመሽ የብሄር ተፋላሚዎቹም ሆኑ ብልጽግና ቁጭ ብለው ቢመክሩ መልካም ይመስለኛል። ያኔ ስለ አማራ ቱሪዝም እናወራለን። አሁን ዳቦ አሮበት ነፍሱን ለማዳን ለሚሯሯጥ ህብረተሰብ ስለ ቱሪዚም ደንታም አይሰጠውም። ወይም ቁልጭ ብሎ ከታየው እንደ ስፔኖች ቱሪስቶችን ወደ መጡበት እንዲሄድ የሚጠይቅ ይመስለኛል። የምበላው የለኝ የምደርበው አማረኝ አይነት ይሆንና ነገሩ። ዋ አለማችን ያለቅጥ እያጋደለች ነው። አሁን ልክ ነው ብላችሁ የያዛችሁት ነገር ቆይቶ ፉርሽ ቢሆን ጸጸቱ አይወጣላችሁም። ለሰላም፤ ለሰው ልጆች አንድነትና መብት እንታገል። ሌላው ሁሉ አሻሮ ሃሳብ ነው። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule